. ም.1 #የመጨረሻው ክፍል
ተከታታይ ትረካ
#ክፍል_24
...ላይ ሊያሳርፈው ሲል ራሴን ከሆስፒታሉ ጥግ ላይ ተኮራምቼ ሳላስበው ይዞኝ ከተመመው የሰመመን እንቅልፍ ጉዞ ተመልሼ ከእንቅልፌ ነቃሁ ደህና መሆኔን አላመንኩም ራሴንም ጠርጥሬ ከተቀመጥኩበት ተነስቼ ደጋግሜ ሰውነቴን እየደባበስኩ ደህንነቴን አረጋገጥኩ...እኔ ብዙ ጊዜ ነፍሴን ያስጨነቃትን ነገር ነው በህልሜ ማየው...እየደባበስኩ ደህንነቴን እየተመለከትኩ ሳለ አይኔ የቅድስቴ በድን ላይ አረፈ እዛው እንደተንጋለለ ነበር ማንም አልነካውም ቀስ ብዬ ተጠጋሁ በእጄም እጇን ነካሁት ገላዋ ከቀረዶ በልጦ ቀዝቅዟል የሷን በድን ምን ማድረግ እንዳለብኝ እያሰብኩኝ ሳለ በድንገት የእግር ኮቴ ሰማሁ ወዲያውኑ አጠገቤ ካለው ክፍል ገብቼ ራሴን ከሚመጣው ሰው ሸሸኩኝ እየመጣ የነበረውም ሰው ያ አረመኔ ጨካኝ ገዳይ ነበር በድኑን ሊወስድ እንደመጣ ገመትኩኝ ልክም ነበርኩ ልክ በድኑ ጋ ሲደርስ በርከክ አለና እላዯ ላይ የደረቀውን ደም በጣቱ ፈቅፍቆ ወደ አፉ ሰደደው ቀምሶትም በደም የበለዘ ጥርሱን ፈገግ አደረገ...ከዛም ፀጉሯን ይዞ እያንፋቀቀ መሬት ላይ እየጎተተ ይዟት መሄድ ጀመረ እኔ ካለሁበት ክፍል ትንሽ ራቅ ሲል ርቀቴን ጠብቄ መከተል ጀመርኩኝ በድን ሳይና በደም ስጨማለቅ የመጀመሪያዬ ነው ነገር ግን ከዚህ በፊት ይህን ሁሉ ክስተት እንደተመለከተ ሰው ልቤ ደንዳና ሆኗል...ብቻ አንድ ነገር መሆን አለበት ከዚህ አካባቢ እነዛን ሶስት አረመኔዎች ገድዬ እወጣለሁ ወይ ደግሞ እንደጓደኞቼ እዚሁ እቀበራለሁ ስጋዬንም ይቀራመቱታል እንጂ መቼም ቢሆን አልሸሽም...ትንሽ እንደተጓዘም በህልሜ ወዳየሁት መበለቻ ክፍል ይዟት ገባ ይሄን ሰው ማጥቃት ካለብኝ እንደዚህ ክፍል ሊያመቸኝ የሚችል የለምና እራሴን በጥንቃቄ አዘጋጀሁ ልክ ክፍሉ በር ጋር ስደርስ አንገቴን ወደ ውስጥ አስግጌ ተመለከትኩ ክፍሉ ፀጥ ረጭ ብሏል አንድም ሰው አልነበረም የቅድስቴም በድን የለም ወደ ክፍሉም ዘለቅ ብዬ ገባሁ እስካሁን ያላየሁት የተለየ በር ተከፍቷል ወደሗላም ተመልሼ የሚከተለኝ ሰው አለመኖሩን አረጋገጥኩ በተከፈተው በርም ቀስ ብዬ ወደ ውስጥ ገባሁ ነገር እጅግ የሚሰነፍጥ ከባድ የስጋ ሽታ ክፍሉ ላይ ሰፎበታል ሽታውን መቋቋም ስላልቻልኩ ወዲያውኑ ተመለስኩኝ ከዛም አንድ ሀሳብ አሰብኩኝ ከውስጥ የለበስኩን ቲሸርት ቀድጄ አፍንጫዬንና አፌን ሸፈንኩበት ወደ ውስጥም አመራሁ አልፎ አልፎ ቢሆን ሽታው ወደ ውስጤ ይገባል ነገር ግን ከመጀመሪያው የተሻለ ነበር ይህ ክፍል የተለየ ክፍል ነው እንደሌሎቹ ያን ያህል ብርሃን የለውም ጨለም ያለ ነው...አሁን ሙሉ ለሙሉ ወደ ውስጥ ገብቻለሁ ነገር ግን ከፊት ለፊቴ ከሚታየኝ የላስቲክ መጋረጃ በቀር አንዳች ነገር አይታይም ወደ ላስቲኩም እርምጃዬን ጀመርኩ ቀስ ብዬ ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ ነው እንቅስቃሴዬን የማረገው ከቅድሙ ይልቅ ነበር እየበረታ መጣ ቢሆንም ግን ገዳይን ለመግደል ጉዞ ላይ ነኝ ላስቲኩን ገለጥ አድርጌ ወደ ውስጥ ገባሁ አይኔም ቀድሞ ያረፈው ወደላይ ከተንጠለጠሉት በላስቲክ የታሰሩ ነገሮች ላይ ነበር ምን እንደሆኑ ግን መለየት አልቻልኩም በእያንዳንዱ በተሰቀሉት ነገሮች በታች ለሁላቸውም ጠረጴዛ አለ መስመራቸውን ጠብቀው ነበር በረድፍ የተደረደሩት እየተጓዝኩም ወደ መሃላቸው ተጠጋሁ ወደ አንዱም የታሰረ ላስቲክ ቀረብ ብዬ ስመለከት ውስጡ ነጫጭ የስጋ ትሎች ይርመሰመሳሉ ይሄን ባየው ጊዜ በድንጋጤ ወደሗላ ስመለስ ከአንዱ የላስቲክ እስር ጋር ተጋጨሁ ሲንቀሳቀስም ድምፅ አወጣ በሁለት እጆቼም ይዤ ለማቆም ሞከርኩኝ ነገር ግን ያ ክፉ ሰው ድምፁ ወደተሰማበት ቦታ ሲመጣ ኮቴው ተሰማኝ ይሄንንም ባረጋገጥኩ ጊዜ ከአንዱ ጠረጴዛ ስር ተደበኩኝ የሆነ ስለት መሬት ላይ እየጎተተ እንዳለ ከሚሰማው የሚሰቀጥጥ ድምፅ ተረዳሁ እኔም የያዝኩን ስል ቢላ አሰናድቼ መጠበቄን ጀመርኩ ጠረጴዛዎቹ ረዘም ባለ ላስቲክ ስለተሸፈኑ ከስር ያለውን ነገር ካልተገለጠ በቀር በቀላሉ አያሳዩም ይሄ ነገር ትንሽም ቢሆን ሰላም ሰቶኛል መሬት ላይ ሲጎተት የነበረው የስለት ድምፅ አሁን ላይ ወደ ጠረጴዛዎቹ ላይ የተቀየረ ይመስላል...ይህንንም ከምሰማው ድምፀሸ ለይቻለሁ...እየቀረበኝ እንደሆነ ኮቴው ይነግረኛል ውስጤ ግን ቅንጣት ፍራቻ አልነበረበትምዝግጁ ነበር እኔ ያለሁበት ጠረጴዛ እጅግ ተቃርቧል ልቤ ባይፈራም የልብ ምቴ ግን አብዝቶ ጨምሯል በእልህ ከንፈሬን ነክሼ ሁኔታውን መጠባበቅ ጀምሬያለሁ ለሚመጣው ነገር ምላሽ ለመስጠት ሙሉ በሙሉ ነኝ መዳፌ ጠንከር ብሎ ቢላውን ጨብጧል በቀል ውስጤ እንደ ዘይት ይፈላል ቁጭት አንጀቴን ይበላኛል ምሬት ውስጤ ይርመሰመሳል ነገር ግን ሳላስበው እያላበኝ ነበር ከጥቂት እርምጃዎች በሗላ ካለሁበት እና ከተደበኩበት ሰፍራ ደርሷል እኔ ጋር ሲደርስም ቀጥ ብሎ ቆመ ጊዜ ሳያባክን ወዲያውኑ አጎንብሶ ላሲቲኩን ሲገልጠው...................
"#የጠፋው_ሬሳ"
"#የጠፋው_ሬሳ"
"#የጠፋው_ሬሳ"
"#የጠፋው_ሬሳ"
ምዕራፍ #አንድ በዚህ መልኩ ተጠናቋል
ምዕራፍ ሁለትንም ለመቀጠል የእናንተ ፍላጎት ይወስናል በcomment box ውስጥ ተነጋገሩ
በቅርብ ቀን እንጀምራለን
አስተያየት ወይም ጥያቄ ካላችሁ በውስጥ መስመር አድርሱኝ
👉 @Chanaz_72
👉 @Firaan90
ምዕራፍ 2 ___በቅርቡ....
#𝐑𝐞𝐚𝐜𝐭
#𝐂𝐨𝐦𝐦𝐞𝐧𝐭
#𝐬𝐡𝐚𝐫𝐞 🙏
¶ 𝚈𝙴𝙵𝙸𝙺𝙴𝚁 𝙲𝙻𝙸𝙽𝙸𝙲🥀 ¶™🌐
📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! 📱
ልብ አንጠልጣዩ "የጠፋው ሬሳ"

ከተመቻቹ ÷
#𝐑𝐞𝐚𝐜𝐭
#𝐂𝐨𝐦𝐦𝐞𝐧𝐭
#𝐬𝐡𝐚𝐫𝐞 🙏
¶ 𝚈𝙴𝙵𝙸𝙺𝙴𝚁 𝙲𝙻𝙸𝙽𝙸𝙲🥀 ¶™🌐
📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! 📱