እንዲያ_ነኝ 🥹
:
:
« ሳቄ መለያዬ ነው። ለመሳቅ መስፈርት የለኝም። ሰዎች በሳቄ ነው የሚያስታውሱኝ። ለመደሰት ትንሽ ነገር የሚበቃኝ ሰው ነኝ። ተው ዝም ብለክ አትገልፍጥ ሲሉኝ ግራ ይገባኛል። አሁን መሳቅ ፈገግ ማለት ምን ችግር አለው እላለሁ። አይገርምም ግን እያደግኩ ስመጣ ግን ነገሮች እየተቀያየሩ መጡ። ሰዎች ቁም ነገር አልባ እና ሁሌም ህፃን አድርገው ይመለከቱኝ ጀመር።
አንተ አይገባህም! አንተ ምን አለብህ? እንተስ የደላው የለም ይሉኛል። ከፍቶኝ እንኳ ከፍቶኛል ስላቸው ከቀልድ ይቆጥሩታል!
ለካ አንዳንዴ ፈገግታና ሳቀ ሰው ያሳጣል! ለካ ከቁም ነገረኛ ለመቆጠር ትንሽ መጨፈገግ፣ ሳቅና ፈገግታን ማፈን ይጠይቃል። አሁን አሁን እንደ ድሮው ባይሆንም እስቃለሁ፣ ግን እንደ ድሮው ሳቄ ቶሎ አይመጣም።
እኔኮ ስንት ነገር በውስጤ አፍኜም እስቃለሁ። የሚያባብለኝ ስለሌለም እንዲሁ እስቃለሁ። የሚጠይቀኝ ባይኖር ሳቅና ፈገግታ ለሚያበዛ ሰው ስለ ልቡ ደህና መሆንና ደስተኛ ስለመሆኑ መጠየቅ ነውር ተደረገ እንዴ እላለሁ። ደስተኛ ነው ተብሎ ተፈርዶበት አድማጭ አጥቶ፣ የልቡን ለማውራት ሲሞክር አትቀልድ እየተባለ እንዲሁ እንደሚስቅ ሰው ግን የሚያሳዝን ሰው ግን አለ? ሃሃሃ… ነገሩ ግን ያስቃል። እኔ ግን አሁንም መሳቅ አላቆምኩ ምኑ ጋር ነው ጥፋቴ እስኪ ንገሩኝ እእእእእ.............
{ ብቻ እኔ እንዲያ_ነኝ! » }
ከተመቻቹ ÷
#𝐑𝐞𝐚𝐜𝐭
#𝐂𝐨𝐦𝐦𝐞𝐧𝐭
#𝐬𝐡𝐚𝐫𝐞 🙏
¶ 𝚈𝙴𝙵𝙸𝙺𝙴𝚁 𝙲𝙻𝙸𝙽𝙸𝙲🥀 ¶™🌐
📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! 📱