መገናኛ ድንኳን


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


"በአንዳንዶች ዘንድ ልማድ እንደሆነው መሰብሰባችንን አንተው" ስለዚህ ይህ ቻናል በአካል ብንራራቅም በመንፈስ የሚንሰበሰብበት ይሁን!
በቻናላችን👇
🎶አዳዲስና ቆየት ያሉ መዝሙሮችን

📖 ስነ-ፅሁፎችንና መጣጥፎችን ሌሎችን በአንድ ቋት መገናኛ ድንኳን ቻናል ላይ ያገኛሉ!

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


እንኳን ለ33ኛው ዓመት የዋራ ቤቴል አለም አቀፍ ጉባኤ በሰላም አደረሳችሁ!

በኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን የዲጂታል ሚዲያ አገልግሎት መቋቋሙ ይታወሳል። የሚዲያ አገልግሎት ክፍሉ ስራውን በይፋ የጀመረ ሲሆን፣ ቤተክርስቲያንን በሚመጥን ደረጃ ዝግጅቱን ለማቅረብ እንቅስቃሴ መጀመሩን ሲያበስር በታላቅ ደስታ ነው።

አገልግሎቱም እንደ መነሻ “አሜን-የኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን መልቲ ሚዲያ አገልግሎት” የተሰኘ የቴሌግራም ቻናል የከፈተ ሲሆን በቅርቡ ለታሰቡት የማህበራዊና ዲጂታል ሚዲያ አማራጮች እንደ መደላድል የምንጠቀምበት አማራጭ ይሆናል። ከዚህም በተጨማሪ ከክፍሉ የሚተላለፉ የጅማሬ ማስታወቂያዎችና ዝግጅቶች ወደ ቅዱሳን የሚደርሱበት መንገድ ይሆናል።

ቻናሉን አሁኑኑ ለመቀላቀል ይህንን ሊንክ ይጠቀሙ!👇🏽

https://t.me/AmenApostolicMedia

የዲጂታል ሚዲያ አገልግሎት ክፍል


#ለመገናኛ-ድንኳን የቴሌግራም ቻናል ቤተሰቦች በሙሉ!

✅ሰላም🙏 የተወደዳችሁ ወንድሞችና እህቶች እንደምን ቆያችሁ?

✅ሰሞኑን በቤተክርስቲያናችን በኩል ስለ ማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም መመሪያ መተላለፉ ይታወቃል በመሆኑም ይህ የቴሌግራም ቻናልም(መገናኛ-ድንኳን) የተላለፈዉን መመሪያ በመቀበል ለቤተክርስቲያን ድምጽ መታዘዝን መርጠናል!!

✅ በዚህ የቴሌግራም ቻናል(መገናኛ-ድንኳን) ከCOVID-19 ጊዜ ጀምሮ (ከ2012 ዓ.ም አጋማሽ)  እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ማለትም ቤተ-ክርስቲያናችን ማሳሰቢያ እስከሰጠችበት ቀን ድረስ ወደ እናንተ የተለያዩ መንፈሳዊ ነገሮችን በተለይም፦
🎧መዝሙሮችንና አልፎ አልፎም
🎤መልዕክቶችን እንድሁም
✍️ስነ-ጽሁፎችን  ወደ እናንተ ስናቀርብ እንደ ነበር ይታወቃል።
ይሁን እንጂ በዚህ አመት በቤተ-ክርስቲያን በኩል አንዳንድ ማሳሰቢያዎችን ስንሰማ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ አቁመናል። አሁንም የቤተክርስቲያንን ድምጽ መስማት ለእናንተም ለእኛም አስፈላጊ ሆኖ ስላገኘነን ያንንም አስከፊውን ጊዜ(COVID-19ን) እግዚአብሔር በምህረቱ ስላሳለፈንንና አሁን እንደልባችን በየአጥቢያችን መሰብሰብ ስለምንችል በተጨማሪም በተለያዩ ምክንያቶች ለምሳሌ በውጭ አገር ሆነው ጉባኤዉን በአካል በመገኘት መካፈል ለማይችሉትም ቤተክርስቲያን አስፈላጊውን ሁኔታዎችን እያመቻቸች በመሆኑ እኛም ሁላችን አስፈላጊውን ነገር ሁሉ በቤተክርስቲያን በኩል ከዋኖቻችን ማግኘት ስለሚቻል ይህንን ቻናል መዝጋትና ለቤተክርስቲያን ድምጽ ታዛዥ መሆንን መርጠናል ይህም ሐሳብ የብዙዎቻችሁም ሐሳብ እንደሚሆን እናምናለን።

ይህ ቻናል መች እና ለምን አላማ ተከፈተ?
👇👇👇👇👇
የተከፈተው በ2012ዓ.ም ሲሆን
አላማውም👉 ጊዜው የኮረና(COVID-19) ጊዜ ስለነበረ ሁሉም ነገር የህዘብ መሰብሰቢያዎች ጸሎት ቤትንም ጨምሮ የተዘጋበት(Locked የሆነበት ) ጊዜ በመሆኑ በሰዓቱ ብዙ ሰው ቀኑን ሙሉ ቤት ውስጥ የሚያሳልፍበት ጊዜ ስለነበር መንፈሳዊ ትምህርቶችንና መዝሙሮችን ርቀት ሳይገድበን መካፈል እንድንችልና መንፈሳዊነታችን/የውስጥ ሰውነታችን እንድጠነክር ታስቦ ተከፍቶ እስከ ቅርብ ጊዜም ድረስ ይህንኑ አላማ ተግባራዊ በማድረግ ወደ እናንተ ስያደርስ ነበር።

አሁን ግን በተሻለ ሁኔታና በተቀናጀ መልኩ በቤተክርስቲያን በኩል የDIGITAL-MEDIA እየተዘጋጀ ስለሆነና ቤተ ክርስቲያናችን መመሪያዎችን ስላወጣች እኛም የወጣውን መመሪያ በደስታ ተቀብለን ለመተግበርና ለመታዘዝ ይህንን ቻናል ለመዝጋት ወስነናል።

ስለሆነም ምናልባት በዚህ ቻናል ያላችሁ ወንድሞችና እህቶች ከዚህ ቻናል የሚትፈልጉትን ማንኛውንም ፋይል ሆነ መዝሙር ካለ እስከ መጭው ረቡዕ ወይም 03/07/2016 ድረስ መውሰድ የሚትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን🙏

በእርግጥም ይህን ጥያቄ የሚጠይቅ አይጠፋም 👉 "ለምን ቻናሉን ለሌላ ነገር አትጠቀሙም?" የሚል ጥያቄ እንደሚኖር ይታመናል።
👉 እኛም አስበንበት ነበር ነገር ግን ለመንፈሳዊ እንቅስቃሴ አላማ የተከፈተውን ቻናል ለሌላ ነገር ወይም ለግል ጥቅም መጠቀም ጥሩ ሆኖ ስላላገኘነው መዝጋቱ የተሻለና የሌላውንም መንፈስንም የጠበቀ ሆኖ አገኝተነዋል።


(ወደ ዕብራውያን ምዕራፍ 4)
----------
6፤ እንግዲህ አንዳንዶች በዚያ እንዲገቡ ስለ ቀሩ፥ ቀድሞም የምስራች የተሰበከላቸው ባለመታዘዝ ጠንቅ ስላልገቡ።
. . .
11፤ እንግዲህ እንደዚያ እንደ አለመታዘዝ ምሳሌ ማንም እንዳይወድቅ ወደዚያ ዕረፍት ለመግባት እንትጋ።

" የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከሁላችን ጋር ይሁን፤ አሜን።"
(የዮሐንስ ራእይ 22:21)

ቀን 25/05/2016       date 2024/03/04


Deadline date 03/07/2016 E.C


ምልክት_አድርጉባቸው_መጋቢ_ኤልያስ_ሽባባው_May_7_2012.pdf
188.5Kb
👉 #ምልክት አድርጉባቸው መጋቢ ኤልያስ ሽባባው

👆👆ይህንን ከላይ ያለውን ጽሑፍ ነበር ብሾፕ ደጉ አንብቡ ያሉን እናም ሁላችንም እናንብብና መጠንቀቅ ካለብን ነገር ሁሉ እንጠንቀቅ።

@zaremgetan


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
ለሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ወንድሞችና እህቶች ከአባታችን ከቢሾፕ ደጉ ከበደ የተላለፈ ማሳሰቢያ!

@zaremgetan


          ⚠️ ለጥንቃቄ ያህል!!!

ቴሌግራማቹን ከአጭበርባሪዎች ይጠብቁ!!!

ቴሌግራም ላይ ከማንኛውም ሰው በ cutt.ly  ወይም  bit.ly  የሚጀምር ማንኛውም ሊንክ ተልኮላችሁ ስታገኙ እንዳትከፍቱት ምክንያቱም ሰሞኑን የመጣ ቫይረስ አለ ሙሉ ለሙሉ የተፃፃፋችሁትን እና Join ያደረጋችሁትን ቻናሎች ሁሉ በማጥፋት እንደ አዲስ አካውንት ያስከፍታችኋል። ይህ ትልቅ ጥንቃቄ የሚያስፈልገው ነገር ነው ።

እንደዚህ ዓይነት ሊንኮች በምታውቋቸው ሰዎች ስም ጭምር ሊላክላችሁ ይችላል ነገር ግን በጭራሽ እንዳትከፍቱ።

በተጨማሪም ከሀከሮች አካውንታችሁን ለማዳን በምታስታውሱት Password Two-Step Verification On ያድርጉ!
በቴሌግራም በኩል የሚመጡ የተማጽኖ፣ የሚያጓጓ፣ የወዳጅነት ማማለያዎች ከተላከልዎም ማስፈንጠሪያውን እንዳይነኩት።
አደገኛ ቀበኞች በቴሌግራም በኩል መጥተው በእርስዎ ስም የፈለጉትን ብክለት ሊያስተላልፉ ታጥቀው ተነስተዋል።

ቲክቫህ የዜና አውታርናና ሌሎችም ይህንን ችግር በመረዳት ሰፋ አድርገው  ዘግበውታል መረጃ ይጠቅማልና እነሆ!!

"ከተለያዩ ሰዎች ጹሑፍና ሊንክ ያለው መልዕክቶች እየተላኩ ነው። ብዙዎች ይህ ጉዳይ በተደጋጋሚ እየደረሳቸው እንደሆነና የጥንቃቄ መልዕክቱን እንድናስተላልፍ ጠይቀውናል።

በመልዕክት የሚላከው ሊንክ ምንድን ነው?

በመልዕክቱ አብሮ የሚደርስዎት ሊንክ የቴሌግራም አካውንትዎን ለመጥለፍ የተዘጋጀ ቴሌግራምን የሚመስል ድረ-ገጽ ነው። ሊንኩን ሲከፍቱት ስልክ ቁጥር አስገብተው ወደ ቴሌግራም እንዲገቡ ይጠይቅዎታል።

ቁጥርዎን አስገብተው የሚመጣው ሌላኛው ገጽ በቴሌግራምዎ የተላከልዎትን አጭር የማረጋገጫ ቁጥር እንዲያስገቡ የሚጠይቅ ነው።

የተላከልዎትን የማረጋገጫ ቁጥር ካስገቡ የእርስዎን ቴሌግራም በቀጥታ ወጥመድ ያዘጋጁ ሰዎች መጠቀም ይጀምራሉ። በዚህም መልዕክቶችን ለሌሎች መላክና እርስዎ እንደላኩት አድርገው ማቅረብ ይችላሉ።

ይህ ገጽ ልክ ቴሌግራምን እንዲመስል ተደርጎ የተሰራ ሲሆን የሚያስገቡት መረጃ ግን ወደ ቴሌግራም ሳይሆን ይህንን ወደ ሚቆጣጠሩት ሰዎች የሚላክ ነው። ይህ ዓይነቱ ማጭበርበር ማጥመድ (Phishing) በመባል ይታወቃል።

ምን ማድረግ እችላለሁ ?

ይህ ችግር ካጋጠምዎት ቀጥታ ቴሌግራምዎ ላይ Setting ውስጥ በመግባት #Device የሚለውን በመጫን የእርስዎ አካውንት በምን በምን ስልኮች ላይ እየሠራ እንደሚገኝ ማየት ይችላሉ። በዚህም ከእርስዎ ቁጥጥር ውጪ ያሉ ስልኮችን በሙሉ ማስወጣትና እርስዎ የሚጠቀሙበትን ብቻ ማስቀረት ይችላሉ።

ሁለተኛው መንገድ ይህ ችግር ከመፈጠሩ በፊት የሚያገለግል ሲሆን ሁለተኛ ዙር የደኅንነት ማረጋገጫ (Two-Step verification ) መጠቀም ድንገት ለእንደዚህ ዓይነት ችግሮች ብንጋለጥ ተጨማሪ የደኅንነት ማረጋገጫ ይሆነናል።

Share በማድረግ ለምታውቁት ሰው ይላኩ!

@Zaremgetan
@zaremgetan
@zaremgetan


ሁላችሁም ተጋብዛችሁኃል!
23ኛ ዓመት በሆሳዕና ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን ማራናታ ሕብረት መዘምራን የመዝሙር ፌስቲቫል
መስከረም ከ12-13 ሙሉ ቀን

Join👉 @zaremgetan
👉@zaremgetan
👉@zaremgetan


Forward from: Apstolic songs🎧🎤
በስፍራው ሁሉ ላላችሁ የቤተክርስቲያን ልጆች ሰላም ለእናንተ ይሁን!

እንኳን ለ 2016 ዓ.ም አዲስ አመት በሰላም አደረሳችሁ!

አዲሱን አመት በልባችን ለጌታ እየተቀኘንና እየዘመርን ለመጀመር የኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ኦዲዮቪዥዋልና ስነ-ጽሑፍ ክፍል በዘማሪት ዮርዳኖስ መለስ የተዘጋጀውን አዲስ የዝማሬ ሰንዱቅ (Album) ለመታነጽና ለበረከት እንዲሆንላችሁ ወደ እናንተ ሲያደርስ በታላቅ ደስታ ነው።

ይህንን አልበም አዘጋጅታ ለእግዚአብሔር ክብርና ለቤተክርስቲያን መታነጽ ያበረከተችውን እህት ዮርዳኖስንና በዝግጅቱ የተሳተፉትን ሁሉ እግዚአብሔር በማያልቀው በረከቱ እንዲባርካቸው እየጸለይን ጌታችን ቢፈቅድ ብንኖር አልበሙ በጥቂት ቀናት ውስጥ እጃችሁ ባለው ስልክ ላይ በሚገኘው የአፖስቶሊክ ሶንግስ መተግበሪያ ላይ ዝግጁ ይሆናል።

የኦዲዮ ቪዥዋልና ስነ-ጽሑፍ ክፍል

ነሐሴ 2015 ዓ.ም
@apostolic_songs


Watch "ዶ/ር ተስፋዬ ሮቤሌ "ለምን only Jesus አልሆንክም ቢለኝ confused ያደረከኝ አንተ ነህ እለዋለሁ"" on YouTube
https://youtube.com/shorts/JXPtTajNjlA?feature=share

" የማያምኑ ስለ ሆኑ በቃሉ ይሰናከሉበታልና፤ ለዚህ ደግሞ የተመደቡ ናቸው።"
(1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 2:8).

ይህ ነው እንግድህ የስላሴ ትምህርት መጨረሻው! እግዚአብሔር ቃሉን ይግለጥላቸው🙏


👇👇FAKE ACCOUNT 👇👇
ውድ የቃሉ ይናገር ቤተሰቦች ከታች እንደምታዩት በቃሉ ይናገር ስም ሥላሴያውያን Fake YouTube account ከፍተዋል። ይህ የመሸነፋቸው ማሳያ ነው። ትክክለኛው የቃሉ ይናገሩ YouTube account ከ1660(1.66k) በላይ subscribers ያለውና 167 videos ያለው ስለሆነ እንድታውቁ እናሳስባለን!።
👇👇ትክክለኛው የቃሉ ይናገር YouTube link 👇👇
https://youtube.com/@letthewordspeakout7131


ውድ ወንድሞች እና እህቶች፣ ምሩቃን ፣ እንዲሁም ተማርዎች የየሱስ ክርስቶስ ሰላም ይብዛላችሁ!!
ጠቃም ምክር-ሀሳብ/ማሳሰቢያ/

በመጽሐፍ ቅዱስ ለምትደገፉ ሁሉ

ይህ ያለንበት 21ኛ Century /ክፍለ-ዘመን Globalization እና Modernization ብዙ የሰውን ልጅ ሕይወት በPositiveም በNegativeም
የተቆጣጠሩበት ዘመን መሆኑ ለሁላችንም ግልጽ የሆነ ነገር ሲሆን፣

በተለይ እውቀት መሳይ የዲያብሎስ አሳብ የምሳካበት መሳርያ እየሆነ መምጣቱ ፣ በጣም የሚያሰጋ ጉዳይ ሆኖዋል።

ይህ እንድህ እንዳለ፥ እንደአንዳንድ ነገሮች ለሥጋ ኑሮአችን ስለምጠቅሙን Update እንዲሆኑ /እንዲታደሱ/ ሚንፈልጋቸው ልኖሩ ይችላሉ፥

ግን ይህን እድሳት/Updating/ ሁሉም ቦታ እና ነገር ላይ ስንጠቀም /Apply/ ስናደር አሉታዊ ተጽኖ ልኖረው እንደምችል ይታመናል ፣ምንም ጥያቄም የለውም።

ይህን ነገር "አድሱ መደበኛ ትርጉም" የሚል መጽሐፍ ቅዱስ እትም International Bible Society  1993 ዓ.ም(2001) ታተመ ይላል፣
በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ያሉ ፣  በተለይ ስለ መለኮት እና ስለመዳን ቁልፍ የሆኑ ጥቅሶች በተለይም ዮሐንስ በጻፈው ወንጌል ላይ ያነጣጠረ ፣ ከዚህ በፍት ሁላችንም ስንጠቀም ከነበርነው፥ 1962 እትም ጋር ስናስተያየው ፥ በማይገናኝ መልኩ ታድሶዋል(Updated) ሆኖዋል።
ከሆነውም አብላጫው ከአድስ ክዳን ነው ፣ ለምሳሌ ያክል፥
ማቴ 1^23
ዮሐ/ወ 1^1-2
ዮሐ/ወ 1^9-10
ዮሐ/ወ 8^24-25
ዮሐ/ወ ምዕ 8 ሙሉ እዩ
ዮሐ/ወ ምዕ 10
በአድስ ክዳን ገጽ መጨረሻ ላይ በተቀመጡ ጥቅሶች ውስጥ፣
1962ቱ የሐዋ.ሥ 2^38=ማቴ 28^19 ፤ ግን 19993/2001ቱ ላይ ደግሞ የሐዋ 2^38 ን ማቴ 28^19ን ቆርጦ አውጥቶታል!

ድፍረታቸው በጣም ነው ያስፈራኝ
ስለዚህ ፣ ውድ ወንድሞች እና እህቶች፥ በተለይም ይህ ድርግታቸው ግልጽ የሚሆናችሁ፣
" በሰይጣን እንዳንታለል፤ የእርሱን አሳብ አንስተውምና።" ተብሎ የተጻፈውን የእግዚአብሔር ቃል ልብ በሉ!
(2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2:11)

በተጨማር የእግዚአብሔር ቃል /መጽሐፍ ቅዱስ/ Update አይደረግም የሚል እምነት፣ በሁሉም አእምሮ መታተም አለበት።
ይህን መረጃ ለወዳጅ ፣ ለዘመድ እና በዚህ ለምደገፉ ሁሉ Share እንድታደርጉ፣
1993/2001 እትም በእጃችሁ ካለም እንዳትጠቀሙ።

በተጨማሪ ማስረጃ ከፈለጋችሁም ስለ መዳን እና ስለ መለኮት የተጻፉ ጥቅሶችን ማስተያየት ትችላላችሁ።

@zaremgetan


በቤተክርስቲያናችን አገልጋዮች የተከፈተና ስለ ኢየሱስ ማንነት በግልጥ እያስተማሩ እና የስላሴ ትምህርት መጽሐፍ ቅዱሳዊ እንዳልሆነ በግልጥ የሚንማርበትና እኛም ለሌሎች እንድንመሰክር የሚረዳን ቻናል ተከፍቷል!
ቃሉ ይናገር👉 @kalu2023
Join & Share በማድረግ የውሸት አስተምህሮን እናጋልጥ የእውነተኛውን ኢየሱስ ማንነት እንናገር!

በተጨማሪም በዩቲዩብም ይህንን ቻናል ታገኛላችሁ!

ከአገልጋዮቹም መካከል ቄስ ኤልያስ ሽባባው፣ቄስ ታምራየው፣ ቄስ በረከት እና ሌሎችም በጥልቀት እያስተማሩ ይገኛሉ።






አርባምንጭ ዩንቨርሲቲ ለተመደባችሁ ወንድሞች እና እህቶች ከላይ በፎቶው ላይ ባለው አድራሻ የፌሎ ወንድሞችን እና እህቶችን አነጋግሯቸው! ይረዷችኋል!


Forward from: Fellowship Apostolic Church Students WCU 💒
አማላጅ_በቅዱስ_ቃል_መሠረት_መዝገቡ_ጌታቸው_ማሞ_ኤጲስ_ቆጶስ.pdf
1.4Mb
ኢየሱስን ማን ይሉታል .PDF
1.0Mb
#አዲስ_መጽሐፍ

አማላጅ - በቅዱስ ቃል መሠረት - መዝገቡ ጌታቸው ማሞ (ኤጲስ ቆጶስ).pdf


Forward from: Fellowship Apostolic Church Students WCU 💒
Silase Ateyayaki Mistr.pdf
75.1Mb
የሥላሴ አጠያያቂ ሚስጢር...
በፓስተር ኤልያስ ሽባባው

ሁላችሁም አውርዱ አንብቡ ጊዜ እና ትኩረት ሰጥታችሁ


➣መንፈሳዊ_ግጥም

😇 ሠራተኛ ቀባልን 😇

ከዘመድ ከወገን ለአንተ የተለየ
የሰማዩን ራዕይ አሻግሮ ያየ
ሀሳብህን ብቻ ሊያገለግል የወሰነ
ቆረጥና ጀግና ልበ ሙሉ የሆነ
እንደ ሙሴ ያለ እጅግ የጨከነ
ከአንደበቱ ይልቅ በሥራዉ የተመነ
ይህ አለም ቢዳላዉ ቢሎም ባይዳላ
የማያይ ግራ ቀኝ የማያስብ ሌላ
ፊት ብቻ የሚጓዝ ማይል ወደ ኋላ /2*
አላማውን ያወቀ ጠንቅቆ የተረዳ
ብሎ የማይከፍል ሰውን ዘመድ ባዳ
ገብቶ የሚጠይቅ ምስኪኑን ከጓዳ
አለት ነው ሀሩር ወይም ምድረ ባዳ
ይሄኛዉ ይቅርብኝ ነዉ እኔን ሚጎዳ
ሳይል ሳያቅማማ በፍቅር ሚነዳ
ተዘጋጅቶ ያለ በትግሉ ሜዳ
ወገቡን አጥብቆ ለመሮጥ የተሰለፈ
ስለ አንተ የገባዉ ከመውደድም ያለፈ
ከሚያወራዉ በላይ ሞልቶ የተረፈ
ርሃብ ይሁን ችግር የሚናድ ተራራ
ስደት ቢሆን ሞት ወይ ሌላ መከራ
ይህ ሁሉ ቢደረብ ሳያንገረግር ሳይፈራ
ጉዞዉን ሚቀጥል ሥራህን ሚሠራ /2*
ቅንአትህ ሚባለዉ ሁሌ የሚተጋ
ከጨለማ ሀይለት ጋራ ጸንቶ የሚዋጋ
ከአንተ በተሰጠው በፈሰሰው ፀጋ
ለሚጠፉት ነፍሳት የሚከፍል ዋጋ
ለማስመለጥ ሚጥር ከሳይጣን መንጋጋ
የሀሰት ነቢያትን አፍ የሚያስዘጋ
የሚሠራ ለአንተ ያማረ መሠዊያ
ማይርቅ ከመቅደስህ የሆነለት መኖሪያ
ነፍሱን ሥጋዉን የደረገ ለአንተ ማደሪያ
የታሰረ በፍቅር በሠለም ማሰሪያ
ለሚያዩት የሆነ መልካም አርአያ
በእጁ የያዘ መዋጊያ መሣሪያ
አስነሳ ኢየሱስ እንዲህ ያለ ባሪያ /2*
የጊዜውን ጥቅም ስለ አንተ የተወ
ስለ ተሰጠው ሥራ ራሱን ሚሰዋ
ብርቱ ወታዳር የማይሆን ፈዘዛ
የአለም ነገር መሆኑን አውቆ ጤዛ
ጊዜዉን ሚጠቀም የማይውል በወዛ
እያደገ ሚሄድ ቁም ነገር ሚያበዛ
የተረከበዉን ያን ትልቅ አደራ
ማያየው አሳንሶ አቅልሎ እንደተራ
እጅግ ተፈትኖ ተቀምሞ የነጠረ
መንጋዉን ወደ መስክ የሚያሠመራ
ለዚህ የተሰበውን የዘመኑን ባለ ተራ
አንድ ሰዉ አሳድግ እባክህ አደራ/2*
ሸክም የሚሰመዉ ከአንተ የተቀባ
አምላኩን ሚገነኝ በጸሎትና እንባ
ሕዝቡን የሚያኖር አንጾ እንደ ሚገባ
የሚመራ ሳይዝል ከነአን እስክያገባ
ማንም ሳይገፋፋዉ ሳይባል ተነስ
በበጎ ፈቃዱ ፊት የሚገሰግስ
ለምለሙን ሣር በሬ አንደ ሚጨርስ
በእዉነቱ ወንጌል ምድሪቱን የሚወርስ
የጣዖትን መሠዊያ ከለበት የሚያፈርስ
ጥሮና ታግሎ ምርኮን የሚያስመልስ
ስምህን አድርጎ መከታና ምርኩዝ
ከቶ የማይፈራ በእምነት የሚያዝ
በበዘለት ቅባት የተባለ ጎበዝ
የጠለትን ደጅ በድፍረት ሚበዘብዝ
ነጥሎ ሚያወጠ ከሚበለው ነቀዝ
አይዞህ እያለ ደካማዉን ሚያግዝ
የኋላዉን ትቶ ወደ ፊት ሚሰለፍ
ተላላ የማይሆን በምንም የማይሰንፍ
በአገልግሎቱ ብዙዎችን የሚያተርፍ
ከአንተ ይላክልን ጽድቅን ሚደግፍ
እፎይ የሚያሳኝ ልብህን ሚያሳርፍ
ነገር ግን ከጌታ ኢየሱስ የተቀበልኩትን
እርሱም ፀጋን ወንጌል መመስከርን
አገልግሎቴንና ደግሞም ሩጫዬን
ካልፈፀምኩ ነፍሴ በእኔ እንደማትከብር
እቆጥራለዉ አንደተራ አንደ ከንቱ ነገር
ሃዘን ቢሆን ደስታ አይለየኝም ያለ
በከበረዉ ቃልህ እንዲህ ብሎ የማለ/2
ጌታ ሆይ ሹምልን አንተን ብቻ የሚያይ
ምንም ቢፈጠር የማይሆን ወለዋይ
ስኬቱን ያለመ ያለዉ ትልቅ ራዕይ
እግሮቹን ያጸና በእውነት አለት ላይ
የሩጫዬ መደሚዳሚያ ነዉ ሰማይ
ብሎ የሚጓጓዉ ደርሶ እሰከ ሚያይ
የማያመነታ ፍፁም እዉነተኛ
ታማኝና በጎ የአንተ መልዕክተኛ
በመንግስትህም ዉስጥ ትጉ ሠራተኛ
የመረጥከውን ላክ ተተኪ ተረኛ
ቀብተህ አውጣልን የወንጌል አርበኛ።/2


........ ➣ በወ/ም ይስሐቅ ወ/ማርያም (ከምስራቅ ሆሳዕና )

@zaremgetan


በቶሎ ይነበብ ልንነቃ ይገባል
ለማንበብ 15 ደቅቃ ብቻ ስጥ ህይወትን ይቀየራል አትሳሳት
share አድርገው
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ዓለም ወዴት እየሄደች ነው? 1. - መጽሐፍ ቅዱስን ማቃጠል በኡጋንዳ በይፋ ተረጋግጦአል
* በደቡብ አፍሪካ ውስጥ ፣ ወንድ ወይም ሴት በዝሙት ምክንያት ሌላውን የመክሰስ መብት የለውም
*በአሜሪካ እየታየ ያለው የወንድ ለወንድና የሴት ለሴት ጋብቻ
*ጀርመን ወንድም እህቱን ማግባት እንደሚችል ፣ አባት ልጁን:እናት ልጆአን የማግባት ፍቃድን መስጠቱ ፡፡
*የmiami ከተማበመንገድ ላይ ፣ በቤተ ክርስቲያን ፣ በገቢያ ፣ በእግር ኳስ ሜዳ ወዘተ ውስጥ ወሲባዊ ግንኙነት በማንኛውም መንገድ ማግኘት እንዲችሉ መፍቀዶአ
.*ካናዳ (ከእንስሳት ጋር የ sexታ ግንኙነትን መፍቀዶአ
* በስፔን ውስጥ-የወሲብ ፊልሞች በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እና በዩኒቨርሲቲዎች መፈቀዱ *- ለአካለ መጠን ያልደረሱ ዝሙት አዳሪዎች ፈቃድ ማሪ ሉክ በህግ መፈቀዱ *በመጨረሻም ዩኤስ አሜሪካ የሰይጣንን ቤተ ክርስቲያን ከፍታለች ፡፡ በይፋ።
የተከበራችሁ ወንድሞች እና እህቶች ፣ መጨረሻው ተቃርቧል ፣ ጌታ ኢየሱስ በቅርቡ ይመጣል! ማርታናታ!!!
ክርስትያኖች ትኩረታቸው እየተከፋፈሉ ሲሆን ዲያቢሎስ መለኮታዊውን ምህረት ለማስቆም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ነፍሳት ከእርሱ ጋር ሊወስድ ይፈልጋል ፡፡ ደቂቃ ካለዎት ... ይህንን መልእክት ያጋሩ ፡፡ ለምን በቤተክርስቲያን ውስጥ እንተኛለን ? ስለ እግዚአብሔር ማውራት ከባድ የሆነው ለምንድነው ሐሜት ለመናገር በጣም ቀላል የሆነው ለምንድነው? የእግዚአብሔርን መልእክት ችላ ማለት ለምን ቀላል ሆነ?
ይህንን መልእክት ለጓደኞችዎ ይልካሉ ወይም ችላ ይላሉ? እግዚያበሔር “በሰዎች ፊት ብትክዱኝ በአባቴ ፊት እክድዳችሁአለሁ” አለ ፡፡ እግዚያበሔር ከወደዱ ይህንን መልእክት ለምርጥ ጓደኞችዎ እና በቡድን በ 60 ሴኮንድ ውስጥ ያጋሩ ፡፡ እግዚአብሔር ይባርኮት. ኣሜን
የአለም መጨረሻ ተቃርቧል አትዘናጉ
አሁን ያለንበት 2014 ዓም + 5500 ዘመን=7514 ስለዚህ ከ 8ኛው ሽ ላይ ቀንሱት ።
8000 – 7513= 486 ዓም ይቀራል።
ነገር ግን ሰምታችሁ ከሆነ ዘንዶ 400 ዓመት ገዝቷል ይባላል እስኪ ጠይቁ።
እና የዘንዶው ሲቆጠር 486 – 400 =86 አመት ቀረው።ትንቢቱም እየተፈፀመ ነው። ሌላው ይህ በንዲህ እንዳለ ደሞ
666 አሁን እዚህ በደጃችን ነው፡፡ አጠንክረን እንፀልይ፡፡ የአውሬው
ቁጥር 6 6 6 የሚፈፀምበት የትንቢት ጊዜ አልቋል/ተፈፅሟል፡፡
የአሜሪካ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት ባስተላለፈው የኦባማን የጤና
ሽፋን ረቂቅ በህግ እንዲካተት ተደርጓል፡፡ የህግ ተግባሩ በቅርቡ
ይጀምራል፡፡ ይህን የጤና ሽፋን ረቂቅ በእያንዳንዱ የአሜሪካ ዜጋ
የሰውነት ክፍል ላይ ግላዊ የሬዲዬ ፍሪኩዌንሲ ቺፕስ መልክ (RFID
CHIPS) እንዲተከል ታዟል፡፡ ይህ ቺፕስ በግንባር ወይም በክንድ ላይ
ይደረጋል፡፡ ይህ ደግሞ በመጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረው በራዕይ 13 :
15 -18 የተቀመጠውን የአውሬው ምልክት ይፈፀም ዘንድ ነው፡፡ እና
አሁንም ስለ ፍፃሜው ትጠራጠራለህ? ታውቃለህ ለኦባማ የተለየ
መኪና እንደተሰራ አውሬው የሚባል? ተዘጋጅ ንጥቀት አሁን
ይጀምራል፡፡ ራዕይ 13ን ቀድመው ተጫውተውታል፡፡ ብዙዎች ግን
ይህን አልተገነዘቡትም፡፡ 1. ለምንድን ነው ይህ ችፕስ ከባንክ
አካውንት ጋር የተቆራኘው ወይም የተገናኘው? አስታውሱ መጽሐፍ
ቅዱስ እንደሚለው ካለ አውሬው ቁጥር 666 ልትገዙም ወይም
ልትሸጡም አትችሉም ስለሚል፡፡ እስኪ ገምቱ ይህ ቺፕስ ከገንዘብ
ዝርዝር መረጃ ጋር ለምን ተገናኘ? እንዲያውም በጣም ያሳዘነኝ
በቤተክርስቲያን ያሉ ብዙዎች ሰዎች ጌታ ሲመጣ ይህን ሁኔታ
ሊያልፉት አይችሉም፡፡ ደግሞም ብዙዎቹ መጨረሻው እንደቀረበ
አያውቁም፡፡ የቴክኖሎጂ በጣም መራቀቅ ምክንያት ነው ብላችሁ
መልስ እንዳትሰጡኝ፡፡ በማንኛውም የህይወት ጎዳናችሁ
ከእግዚአብሔር ጋር ካልተስማማ አሁኑኑ ንሰሀ ግቡና ተለወጡ፡፡
ካለበለዚያ መንግስተ ሰማያትን ካጣችሁት ገሀነምን አታጡትም፡፡
ስለዚህ አስቡበት፡፡ ገሀነም መልካም ስፍራ አይደለም በጣም
አስከፊው ክፍሉ እንደ መንግስተ ሰማያት ዘላለማዊነት እንዳለበት
እዚህም እንደዛው ነው፡፡ ጆሮ ያለው ይስማ መንፈስ ለአብያተ
ክርስቲያናት የሚለውን ይስማ፡፡ ጠቃሚ ያልሆነ ነገር ከምትልኩ ይህን
ለሌላው ብታስተላልፉ መልካም ነው፡፡ ለምታውቋቸው ቅርብ
ለሆኗችሁ ሰዎች ላኩላቸው፡፡ እስኪ የወንጌላዊ ስራ እንስራ፡፡
እባካችሁ ለምታውቋቸው ለእያንዳንዳቸው በየስማቸው ላኩላቸው፡፡
ለሞባይል እንደምንጠነቀቅ ያክል ለእግዚአብሔር ቃል ብንጠነቀቅ
ምን እንደሚሆን ልትገምቱ ትችላላችሁ፡፡ ከዚህ ደግሞ በጭራሽ
ልንላቀቅ ነፃ ልንሆን አንችል፡፡ ስለዚህ የቻልነውን ያክል እንትጋ
እንጋደል፡፡ 7% የሚሆኑቱ ናቸው መልዕክቱን የላኩት በድጋሚ 93%ቱ
ግን አልላኩም አላወቁም ስለዚህ ጠንክረን እንስራ፡፡ ይህን መልዕክት በኋላ
እንዳትልኩት አሁኑኑ ላኩት!!!

ለ # 50 ሰው እባካችሁ 🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

@zaremgetan




new song : singer biniyam berhanu በኔ ላይ ከብረ ታይ

@zaremgetan 👈Join

20 last posts shown.

373

subscribers
Channel statistics