✞ ገብርኤል መልዐከ ራማ ✞
ገብርኤል/፪/ መልዐከ ራማ /፪/
ስንጠራህ ፈጥነህ ድረስ ድምጽህን እንስማ
ትንቢቱ ሲፈጸም ዘመኑ ሲያበቃ
ከቀናት ሳትዘገይ ሳትጎድል ደቂቃ
ወደ ድንግል መጥተህ ደስታን አበሰርክ
የአምላክን ሠው መሆን ለዓለሙ ሰበክ /፪/
አዝ=====
ከውሃና ከእሳት ከሞት አመለጡ
በእሳቱ መካከል ለጥፋት ቢሰጡ
አንተ ባለህበት በየትኛውም ስፍራ
ምንም ቦታ የለው ሞትና መከራ /፪/
አዝ=====
የመንገዴ መሪ ፈውስ ነህ ለህመሜ
ገብርኤል ስትመጣ በዛልኝ ሰላሜ
ደስታን አብሳሪ ተሸክመህ ዜና
ዛሬም ለሀገራችን ምስራች ይዘህ ና /፪/
አዝ=====
አንጌቤናይቱ ቅድስት ኢየሉጣ
ስላንተ ትመስክር እስከ ልጇ ትምጣ
እሳት ነህ ገብርኤል ነበልባል አስወጋጅ
የአምላክን መወለድ ለዓለም የምታውጅ/፪/
| በዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ
ገብርኤል/፪/ መልዐከ ራማ /፪/
ስንጠራህ ፈጥነህ ድረስ ድምጽህን እንስማ
ትንቢቱ ሲፈጸም ዘመኑ ሲያበቃ
ከቀናት ሳትዘገይ ሳትጎድል ደቂቃ
ወደ ድንግል መጥተህ ደስታን አበሰርክ
የአምላክን ሠው መሆን ለዓለሙ ሰበክ /፪/
አዝ=====
ከውሃና ከእሳት ከሞት አመለጡ
በእሳቱ መካከል ለጥፋት ቢሰጡ
አንተ ባለህበት በየትኛውም ስፍራ
ምንም ቦታ የለው ሞትና መከራ /፪/
አዝ=====
የመንገዴ መሪ ፈውስ ነህ ለህመሜ
ገብርኤል ስትመጣ በዛልኝ ሰላሜ
ደስታን አብሳሪ ተሸክመህ ዜና
ዛሬም ለሀገራችን ምስራች ይዘህ ና /፪/
አዝ=====
አንጌቤናይቱ ቅድስት ኢየሉጣ
ስላንተ ትመስክር እስከ ልጇ ትምጣ
እሳት ነህ ገብርኤል ነበልባል አስወጋጅ
የአምላክን መወለድ ለዓለም የምታውጅ/፪/
| በዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ