😭😭ያስለቅሳል😭😭
ተነሽ እናቴ መንጋለልሽ ምነው
በያ መልሽልኝ ዝምታሽ ለምነው
ለማን አቤት ልበል ደራሼስ ማን ነው
ያለ እናት መቅረቴ ጥፋቴስ ምንድን ነው
ገና ልጅ ነኝ ህፃን ብላቴና
አየሁ እናቴ ተገጭታ መኪና
ህይወቴን ነጠከኝ ቀኔን አጨልመህ
ደስታዬን ነሳኸኝ እናቴን ገለህ
አላስቆምህም ካሳ አልጠይቅህም
የእናቴን ደም ዋጋ ክፈል አልልህም
ብቻ አዝኛለሁ ሃዘን ተሰምቶኛል
የሰው ልጅ ጭካኔ ክፋቱ ገርሞኛል
አልተጠነቀቅክም ዋጋ አልሰጠሃትም
እንስሳ በመሆኗ እንደ ሰው አላየሃትም
ምንም እንኳን ብናንስ ባስተሳሰባችን
የምንወደውን ስናጣ አይቀር ማዘናችን
እባካችሁ ሰዎች ሃዘኔ ይግባችሁ
ጥንቃቄ አድርጉ በየመንገዳችሁ
እንግዲህ ምን ልበል ከማዘን በስተቀር
ሰው ፈረደብኝ ለብቻዬ እንድኖር
በይ እንግዲህ እናቴ አፈሩ ይቅለልሽ
መቼም አረሳሽም # ባይተዋሯ__ልጅሽ
@yefikir_menorya
ተነሽ እናቴ መንጋለልሽ ምነው
በያ መልሽልኝ ዝምታሽ ለምነው
ለማን አቤት ልበል ደራሼስ ማን ነው
ያለ እናት መቅረቴ ጥፋቴስ ምንድን ነው
ገና ልጅ ነኝ ህፃን ብላቴና
አየሁ እናቴ ተገጭታ መኪና
ህይወቴን ነጠከኝ ቀኔን አጨልመህ
ደስታዬን ነሳኸኝ እናቴን ገለህ
አላስቆምህም ካሳ አልጠይቅህም
የእናቴን ደም ዋጋ ክፈል አልልህም
ብቻ አዝኛለሁ ሃዘን ተሰምቶኛል
የሰው ልጅ ጭካኔ ክፋቱ ገርሞኛል
አልተጠነቀቅክም ዋጋ አልሰጠሃትም
እንስሳ በመሆኗ እንደ ሰው አላየሃትም
ምንም እንኳን ብናንስ ባስተሳሰባችን
የምንወደውን ስናጣ አይቀር ማዘናችን
እባካችሁ ሰዎች ሃዘኔ ይግባችሁ
ጥንቃቄ አድርጉ በየመንገዳችሁ
እንግዲህ ምን ልበል ከማዘን በስተቀር
ሰው ፈረደብኝ ለብቻዬ እንድኖር
በይ እንግዲህ እናቴ አፈሩ ይቅለልሽ
መቼም አረሳሽም # ባይተዋሯ__ልጅሽ
@yefikir_menorya