ይችላል ሚካኤል
የቀደመው እባብ ከላይ የተጣለው
በዚህ በምድር ላይ ኃይል ስልጣን ካለው
የእግዚአብሔር መላእክማ
ቅዱስ ሚካኤልማ
አለልን በፊቱ አለልን በግርማ
አዝ_
ዓለምን ከያዛት ከላይ የወደቀው
ወጥመድ እየሰራ ምድሩን ካስጨነቀው
ድል ያደረጉትማ ሰፍረዋል ፊታችን
የማይደፈር ነው የእሳት ነው ቅጥራችን
የእግዚአብሔር መላእክማ
ቅዱስ ሚካኤልማ
አለልን በክብር አለልን በግርማ
አዝ_
ሊውጥን ከዞረን የወደቀው ዘንዶ
ሊያድነን ይሰፍራል ሚካኤልም ወርዶ
ወጥመድ ሊያደርግብን ዳቢሎስ ከቻለ
የሚሰብረው መልዕክ በዙሪያችን አለ
የእግዚአብሔር መልዕክማ
ቅዱስ ሚካኤልማ
አለልን በክብር በግርማ
አዝ_
በሰማይ ተዋግቶ ድል የተደረገ
ሰይፍና መከራን ችሎ ካደረገ
ይችላል ሚካኤል ከእሳቱ ሊነጥቀን
የሚነካን የለም የንጉስ ልጆች ነን
የእግዚአብሔር መልዕክማ
ቅዱስ ሚካኤልማ
አለልን በክብር አለልን በግርማ
አዝ_
ከእግዚአብሔር ሊለየን ሰይጣን ከደከመ
በሀሰት ሊከሰን በፊቱ ከቆመ
ብርሃናዊ መልዕክ ሚካኤል ይደርሳል
በምልጃ በኃይሉ ክሱን ይሰርዛል
የእግዚአብሔር መልዕክማ
ቅዱስ ሚካኤልማ
አለልን በክብር አለልን በግርማ
ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
የቀደመው እባብ ከላይ የተጣለው
በዚህ በምድር ላይ ኃይል ስልጣን ካለው
የእግዚአብሔር መላእክማ
ቅዱስ ሚካኤልማ
አለልን በፊቱ አለልን በግርማ
አዝ_
ዓለምን ከያዛት ከላይ የወደቀው
ወጥመድ እየሰራ ምድሩን ካስጨነቀው
ድል ያደረጉትማ ሰፍረዋል ፊታችን
የማይደፈር ነው የእሳት ነው ቅጥራችን
የእግዚአብሔር መላእክማ
ቅዱስ ሚካኤልማ
አለልን በክብር አለልን በግርማ
አዝ_
ሊውጥን ከዞረን የወደቀው ዘንዶ
ሊያድነን ይሰፍራል ሚካኤልም ወርዶ
ወጥመድ ሊያደርግብን ዳቢሎስ ከቻለ
የሚሰብረው መልዕክ በዙሪያችን አለ
የእግዚአብሔር መልዕክማ
ቅዱስ ሚካኤልማ
አለልን በክብር በግርማ
አዝ_
በሰማይ ተዋግቶ ድል የተደረገ
ሰይፍና መከራን ችሎ ካደረገ
ይችላል ሚካኤል ከእሳቱ ሊነጥቀን
የሚነካን የለም የንጉስ ልጆች ነን
የእግዚአብሔር መልዕክማ
ቅዱስ ሚካኤልማ
አለልን በክብር አለልን በግርማ
አዝ_
ከእግዚአብሔር ሊለየን ሰይጣን ከደከመ
በሀሰት ሊከሰን በፊቱ ከቆመ
ብርሃናዊ መልዕክ ሚካኤል ይደርሳል
በምልጃ በኃይሉ ክሱን ይሰርዛል
የእግዚአብሔር መልዕክማ
ቅዱስ ሚካኤልማ
አለልን በክብር አለልን በግርማ
ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ