#ነብዩሏህ_ኢብራሂም_(ዐ,ሰ)
#ክፍል1⃣
#ኢብራሂም_ኢብን_ተሳርኽ/ኣዘር_ኢብን_ሳሩግ_ኢብን_ናዑር_ኢብን_ፋሊግ_ኢብን_ዓቢር_ኢብን_ሻሊህ_ኢብን_አርፈከሽዝ_ኢብን_ሳም_ኢብን_ኑህ እኚህ ነቢይ ናቸው የዛሬ እንግዳችን።
#ኢብራሂም #(ኡሉል-ዐዝም)ከተባሉት ከአምስቱ ከበርት ነቢያቶች አንዱ ናቸው።
1፦ኑህ (ዐ ሰ)
2፦ ኢብራሂም (ዐ ሰ)
3፦ ሙሳ(ዐ ሰ)
4፦ ዒሳ(ዐ ሰ)
5፦ ሙሀመድ የኔ ውድ (ሰ ዐ ወ)....እነዚህ ናቸው ኡሉል ዐዝም የሚባሉት።
ኢብራሂም ከጣኦት አምላኪያን ቤተሰቦች ነው የተወለዱት።አንዱ ድንጋይ
ጠርቦ ያመልካል፣ከፊሉ ፀሀይን እና ኮከብን ያመልካል፣ሌላው ደሞ ንጉሶችን
ያመልካል።
በዚህ የድንቁርና ዘመን ኢብራሂም ገና በልጅነታቸው ነበር የሰዉ ጅልነት
ሚያስገርማቸው።ከምንም በላይ እሚገርመው የኢብራሂም አባት ነበር
ለከተማይቱ ህዝብ የተለያዩ ጣኦታትን እየሰራ የሚሸጥላቸው።
በዚህም የተነሳ የነኢብራሂም ቤተሰብ እጅጉን የተከበሩ ነበሩ።
በዚህች ድንቁርና በተጠናወታት ባቢሎን በምትባል ከተማ ኢብራሂም
ከጣኦታት ሁሉ ታቅበው አደጉ።አሁን አሁን ኢብራሂም በጣም ማሰላሰል
ጀምረዋል።
ኢብራሂም ብቻውን ቁጭ ብሎ፦"እንዴት አባቴ ከእንጨት እና ከድንጋይ
እየጠረበ የሚሽጠውን ግኡዝ ነገር ሰዉ ያመልከዋል !!!
ሰዉ ጤና የለውም እንዴ !!!
አይ... ! አይ... ! ነገሩ እንኳን እንዲህ አይሆንም። በእርግጠኝነት ጌታ ማለት
ፍጥረታትን ይፈጥራል እንጂ ፍጥረታት እሱን አይፈጥሩትም።
እሺ እነዚህ አማልክት ምንም አይጠቅሙም አይጎዱም ካልኩ ታዲያ ፈጣሪ
የታለ !!! እራሱስ ማን ነው?" በማለት ያሰላስላል።
ከእለታት አንድ ቀን ኢብራሂም ዐ ሰ እንደተለምዶዋቸው ቢቻቸውን ቁጭ
ብለው ስለ ፈጣሪ ማንነት እና ምንነት እያሰላሰሉ ስለ ድንገት አይናቸው
ጨለማ ውስጥ በሚምዘገዘግ ኮከብ ላይ አረፈ።
ኢብራሂምም ድምፃቸውን ከፍ አድርገው፦"ይሄው ጌታዬን አገኘሁ። አዎ ጌታዬ
በሰው እጅ አይፈጠርም እንደ ጣኦታትም ወድቆ አይሰበርም" አሉ።
ባየውም ነገር በጣም ተደሰተ ከደስታው ብዛት ለዚያ ኮኮብ ሌሊቱን ሙሉ
ሲሰግድ አደረ።በዚያ ሌሊት ትክክለኛውን ጌታ እንዳገኘ ለህዝቡ ሁሉ
ተናገረ።ሌሊቱን ሲሰግድ ካነጋ በኋላ ድንግት ጠዋት ላይ ቀና ሲል ያ ጌታ
የመሰለው ኮከብ በብርሀን ተሸፈኖ ጠለቀ።
አሀ...አሁን ማታውን ሙሉ ሲሰግድ ያሳለፈው ለትክክለኛ ጌታ እንዳልሆነ
ተገነዘበ።ከዚያም፦"እኔ ጠላቂዎችን አልወድም" አለ።
ኢብራሂም አሁንም ግን ተስፋ አልቆረጠም።ጌታውን ፍለጋ ዳግም አጠናክሮ
ቀጥሏል።በሁለተኛውም ቀን ኢብራሂም በማታ ብቻውን ቁጭ ብሎ ስለ ጌታው
እያሰላሰለ ሳለ ወደ ላይ ቀና ሲል የሰማዩን ፅልመት በብርሀኑ የገፈፈ ውብ
ጨረቃ ተመለከተ።
አሁን ትንሽ ከመጀመርያው ረጋ አለ'ና፦"ትክክለኛ ጌታዬማ ይህ ነው እንዴት ግን
እስካሁን አላየሁትም!!!" ሲል ከራሱ አወራ።
የዛሬዋን ግን እንደትናንቱ እየሰገደ አላደረም ትንሽ ቆይቶ ተኛ።ጠዋት ላይ
ጌታዬን ልየው ብሎ ሲያንጋጥጥ ጨረቃው ተሰውሯል።
ኢብራሂምም እጅጉን አዘነ እዛው ባለበት ሆኖም፦"ጌታዬ ቀጥተኛውን መንገድ
እራሱ ካልመራኝ ከተሳሳቾች እሆናለሁ" አለ።
ተስፋ ቆርጦ በባይተዋርነት ውጭ ላይ ቁጭ ብሎ ሳለ ፀሀይን
ተመለከተ።በጣም ግዙፍ ናት፣ከጨረቃ እና ከኮከብ ስትነፃፀር በጣም ጎልታ
ታየችው።
ኢብራሂምም፦"ጌታዬን አገኘሁ ይህ ትክክለኛው ጌታዬ ነው በዛ ላይ ከሁሉም
ይገዝፋል"ብሎ ቀኑን በደስታ አሳለፈ።
በመጨረሻም ፀሀይ ወደ ጀምበሯ ስትቃረብ ዘውታሪ አለመሆኗን ተረዳ።ጌታ
ሁሌም ያልለ መሆኑን ተገነዘበ እንዲህም አለ፦"ወገኖቼ ሆይ!! እናንተ
ከምታጋሩት ነገር እኔ ነፃ ነኝ"
አሁን ኢብራሂም ሁሉ ነገር እየተገለፀለት መጥቷል..ጨረቃም፣ፀሀይም
፣ኮከብም አንድ አስተናባሪ ጌታ እንዳላቸው እና እነሱም ጌታ እንዳልሆኑ ተረዳ።ያ ጌታ ደሞ በአይን ሊታይ እንደማይችልም ተገንዝቦ በዛ የፍጥረተ አለሙ ጌታ
በሆነው አላህ አመነበት።
አሁን ኢብራሂም ከድንቁርና ወጥቷል...ቀጣይ እቅዱ ህዝቡን ከድንቁርናለማውጣት ቢሆንም ቅድሚያ ለአባቱ መስጠት እንዳለበት ተገንዝቧል።
አባቱ ዘንድም ሄደ'ና፦"አባቴ ሆይ! ለምንድነው እነዚህን የማይጠቅሙ
አማልክትን ጌታ አድርገህ የምትገዛው?
እስቲ አባቴ ተመልከት እነኚህ አማልክት... ምንም አያዩም አይሰሙም እንዴት
በነዚህ ታምናለህ።
አባቴ ሆይ!! ፈጣሪያችን አላህ ነው። ልናየው አይቻለንም እሱን ብቻ ነው
ልንገዛ የሚገባን።ይህም ብቻ ነው ቀጥተኛው መንገድ" በማለት አባቱን ጥሪ አደረገለት።
ያን ግዜ አባቱ ቁጣው ገነፈለ..."ይህ ብላቴና እንዴት እድሜ ልኬን
ካመለክኩት ጣኦት ተው ይለኛል" ብሎ በጣም ተናደደ።
ኢብራሂምም፦"አባቴ ! ላንተም ለወገኖችህም ሸይጣን ነው ይህንን መንገድ
አስውቦ ሚያሳያችሁ። በምትፈፅሙት ሺርክ ከዝወተራችሁ መመለሻችሁ ወደ
እሳት ይሆናል" እያለ በመለማመጥ ወደ አላህ ይጠራቸው ጀመር።
ከዚያም አባትየው በጣም በመቆጣት ካሁን በኋላ ግን
ሊመታው፣ሊገድለው፣በድንጋይም ሊወግረው እንደሚችል አስጠንቅቆ
ኢብራሂምን ከቤት አባረረው።
ኢብራሂም አባትየውን መምከር ምንም ጥቅም እንደሌለው በተረዳ
ግዜ፦"ሰላም ሆንልኝ።ጌታዬንም ላንተ ምህረት እንዲያደርግልህ እለምነዋለሁ
እርሱ ለኔ በጣም ርኅሩኅ ነው'ና" ብሎት ቤቱን ትቶ ተሰናበተው።
በቃ አሁን የዳዕዋው ጥሪ ከቤት ወጣ ለመላው ህዝብ ይሰራጭም
ጀመር።ኢብራሂምም ከአላህ ሌላ ምንም አምላክ እንደሌለ እና ሌላ
አማልክትም ምንም እንደማይፈይዱ በየሄደበት ማውራት ጀመረ።
ይህ የኢብራሂም ጉዳይ ቀስ በቀስ የከተማዋ ወሬ ሆነ።በዘመኑ ሀገሪቷን
ይመራ ለነበረው እና ከአማልክቱ አንዱ አካል ለሆነውም ኑምሩድ ይህ ወሬ
ደረሰው።
ኢብራሂምንም እንዲያቀርቡለት ወታደሮቹን አዘዘ።
ኢብራሂምም ከንጉሱ ፊት ቆመ። በሀገሪቱም ሆነ በመላ አለም የሚመለኩ
አማልክት ሁላ እንደማይጠቅሙ እና እንደማይጎዱ በድፍረት አስረዳው።አላህ
ህያው የሚያደርግ እና የሚገድል ጌታ መሆኑንም አክሎ ነገረው።
ንጉሱም፦"እኔ መግደልም ህያው ማድረግም እችላለሁ" አለው።
ኢብራሂምም፦"እንዴት?" አለው።
ያን ግዜ ንጉሱ ሁለት የሞት ፍርድ የተፈረደባቸውን እስረኞች እንዲቀርቡ
ካደረገ በኋላ አንዱን በመግደል አንዱን በመተው፦"ይኸው እገድላለሁም
ህያውም አደርጋለሁ" ብሎ ተመፃደቀበት።
ኢብራሂምም፦"አላህ ፀሀይን ከምስራቅ አስወጥቶ በምዕራብ
ያስገባታል።እስቲ አንተ ጌታ ከሆንክ ከ ምዕራብ እስወጣት"ሲለው ንጉሱም
በሀፍረት አንገት ደፋ።
ኑምሩድ ስለተባለው ንጉስ ወደፊት እናያለን ኢንሻ አላህ የኢብራሂምን ጥሪ
ለማሰናከል ሲሞክር አላህ እሱንም ወታደሮቹንም በትንኝ አጠፋቸው።
ከእለታት አንድ ቀን የሀገሪቱ ህዝብ ለአመታዊ በአል በጠዋት ወደ መሰብሰቢያ
ቦታ መትመም ጀመሩ።
ኢብራሂምም በዚህ አጋጣሚ አንድ ምርጥ ሀሳብ መጣላቸው'ና ለመፈፀምም
ወሰኑ።
ከዚያም ህዝቡ ሙሉ ለሙሉ መሰብሰቢያው ቦታ ሲሆድ እሱን ለምን
እንደማይሄድ ሲጠይቁት፦"አሞኛል" ይል ነበር።
በመጨረሸም ሰዉ ሁሉ ከተማይቷን ለቅቆ ወደመሰብሰቢያው ሄደ'ና
ኢብራሂም ብቻውን በከተማይቱ ቀረ።
አሁን ልበ ሙሉው ኢብራሂም ሀሳቡን ሊያሳካ ጉዞ ወደ ቤተ አምልኮ
ጀምሯል...ልክ ጣኦታቱ ያሉበትን በር ሲከፍተው ቤተ አምልኮው ከተለያዩ
እንጨቶች እና ድንጋዮች በተሰሩ ጣኦታት ተሞልቷል።
ኢብራሂም ምንም አልፈራም ዘልቆ ወደ ውስጥ ገባ።ከዚያም በጣኦታቱ
አጠገብ በቁርባን መልኩ የተደረደረውን የምግብ መዐት ተመለከተ'ና
ጠኦቶቹን፦"አትበሉም እንዴ!!!" አላቸው እየፎገረ...
አሁንም በመሀከላቸው ትንሽ ተዟዟረና፦"ምንድነ......