ላንቺ ይሁንልኝ!!
ያኔ በርረሽ የትም መድረስ የምትችዪ የሚመስልሽ ልጅነትሽ ውስጥ ብዙ ህልም የነበረሽ ፣ ብለሽ አርቀሽ የሰቀልሻት አንቺ የነበረችሽ ፣ እደምቅበታለው ያልሽው መክሊት እና ችሎታ የነበረሽ ………
ከዛ ግን ዓመታት ነጉደው ስትነቂ ክንፍሽ የተሰበረ ዓይነት ስሜት ያለው ……..
~ አግብተሽ ወልደሽ ….. በልጆችሽ ፍቅር ውስጥ ጠፍተሽ …. ምናልባትም ባልበሰለ ውሳኔሽ የተሳሳተ አጋር መርጠሽ ያዘመመ ትዳር እየመራሽ …… የእለት ተዕለት ኑሮን ለማስኬድ እጅሽ የደረሰበትን ስራ እየሰራሽ በኑሮ ትግል ደብዝዘሽ ……. ህልምሽ ተዘንግቶሽ ….. ሳድግ የምሆናት ካልሻት አንቺ የልጆችሽን ማደግ አስቀድመሽ …. ከራስሽ ጋር የምታወሪበት ፋታ ስታገኚ
«በቃ?!! ህይወቴ ይሄ ነው በቃ?!! ህልሜ ፣ ምኞቴ ቅዠት ብቻ ነበር?!!» የምትይበት ዝቅታ ለሚሰማሽ
~ደግሞ ለቤተሰቦችሽ ወይም ለልጅሽ ቀን ላውጣላቸው ብለሽ ተሰደሽ በሰው ሀገር ስትለፊ ያንቺ ቀን ያለፈ ለሚመስልሽ ፣ በትከሻሽ ተሸክመሽ ባህር ያቋረጥሽውን ሀላፊነት ቀስ በቀስ ስትንጂ …. ወንድምሽ አግብቶ የራሱን ቤተሰብ መምራት ሲጀምር ፣ ለአባትሽ ቤት ከገዛሽ ኋላ ፣ እህትሽ ትምህርቷን ስትጨርስ ….. ለምትወጃቸው እያልሽ ዓመት ዓመትን ሲደርብ ….. ስትዪ እድሜሽም ሄዶ ፣ ድሮ ያስቀመጥሽውን አንስተሽ መቀጠል እንዳትችዪ ሆኖ ተቀያይሮ … ከዚህ በኋላ ገና ተምሬ? ከዚህ በኋላ ገና ፍቅር ፈልጌ? ከዚህ በኋላ ምንስ ብጀምር እስክጨርሰው የትዬለሌ …… ብለሽ ቀኑ የሰጠሽን ተቀብለሽ «በቃ! አሁንማ አበቃ!! ድሮ ነበር!» የምትይበትን ዝቅታ ለነካሽ
~ ደግሞ ላንቺ …. በአደባባይ የሚባልልሽ ስኬታማ ፣ በመንገድሽ ላገኘሽው ሁሉ ብርታት እና ንቃትን የምታጋቢ ፣ ለልጆችሽ፣ ለጓደኞችሽ ፣ ለቤተሰቦችሽ እና በዙሪያሽ ላሉ ሁሉ በሳቅሽ ቀናቸውን የምታፈኪ ፣ በአደባባይ የዋጥሽው እንባ ብቻሽን ስትሆኚ የሚገነፍልብሽ ፣ እቤትሽ የምታነክሽበት ጉድለትሽ እንስ አድርጎ የሚያኮማትርሽ ….. የምትይበትን ዝቅታ ለነካሽ
ታውቂዋለሽኮ የመጨረሻ የዝቅታ ወለል ላይ ስትሆኚ ያለሽ ምርጫ ሁለት ብቻ ነው!! ወይ ወደላይ (ወደከፍታ) መሄድ ወይ ደግሞ እዛው መቆየት ነው። ምክንያቱም ከመጨረሻው ወለል ወደየትም ዝቅ አትይማ!!
እዛው መቆየት ያንቺ ምርጫ አይሆንምኣ? የሚባልበት እድሜም ሁኔታም የለምኮ!! ረስተሽው ወይ እየደቆሰሽ ባለፈ አስቸጋሪ ቀን የተሟጠጠ መስሎሽ እንጂ እንኳን አንድ ያንቺን የሌላውን ደርበሽ አቀበቱን የምትወጪበት ጉልበትኮ ነው ያለሽ!! ለምን አንድ ዓመት አይሆንም የቀረሽ የእድሜ ዘመን? እየሞከርሽ ፣ እያለምሽ ፣ መራመድ ባትችዪ እየተንከብለልሽ ዘመንሽ ይለቅ!! ምክንያቱም ስኬትኮ የተራራው ጫፍ አይደለም!! ጉዞውም የስኬትሽ አካል ነው!! መፍጨርጨር እና እየወደቁ መነሳቱምኮ ወደ ህልምሽ መቅረቢያ መንገዱ ነው!! የህልምሽ አካል ነው!!
በቀንሽ መጨረሻ ምን ዓይነት ሴት ሆነሽ ማለፍ ነው የምትፈልጊው? ምን አይነት አሻራ ጥለሽ ነው ማለፍ የምትፈልጊው? ሁሉ ነገር ሲመቻች ብቻ አይደለም ያቺን ራስሽን የምትሰሪው ፤ አሁን ባለሽበት ዝቅታሽ ውስጥ ..... በኑሮ ውጣ ውረድ በደበዘዘ ነገሽ..... ምንም ተስፋ የሚሰጥ ጭላንጭል ብርሃን ባይታይሽም ራስሽን ስሪ ፣ ነገ የእኔ ቀን ሲመጣ የማጌጥበት ነው ብለሽ መክሊትሽን አዳብሪ!! አታስቀምጪው (አትደብቂው)!! እጅ አትስጪ እንጂ ያ ቀን ይመጣል!! አድካሚም ቢሆን ያ ያንቺ ቀን ይመጣል!!
እየተዘጋጀሽ ፣ እያደግሽ ፣ እየተለማመድሽ ካልቆየሽኮ ግን ያ ቀንሽ ቢመጣም አትደምቂበትም! ምክንያቱም ተስፋ ቆርጠሽ ቀን እስኪመጣ የጣልሽው ህልም ነው ያለሽ እንጂ የምትሰጪው ወይ የምታሳዪው ነገር አይኖርሽም!!
ደግሞ ከሁሉ በላይ የሰማዩ አምላክ አለ አይደል? ለእያንዳንዷ ለዘራሻት ፍቅር ፣ ለሞላሽው ጉድለት ፣ ላበስሽው እንባ ፣ ቀና ላደረግሽው አንገት …….. ይሄን ሁሉ ብድራትሽን ሊከፍልሽ ሳለ የምን እጅ መስጠት ነው? በይው!! አንድ ለመራመድ የዘረጋሽው እግርሽ አስር ተራምዶ ታገኚዋለሽ!! እመኚኝ አልፎ ወደኋላሽ ዞረሽ ስታዪው እንዳለፈ ውሃ ነው!! ደሞ በተረፈው እኔ እወድሽ የለ? ❤️❤️
ውብ ቀን ውብኛ አዋዋል ዋሉልኝ!!! ❤️❤️❤️
(ወንዶች ካነበባችሁት ምናልባት ሊያስፈልጋት ስለሚችል ለሚስትህ አንብብላት ወይም ስደት ላለች እህትህ!! ቺኮችዬም አንብባችሁት!! ኸረ እኔ የለሁበትም! ያላችሁ እንተላለፍ !! )