Posts filter


ልዩነታችን ስጦታ ነው። በኩራት እንላበሰው።

#ራስንመቀበል #ራስንመውደድ #ውስጣዊሰላም #እርሶበቂነዎት


We are proud of all of your strength, courage and perseverance.
#ካለፈውእንማር #እራሳችንንእናብቃ #እንተባበር


Let's learn from the past: let's empower ourselves: let's help each other.
Equality, Freedom and Justice for all!


ሰላም ሰላም
እንዴት ከረማችሁ? የኵራት ወርን እንዴት እያሳለፋችሁ ነዉ? ለጨዋታ ይችን ላካፍላሽሁ፡፡


Reflect on the past, empower yourself with knowledge to ignite change and unite against the forces that do not want us to exist. Unity at this time is critical to our survival.

#bebold #beyou #pride #pride2024 #yezeginetkibir #yzk #empower #reflect #unite #zega #yezegakurat #pridemonth#pride #pridemonth #lgbtq #qtbipoc #queercommunity


መልካም የኩራት ወር!

#ካለፈውእንማር #እራሳችንንእናብቃ #እንተባበር
#bebold #beyou #pride #pride2024 #yezeginetkibir #yzk #empower #reflect #unite #zega #yezegakurat #pridemonth


መልካም የፓንሴክሹአል/ፓኖሮማንቲክ እይታ ቀን! 💖💛💙 ⚧ ♀ ♂

አንድ አንድ እውነታዎች ስለ ፓንሴክሹአል እና ፓንሮማንቲክ ሰዎች

•ፓንሴክሹአል ማለት ፆታዊ ማንነትን መሰረት ያላደረገ (ፆታቸው ምንም ይሁን ምን) ለሰው የሚኖር ተማርኮ/ፍቅር ማለት እንጂ ለሁሉም ሰው መማረክ ማለት አይደለም።

• ፓንሴክሹአል ሰዎች ስለማንነታቸው ግራ የተጋቡ ሰዎች አይደሉም፤ ይልቁንስ እነዚህ ሰዎች ከባሕላዊ ፆታዊ ክፍፍል ባሻገር የመማረክ አቅም (ችሎታ) አላቸው ።

• ፓንሴክሹአልና ፓንሮማንቲክ “ጊዜያዊ ማንነቶች” ሳይሆኑ ተቀባይነት ያላቸውና ለየት ያሉ የተማርኮ መለያዎች ናቸው።

#ፓንሴክሹአልእይታቀን #ፓኖሮማንቲክእይታቀን #ፓኖሮማንቲክኩራት #ፓንሴክሹአልኩራት #የዜግነትክብር

#PanVisibilityDay #loveislove #yezeginetkibir #pansexualpride #panromanticpride


እንቅስቃሴ ማድረግ የአይምሮ ጤናችንን ለመጠበቅ ወሳኝ ነው። በዚህም የአይምሮ ጤና ግንዛቤ መፍጠሪያ ሳምንት፣ ሁላችንም ከእለት ተእለት ኑሮአችን ላይ ለእንቅስቃሴ የሚሆን ጊዜ እንመድብ!፡

Join our telegram channel for more information and discussion. https://t.me/yezeginetkibir

#MentalHealthAwarenessWeek #MHAW #momentsformovement #mindmatters #lgbt+ #mindforward


በመገለል፣ በክፍፍል፣ በውንጀላ እና በአመጽ ምክንያት ብዙ ተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ ሰዎች በመሠረታዊ መብቶቻቸው ላይ ፈተናዎችን ይገጥማሉ። በዚህ ትግል፣ እኛ አንድነታችንን እናጠናክር። ልዩነታችንን ለመቦዝብዝ ከሚተጉ አካሎች በላይ የጋራ ትብብር ፣ለሁሉም ለውጥ ማምጣት ይችላልና።

በጋራ ጉዞኣችን፣ የእያንዳንዳችን ድምፅ የጋራ ታሪካችንን ያበለፅጋል። ወደፊት ለመጓዝ የምናደርገው እያንዳንዱ እንቅስቃሴ፣ ያለ ምንም ጥርጥር የምንጓጓለትን ኢትዮጵያ እንድናይ ያደርገናል፡፡ በተቀናጀ መልኩ በመተባበር፣ በመከባበር እና በመደማምጥ፣ ትግላችችን እንቀጥል።

ዛሬ እና ሁልጊዜ፣ ከፊታችን ለምንጠብቀው ነጻነት፣ እኩልነት እና ፍትህ እንድናይ እንበርታ!

ለበለጠ መረጃ እና ውይይት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡፡ https://t.me/yezeginetkibir
Please join our Telegram channel for more content and discussion.
#IDAHOBIT2024 🏳️‍🌈🏳️‍⚧️


እንቅስቃሴ ማድረግ የአይምሮ ጤናችንን ለመጠበቅ ወሳኝ ነው። በዚህም የአይምሮ ጤና ግንዛቤ መፍጠሪያ ሳምንት፣ ሁላችንም ከእለት ተእለት ኑሮአቸዉ ላይ ለእንቅስቃሴ የሚሆን ጊዜ እንድናመቻች እናበረታታለን፡፡

#MentalHealthAwarenessWeek #MHAW #momentsformovement #mindmatters #lgbt+ #mindforward


የአእምሮ ጤናችንን በቅርብ እንድንከታተል የሚረዱን ጥያቄዎች ወይም መመዘኛዎች ልናጋራቹህ ወደድን፡፡ እነዚህን ጥያቄዎች መመለስ እና ማሰላሰል የግል ጤናችንን እንድንከባከብ የሚረዱ ማሳሰቢያዎች ሊሆኑ ይችላሉ።
****
Valuable mental health checklists that can help us prioritize self-care and well-being. It's essential to take care of our mental health, and these checklists can serve as gentle reminders to nurture ourselves. #MomentsForMovement #MindMatters #SelfCareChecklists #WellBeing #SupportEachOther


ድብርት ወይ ጭንቀት ሲሰማህ ምን ታረጋለህ?
እኔ ወክ ማድረግ እወዳለሁ፡፡እግሮቼ መራመድ ሲጀምሩ ጭንቀቱ ቀስ እያለ ሲለቀኝ ይታወቀኛል፡፡ጭንቀቱ የመጣው ከመሸ ከሆነ ደሞ ጠዋት ተነስቼ እሮጣለሁ፡፡ስሮጥ እስኪደክመኝና እስኪያልበኝ ነው፡፡ከላቡ ጋ ሲታገለኝ ያደረው ጭንቀት ይለቀኛል፡፡የደበረው ሰሞን ጂም የሚያበዛ ጓደኛም አለኝ፡፡አእምሮው የሚጭንበትን ጭንቀት ሰውነቱ በስፖርት ይቋቋመዋል፡፡
አንተስ ሲደብርህ ወይ ጭንቀት ሲይዝህ አካላዊ እንቅስቃሴ የማድረግ ልምድ አለህ? እስኪ ልምድህን አካፍለን? ##MentalHealthAwarenessWeek #የአእምሮጤናግንዛቤማስጨበጫሳምንት


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
" ለኔው እንጂ ለሌላ አይደል እንዲህ ነኝ የምለው
በእኔነት ውስጥ ራሴን ችዬ ራሴን አውቄአለሁ
በማያውቀው ባልዋለበት ራሱን ያገኘ
ቀድሞ አልፃፈም እንዲነበብ እሱን ያሰኘ
እኔ እንዲህ ነኝ ማለት ለኔ ሊያኮራኝ እንጂ
ልሸማቀቅ ላፍር አልያም ልደት እንጂ"

ስለዚህ....
#pridemonth2022 #ዜጋ #ክብር #ፍቅር #የራስፍቅር #ኢትዮጵያዊዜጋ


Video is unavailable for watching
Show in Telegram


ቤተሰብ የደም ትስስር ብቻ አይደለም :: በህይወታችን ዉስጥ ያሉ በህይወታቸው ውስጥ እንድንኖር የሚፈልጉ ሰዎች ሰብሰብ ነዉ፤ በማንነታችን እንዳለን የሚቀበሉን ፣ ደስታችንን ለማየት ምንም ነገር ከማድረግ ወደኋላ የማይሉ እና ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የሚወዱን ናቸው::

Family isn't always blood. It's the people in your life who wants you in theirs; the ones who accept you for who you are; the ones who would do anything to see you smile and who love you no matter what.

#pridemonth2021 🌈
#chosenfamily #familybychoice #family #queerfamily #ethiopianqueer #zega #zegafamily #EthiopianLGBTIQ
#love


#3 ፍቅር/Love
ፍቅር ባለበት ህይወት አለ!
Where there is love, there is Life!

~Ghandi / ጋንዲ

#love #reasontobeproud #pridemonth2021 #pride #lgbtiq #lgbt #queer #EthiopianQueer #EthiopianLGBTIQ #Life #QueerHabesha


#2
ዕድለኝነት ይሰማኛል - የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሬ (ዜጋ) በመሆኔ፡፡

በዕድገቴ… “ልዩ” ጾታዊ ተማርኮዬን በአካባቢዬ ከማየው እና ከተማርሁት ማንነት ጋር ለማስማማት እና ለማስታረቅ ያደረግሁት የራስ ፍለጋ ዘመቻ ከተማርኮዬ እና ከአስቸጋሪ እድገት በዘለለ ራሴን እንደ ሰው እንድመዝን እና እንድመረምር ስላገዘኝ፤

ይህ አስቸጋሪ የራስ ሽኩቻ ጊዜ የተሻለ በነፃነት የማሰብ ዕድልን የሰጠኝ ሲሆን ስለህይወት ያለኝን ጠቅላላ አስተያየትም ለበጎ ቀይሮልኛል ብዬ አምናለሁ፡፡

Growing up to now, my self-discovery journey to reconcile my sexuality with what I saw and learned in my environment helped me evaluate and examine myself as a person beyond my sexuality.

I believe that these difficult times of conflict and self-discovery have given me a better chance to think freely and be open minded about life in general.

I am proud i get to learn new opportunities in life disguised as problems.

#pridemonth #pridemonth2021 #proudqueer #Zega #Ethiopian #Ethiopianqueer


ዜግነቴ ኩራቴ #1
ፅናት

ብዙ ጊዜ ስለመጣንበት መንገድ ፣ ስላሳለፍነው ህይወት እንዲሁም በዑደታችን ስላጋጠሙን መሠናክሎች መለስ ብለን ስናስታውስ ቀድሞ ትውስታችንን የሚሞላው ምን ያህል ከባድ እና አስቸጋሪ እንደነበረ ነው፡፡ ነገር ግን ያንን ሁሉ አልፈነው እዚህ የደረስንበትን ጥንካሬአችንን እና ፅናታችንንም አብረን ማስታወስ አለብን፡፡

ከየአቅጣጫው ከህይወት የሚወረወርብንን ጦር በሙሉ አውቀንም ይሁን ሳናውቅ ፣ በብርታትም ውስጥ ይሁን በስንፍና ፣ በራሳችንም ይሁን በሌሎች ርዳታ መክተንም ይሁን አምልጠን ዛሬ ላይ ደርሰናል፡፡

አያኮራም?

የነገውንም መሰናክላችንን እናልፍ ዘንድ የእስከዛሬውን ፅናታችንን መለስ ብለን እያየን ለነገ እንበርታ!

ዜግነቴ ኩራቴ!
የዜግነት ክብር




እናንተዬ …. ኧረ እንዴት ከረማችሁ?
በኹሉ ነገር መሐል እንኳን የደህንነት ምኞት እንካችሁ!!!

መፅሔታችን 2ኛ ዕትም ደረሰች እኮ!

በመጀመሪያ ዕትማችን በሰጣችሁኝ ገንቢ እና አበረታች እንዲሁም ገሳጭ አስተያየቶች እንዴት እንደኮራሁ እና እንደተደሰትኩ ብታውቁ! …. ደስስስ ነው ያስባላችሁኝ፡፡ ይኸው ሁለተኛዋንም ለናንተ ለማድረስ ተፍ ተፍ እያልኩ ነው፡፡

የተለያዩ ጉዳዮችን ትዳስሳለች! ለዜጋው ይጠቅማል ፣ ያዝናናል ፣ ያስተምራል ፣ አዲስ ነገር ያስጨብጣል ፣ ያስተዋውቃል ፣ ይሞግታል ፣ ያስቃል ፣ ያስለቅሳል ……. ያልነውን ሁ….ሉ በሚመጥነን መልኩ በዓይነት በዓይነቱ እያሰነዳዳን ነውና …. እናንተም ይኼ ይጨመር ፣ ይኼ ሀሳብ ይነሳ … የምትሉትን በፌስቡክም ሆነ በቴሌግራም ወይም በኢሜይል ላኩልኝ!

ታሪካችንን እንከትብ ፣ ለቀጣይ ትውልድ መሠረት እናስቀምጥ ፣ በዕውቀት የዜግነታችንን ክብር እንጎናፀፋለን!!!

#የዜግነትክብር #መፅሔት #ሁለተኛእትም

20 last posts shown.

218

subscribers
Channel statistics