👉 ወላጅን ማመፅ
አላህ በተለያዩ የቁርኣን አንቀፆች ከራሱ ሐቅ በማስከተል የወላጅን ሐቅ በሁለተኛ ደረጃ ያስቀምጣል የአላህ መልእክተኛ - ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም - ከወንጀሎች ሁሉ ዋነኛው በአላህ ላይ ማጋራት መሆኑን ከተናገሩ በኀላ ወላጅን ማመፅ በሁለተኛ ደረጃ አስቀምጠውታል
አንድ ልጅ ወላጆቹን ለማመፅ ምንም ምክንያት አይኖረውም
ነገር ግን ብዙ ልጆች በተለያየ ምክንያት ወላጆቻቸውን በተለይም አባቶቻቸውን ሲያምፁ እናያለን
ከእነዚህ ምክንያቶች አንዱ አባትየው ሁለተኛ ሚስት ማግባቱ ነው
ይህ ምክንያት እነርሱ አባቶቻቸውን ለማመፅ እንደ በቂ ምክንያት ይቆጥሩታል እናታችንን በድሏል በሚል
ይህ ፍፁም ስህተት ነው በዚህ ምክንያት አባትን ማመፅ ከባድ ወንጀል ነው
አላህ ወላጆችን አስመልክቶ በእሱ ላይ እያጋሩ ልጃቸውንም በሱ ላይ እንዲያጋራ ቢታገሉት እንኳን ማጋራቱን እሺ አትበላቸው በዱንያ ጉዳይ ላይ በመልካም ተኗኗራቸው ነው ያለው ይህ የአላህ ቃል በሱረቱል ሉቅማን 15ኛው አንቀስ ላይ እንዲህ ሲል እናገኘዋለን
" وإن جاهداك على أن تشرك بي ما ليس لك به علم فلا تطعهما وصاحبهما في الدنيا معروفا ..... " الآية
سورة لقمان ( 15 )
" ለአንተ በእርሱ ዕውቀት የሌለህን ነገር በእኔ እንድታጋራ ቢታገሉህም አትታዘዛቸው :: በቅርቢቱ ዓለም በመልካም ስራ ተወዳጃቸው :: "
ተመልከት እነዚህ ወላጆች አጋሪዎች ካፊሮች ናቸው
ይህ ሳይበቃቸው ልጃቸው በአላህ አምኖ እሱን ሲገዛ አይቻልም ብለው እንዲከፍር እንዲያሻርክ በማንኛውም መልኩ ቢታገሉት እንኳን በማሻረኩ አትታዘዛቸው ነገር ግን በዱንያ ጉዳይ እንቢ እንዳትላቸው የወላጅነት ሐቁ አለ ጠብቅ በመልካም ተወዳጃቸው ነው የሚለው
አንድ አባት ሁለት ሚስት ወይም ከዛ በላይ እስከ አራት ማግባትን አላህ ነው የፈቀደለት
እናት ( የመጀመሪያዋ ) በአባት ላይ ልጆች ታሳምፃለች የተበደለች አስመስላ ይህ በጣም ከባድ ወንጀል ነው
እሷ በአብዛኛው በደል የምትለው ሁለተኛ ማግባቱን ነው ይህ በሸሪዓው መስፈርት ከሆነ በደል ሳይሆን ዒባዳ ነው
ልጅ አባቱ እናቱን ቢበድላት እንኳን
በጣም በመልካም ፀባይ እንዳይበድል ማድረግ መምከር ማስተካከል እናትየውም አላህን እንድትፈራ የአላህንም የባልዋንም ሐቅ እንድትጠበቅ ማድረግ በመካከላቸው ፍቅር እንዲኖር ማገዝ እንጂ አባትን ማስፈራራት አልፎም ማመፅ አልታዘዝም ማለት በጣም ከባድ ወንጀል ነው ፈፅሞ የሚታሰብ አይደለም በመሆኑም ልጅ ወላጆቹን ለማመፅ ምንም ምክንያት የለውም አባትም ልጁ በእናቱ ላይ እንዲያምፅ ማድረግ የለበትም እናትም እንደዛው
በመልካም ነገር መተባበር ወደ መልካም ማምጣት እንጂ ወደ ወንጀል እንዲሄድ ማድረግ ራሱ ወንጀል ነው
ስለዚህ ወላጅን ማመፅ የሁለት ሀገር ስኬት ያጠፋል መጠንቀቅ ይገባል።
@Yenebiyattaric