♡ መስቀል ላይ ያየሁት ፍቅር ♡
መስቀል ላይ ያየሁት ፍቅር (፪)
ይቀሰቅሰኛል ለስሙ እንድዘምር (፪)
ፊቱን እያጣፉት እየተንገላታ
በጦር እየወጉት ይሰጣል ይቅርታ
እነርሱ እየጠሉት እርሱ ይወዳቸዋል
አስረው ሲጎትቱት ይከተላቸዋል
ፃድቁን ኃጥዕ ነው እውነቱን ሐሰት
እያሉ ሲጮሁ ይሰቀል ይሙት
እየመረመረው ፍጡር ፈጣሪን
ክርስቶስን አስሮ ፈታው በርባንን
ጀርባውን ሲገርፉት በሚያቃጥል ጅራፍ
በምህረት ያዛቸው በይቅርታው እቅፍ
ጨክነው ሲያጠጡት መራራ ሐሞት
ደም ውሃ ፈሰሰ ጎኑን ሲወጉት
ግምጃን አለበሱት ቀሚሱን ገፈው
በራሱም አኖሩ እሾህ ጎንጉነው
የአይሁድ ንጉስ ሆይ እያሉ ዘበቱ
ለህይወት ሆናቸው የኢየሱስ ሞቱ
መዝሙር
ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@maedot_ze_orthodox
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
መስቀል ላይ ያየሁት ፍቅር (፪)
ይቀሰቅሰኛል ለስሙ እንድዘምር (፪)
ፊቱን እያጣፉት እየተንገላታ
በጦር እየወጉት ይሰጣል ይቅርታ
እነርሱ እየጠሉት እርሱ ይወዳቸዋል
አስረው ሲጎትቱት ይከተላቸዋል
ፃድቁን ኃጥዕ ነው እውነቱን ሐሰት
እያሉ ሲጮሁ ይሰቀል ይሙት
እየመረመረው ፍጡር ፈጣሪን
ክርስቶስን አስሮ ፈታው በርባንን
ጀርባውን ሲገርፉት በሚያቃጥል ጅራፍ
በምህረት ያዛቸው በይቅርታው እቅፍ
ጨክነው ሲያጠጡት መራራ ሐሞት
ደም ውሃ ፈሰሰ ጎኑን ሲወጉት
ግምጃን አለበሱት ቀሚሱን ገፈው
በራሱም አኖሩ እሾህ ጎንጉነው
የአይሁድ ንጉስ ሆይ እያሉ ዘበቱ
ለህይወት ሆናቸው የኢየሱስ ሞቱ
መዝሙር
ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@maedot_ze_orthodox
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈