ልብ አንጠልጣዩ "የጠፋውሬሳ"
ተከታታይ ትረካ
#ክፍል_14
...በጣም ደነገጥኩኝ አንዳች አደጋ ደርሶበት ወደዚ ሆስፒታል መጥቶ ነበር ግን ለምን ህክምናውን ሳይጨርስ ወጣ? ማንስ ሊያስወጣው ቻለ? ዶክተሮቹስ የት ሄደው ነው? የሚሉ መልስ አልባ ጥያቄዎች አይኔን ጫማው ላይ ተክዬ ሳለ ውስጤ ይመላለሱ ነበር ከጫማው ትንሽ ተስፈንጥሮ አንድ ግራ ሚያጋባ ነገር ተመለከትኩ ለማየትም እንዲያመቸኝ ወደፊት እየተጠጋሁ ሳለ ባርሳ "ሜርሲ" እያለች ስጠራኝ ተሰማኝ እኔ ያለሁበት ስፍራ ከመጡ የሚፈጠረውን ስሜት ስለማውቀው ቶሎ ወደ ሆስፒታሉ ተመለስኩ እግሬ ቢያስነክሰኝም እርምጃዬን ፈጠን አድርጌ ወደነሱ ሄድኩኝ ሳያቸው ሶስቱም ፊት ላይ አንዳች ልዩ ነገር ይታየኛል "የት ሔደሽ ነው?" አለች ሜርሲ በንዴት ስሜት ውስጥ ሆና የሷን ጥያቄ መመለስ ሳልጀምር ቅድስቴ ተከተለች "በቅጡ እንኳን የረባ ህክምና ሳታገኚ ምንድነው ሚያዞርሽ" አለችኝ በጣም ደነገጥኩት "ምን የተፈጠረ ነገር አለ" ብዬ ጥያቄዬን ቀጠል አደረኩኝ "የመኪናችንን ጎማ ማን እንደሆነ እንጃ በሆነ ነገር ወግቶታል" አለ ባባ ወዲያውኑ ያ ሰው ነበር ጭንቅላቴ ውስጥ ብልጭ ያለው "የመንደሩ ነዋሪ መሆን አለበት ማለትም ያ አንቺ ከምታስቢው ሰውዬ ሌላ" አለ ባባ እንዴት እንደዚ ማለት እንደቻለ ጥያቄ ፈጥሮብኛል ሆኖም ግን ምንም አላልኩትም ነበር...መልስ ሳልሰጣቸው ወደ መኪናው እያነከስኩኝ ሄድኩ እነሱም ከሗላዬ ተከተሉኝ የሗላው ጎማ ነበር የተወጋው...የቆምንበት ስፍራ ከአስፓልቱ ወረድ ብሎ ስለነበር አፈርማ ነው ግን መኪናው ዙሪያ ምንም አይነት የእግር ኮቴ የለም ከእኛ ውጪ...ከኛ መኪና ትንሽ ተስፈንጥሮ የሆነ ነገር ተመለከትኩ እያነከስኩኝ ተጠጋሁ "ምንድው ሜርሲ" አለችኝ ባርሳ የማየውን ነገር እስካረጋግጥ ድረስ ምንም አላልኳትም ነበር ግን ከእኛ ሌላ እዚ አካባቢ የቆመ መኪና እንዳለ ይሰማኛል እኛ ከቆምንበት በተቃራኒ አቋቋም የሆነ መኪና እንደነበር ያስታውቃል...ግን ሙሉ ለሙሉ ከአስፓልቱ ወርዶ አልቆመም ነበር በአንድ ጎን ያሉት ጎማዎች ናቸው አፈሩ ላይ ያረፉት አሁንም የጎማውን ቅርፅ ወዳየሁበት በጥንቃቄ መመልከት ጀመርኩኝ ይመስለኛል መኪናው ለኛ መኪና ጀርባውን ሰጥቶ ነው የቆመው አቅጣጫው ደሞ እና በቆምንበት ነበር...አተኩሬ ስመለከት የሰው የእግር ኮቴ አለ ኮቴውን እየተመለከትኩ ተጠጋሁ ብዙ ዱካ የለውም ከአምስት እርምጃ በላይ አልተራመዳም ታዲያ ወደመኪናችን እንዴት ሊደርስ ቻለ የሚለው ጥያቄ ውስጤ እያሰላሰልኩ ያለፍኳቸውን የእግር ዳና ድጋሜ እየተመለከትኩ ሳለ አስፓልቱ ላይ የእግር ዱካ ተመለከትኩ ይህ ሰው ካቆመው መኪና እስኪያልፍ ብቻ ነው የተራመደው ከዛ በአስፓልቱ ተራምዶ ወደ መኪናችን ይደርሳል አሁን ጥርጣሪዬ እውነት እየመሰለ ነው...እነ ሜርሲም የማየውን ነገር ሲያዩ የሆነ ነገር እንደተገለጠላቸው ያስታውቃሉ ወዲያው የመኪናው የፊት ጎማ ወዳረፈበት ተጠጋሁ ሲገባና ሲወጣ ይመስለኛል በዛ ያለ ዱካ ይታያል "ያ ሰው አሁንም እየተከታተለን ነው አልተወንም" አልኩኝ "ምነው እግራችንን በቆረጠው ባንመጣስ" አለች ባርሳ እጅግ ተበሳጭታ "አሁን ማማረሩን ትተን ከዚ አካባቢ የምንሄድበትን መንገድ እንፍጠር መዋከቡ ዋጋ ቢስ ነው" አለች ቅድስቴ የማልጠብቀውን የእርጋታ ስሜት እያሳየች "ልክ ብለሻል" በማለት ባባ በሀሳቧ ተስማማ "ትርፍ ጎማ አልያዝክም" ብዬ ባባን ጠየኩት በጭንቅላቱ ንቅናቄ አለመያዙን ነገሮኝ ቀጠል አርጎ "ጎሚስታ ቤት ነው ያለው ኔትወርክ እንኳን ቢኖር ብደውል ይልኩልኝ ነበር" አለ "እና ዛሬ እዚ ልናድር ነው" አለች ባርሳ በጭንቅላቴ ንቅናቄ አውንታዬን ገለፅኩላት ቢመራትም ትዋጠው ምንም ምርጫ የለንም እዚ ባናድር መልካም ነበር ግን አለማደር አንችልም...ሰዓቱ ተጉዞ ወደ አመሻሹ እየተቃረበ ነው ከመኪናው ውስጥ ምግብና አልባሳት ይዘን ወደ ሆስፒታሉ ውስጥ ተመለስን እኔ ከታከምኩበት ክፍል ፊት ለፊት ገባንና ማስተካከል ጀመርን እኔም ልብሴን ለመቀየር ወደ ሻንጣዬ ሄድኩኝ ለአይን ያዝ ያዝ ማረግ ጀምሯል ባባ መብራት ካለ ብሎ ሲሞክር ምንም የለም "መቆጣጠሪያው ጋ አይቼ ልምጣ" ብሎ ባባ ወጣ "ተጠንቀቅ አባቴ" አለች ባርሳ በስስት እያየችው ይሄን ጊዜ ቅድስቴ አይኗ እንባ አረገዘ የባሰ እንዳይከፋት ብዬ ምንም አላልኳትም እኔም ልብሴን ቀያይሬ ተቀመጥኩ ባባ ተሳካለት መሰለኝ መብራቱ በራ "የስ" አሉ ቅድስቴና ባርሳ እኔም ፈገግ አልኩኝ ወዲያውኑ ምግቡን አቀራረቡት ባባም መጣና ለመመገብ ተዘጋጀን በሩን ዘጋንና መመገባችንን ጀመርን አሁን ምሽቱ ጀምሯል ነፍሴ እየተጨነቀች ነው...እየተጨዋወትን መመገባችንን ቀጠልን ግን መብራቱ ጠፋ በጣም ደነገጥን ሁላችንም ፀጥ አልን የሆስፒታሉ አንዱ ክፍል በሃይል ጓ ተደርጎ ተዘጋ በጣም ደነገጥን ግን መብራቱ ወዲያውኑ መጣ ውጪ ያለውን ነገር ለመመልከት ሁላችንም ተነስተን በሩን ከፍተን ወጣን ግን አንዳች አልነበርም ወዲያውኑ ድጋሜ መብራቱ ጠፋ ግን ባሁኑ ብዙ አልቆየም ከመቅፅበት መጣ ደግሞም ጠፋ ድጋሜ ሲበራ ግን................
part #15 ___ ይቀጥላል
ቶሎ እንዲለቀቅ 👍 አሳዩኝ
ከተመቻቹ ÷
#𝐑𝐞𝐚𝐜𝐭
#𝐂𝐨𝐦𝐦𝐞𝐧𝐭
#𝐬𝐡𝐚𝐫𝐞 🙏
¶ 𝚈𝙴𝙵𝙸𝙺𝙴𝚁 𝙲𝙻𝙸𝙽𝙸𝙲🥀 ¶™🌐
📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! 📱