"የጉንዳኖች ፍልስፍና"
ጉንዳኖች ሲጓዙ መንገድ ብትዘጋባቸው ከጉዟቸው አይገቱም፤ሌላ መንገድ ፈልገው ጉዟቸውን ይቀጥላሉ፡፡ ከተስፋ መቁረጥ ጋር ፈጽሞ አይተዋወቁም፡፡
ጉንዳኖች ለመጪው ጊዜ ይዘጋጃሉ፡፡ በበጋ ወቅት ለክረምት ጊዜ የሚሆናቸውን ቀለብ ያከማቻሉ፡፡ በዝናብ ወቅት ወደ ውጭ ሳይወጡ ክረምቱን ለማሳለፍ የቻሉትን ያህል ዝግጅት ያደርጋሉ፡፡ በክረምት ወቅት ነገ በጋ እንደሚመጣ ወይም ብራ እንደሚሆን እርግጠኞች ናቸው፡፡ ክረምቱ ለረዥም ጊዜ እንደማይዘልቅ ያውቃሉ፡፡ በጋውን በብሩህ ተስፋ ይጠብቃሉ፡፡ ጸሃይዋ ብጭ ስትልም ተግተልትለው ይወጣሉ፡፡
ጉንዳኖች ከአካላቸው ክብደት 20 እጥፍ የሚልቅ ነገር መሸከም ይችላሉ፡፡ ፈጣንም ናቸው፡፡ ሁልጊዜ በሥራ ተጠምደው ነው የሚታዩት፤ ምንጊዜም በእንቅስቃሴ ላይ ናቸው፡፡ መሰራት ያለበትን ሁሉ በትጋት ይሰራሉ፡፡ ለዛሬ ብቻ ሳይሆን ለነጋቸውም ያስባሉ - መኖሪያቸውን ይገነባሉ፤ቀለባቸውን ይሰንቃሉ፡፡
የሰው ልጅ ታዲያ ከጉንዳኖች ህይወት ምን ይማራል?
በአሜሪካ የሞቲቬሽናል አባት የሚባለው ጂም ሮን፣ ከጉንዳኖች ለህይወት ስኬት የሚጠቅሙ አራት መመሪያዎችን መቅሰም እንችላለን፤ ይላል፡፡ "የጉንዳኖች ፍልስፍና" ሲልም ሰይሞታል፡፡ አራቱ የስኬት መመሪያዎች የሚከተሉት ናቸው፡-
• ምንጊዜም ተስፋ አትቁረጡ
• ሁልጊዜም ለነገ ወይም ለወደፊቱ አስቡ
• አዎንታዊ ብሩህ ተስፋ ይኑራችሁ
• የምትችሉትን ሁሉ አድርጉ