ልብ አንጠልጣዩ "የጠፋው ሬሳ"
ተከታታይ ትረካ
#ክፍል_፲፪
...በጣም ደነገጥኩኝ አንዳች ነገር ሆነው እንደው ብዬም ተጨነኩኝ ባባ ይቁነጠነጣል ምን እንደሚያደርግ ፈፅሞ ግራ ገብቶታል ግን ከትንሽ ደቂቃ በሗላ ሁለቱም መጡ ባዩኝ ጊዜ በጣም ደነገጡ ባርሳም ወደኔ እየመጣች "ምንድነው ሜርሲ ምን ሆንሽብኝ" አለች ምንም መልስ አልሰጠሗትም ቅድስቴም እኔን አይታ "ከዚህ ቦታ አሁኑኑ ተነስተን መሄድ አለብን አንድ በአንድ ከማለቃችን በፊት" አለች ትዕዛዝ የሆነ ንግግር ቁጣም ቀላቅላበት "አሁን ተረጋጉ መጀመሪያ ሜርሲን ወደ ሀኪም ቤት እንውስዳት" አለ ባባ ድንኳኖቹን እየነቃቀለ እነ ባርሳም ሌሎች ዕቃ በማዘገጃጀት እያገዙት...ቅድሚያ እኔን ወደ መኪናው ወሰዱኝና እነሱ እየተመላለሱ ዕቃዎቹን ጫኑ ከደቂቃ በሗላ ጉዞ ጀመርን በተቀመጥኩበት የጋቢና መስኮት በኩል ፊቴን መስታወቱ ላይ ተደግፌ አይኔን ወደ ውጪ ልኬ ያንን ክፉ ጫካ እየተመለከትኩ ጉዞዬን ቀጠልኩ እጅግ በጣም ሰፊ ቦታ የያዘ ውስጡ ጨለማ የሆነ ጫካ ነው ከዚ ስፍራ በሰላም መውጣታችን እጅግ ድንቅ ነው..."አይዞሽ የኔ ጓደኛ ምንም አትሆኚም" አለች ባርሳ በእጇ ትከሻዬን እየነካች እሺታዬን በአንገቴ ንቅናቄ ገለፅኩላት ጉዟችን ለረጅም ደቂቃዎች ፀጥታ የተሞላበት ነበር ሁላችንም የድንጋጤ ስሜት ላይ ስለሆንን ይመስለኛል ከግማሽ በላይ ለሆኑ ደቂቃዎች ጉዞ በሗላ አንድ የድሮ ሆስፒታል ተመለከትን ታፔላው እንኳን የለም ነበር በሽተኛም ሆነ ዶክተር በዙሪያው አይታይም ባዶ ነበር መኪናችንን ከመግቢያው ትየይዩ አድርገን አቆምናት "እዚሁ ጠብቁኝ" አለ ባባ ከመኪናው እየወረደ ውስጡ ገብቶ ያለውን ነገር ቃኝቶ መግባት እንደምንችል ነገረን እነ ባርሳ ቀድመው ወርደው በጥንቃቄ ከመኪናው አወረዱኝና መሸከም የሚለው ቃል በሚገልፀው ድጋፍ ደግፈውኝ ወደ ውስጥ ገባን ፍፁም ፀጥ ያለ ስፍራ እርገግጠኛ ነኝ ከኛ ሌላ በዚ ሆስፒታል ውስጥ የለም ባባ ከኛ በፊት እየተራመደ ወዴት መሄድ እንዳለብን እየመራን ነው ከጥቂት እርምጃ በሗላ ከአንድ ክፍል በር ላይ ቆመ ወደ ውስጥም እንድንገባ ምልክት ሰጠን ገባንም ወዲያው ክፍሉ ውስጥ ካለው አልጋ ላይ አስተኝተውኝ መድሀኒት መፈለጉን ተያያዙት በነገራችን ላይ ቅድስቴ የህክምና ተማሪ ነች "አይዞሽ ሁሉም ሰላም ይሆናል አለ ባባ ከዛም ቅድስቴ በደረቴ መተኛት እንዳለብኝ ነግራኝ ለሶስት ገለበጡኝ የጭንቅላት ቁስሌን ለማከም እንዲመቻት...ከዛም ቁስሉን ለመመልከት ፀጉሬን ስትገለጥ ቁስሌ ላይ ተጣብቆ ኖሮ እጅግ አመመኝ ግን ህመሙን ጨክኜ ያዝኩት ከዛም ፀጉሬን መቁረጥ ጀመረች ባርሳ ከፊት ለፊቴ ካለው ወንበር ላይ ሆና አይዞሽ እያለች ታበረታኛለች አሁን ቅድስት ቁስሉን ለመመልከት ግልፅ ሆነላት መሰል መሰፋት አለበት አለች በሰለለ ድምፅ ሆኜ "እንደዚ አይሆንም እንዳታደርጊው" አልኳት "የጭንቅላትሽን ክፍተት ቶሎ ካልሸፈነው ወደ ሌላ ኢንፌክሽን ሊቀየር ይችላል እዛ ደረጃ ከመድረሱ በፊት አሁን ላይ እንፍጠን" አለች ባርሳ ጭንቅላቷን በመነቅነቅ በቅድስቴ ሀሳብ መስማማቷን ገለጸች "ግን እርግጠኛ ነሽ ይሄን ማረግ ትችያለሽ?" አለ ባባ እርግጠኛ ለመሆን እየጠየቀ "በኔ ተማመን ምንም አይፈጠርም" አለች ባባም ተስማማ እኔም ውስጤን አሳመንኩትና ተዘጋጀሁ የዶክተሮቹን ጓንት አድረገችና በሆነ ፈፃሽ ቁስሌን ማጠብ ጀመረች በትንሹ የማቃጠል ስሜት ይሰማኛል "አቃጠለሽ እንዴ" አለችኝ ቅድስቴ "በትንሹ" ብዬ መለስኩላት "ሰውነትሽ እየደነዘዘ ነው ማለት ነው" ብላ መለሰችልኝ "እንደዚም ቢሆን ግን ማደንዘዣ ያስፈልገናል" አለች ቅድስቴ በቁራጭ ወረቀት ላይ የሆነ ነገር ፅፋ "ይሄን መድሃኒት ፈልጉ" አለቻቸው እነ ባባን "ከየት" አለች ሜርሲ ግራ በመጋባት "ከክፍሎቹ አንዱ የመድሃኒት ማከማቻ መሆኑ አይቀርም ፈልጉና አምጡ" ብላ ትዕዛዝ ሰጠች እነሱም ተቀብለው አብረው ወጡ ከዛ ጫማዬን ፈትታ የእግሬን ቁስል መመልከት ጀመረች "የወጋሽ ነገር ብረትነት አለው" ብላ ጠየቀችኝ "እሾህ ነው መሰለኝ አላስተዋልኩትም" ብዬ መለስኩላት "ለማንኛውም ለጥንቃቄ ቲታነስ መወጋት አለብሽ" አለችኛና መድሃኒቷን ማዋሃድ ጀመረች "ከዚ ክፍል የጠፋ ወይም ህክምናውን ሳይጨርስ የወጣ ሰው አለ " አለችኝ በጣም ግራ ተጋብቼ "በምን አወቅሽ" ስላት የህክምና ካርዱ እና እዚ ያሉት መድሃኒቶች የሱ ናቸው" ብላ መለሰችልኝ "ስሟ ማን ይላል" ብዬ ጠየኳት እሷም እያነበበች ድንጋጤ በሚመስል መልኩ ግንባሯን አጨማደደች "ምነው" አልኳት...
_part #13 ___ ይቀጥላል
ቶሎ እንዲለቀቅ 👍 አሳዩኝ
ከተመቻቹ ÷
#𝐑𝐞𝐚𝐜𝐭
#𝐂𝐨𝐦𝐦𝐞𝐧𝐭
#𝐬𝐡𝐚𝐫𝐞 🙏
¶ 𝚈𝙴𝙵𝙸𝙺𝙴𝚁 𝙲𝙻𝙸𝙽𝙸𝙲🥀 ¶™🌐
📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! 📱