#ነዳጅ #ቤንዚን
በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተባባሰ የመጣዉን የነዳጅ ምርቶች ሕገወጥ ግብይት ለመከላከልና በየከተማዉ የሚስተዋሉ ረጃጅም ሰልፎችን በማስቀረትና የተጠቃሚዎችን ቅሬታ ለመፍታት በትኩረት እየሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን አስታወቀ።
የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሳህረላ አቡዱላሂ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፤ በነዳጅ ምርቶች በተለይ በቤንዚን አቅርቦትና ስርጭት በሁሉም የሀገራችን ክፍሎች ቅሬታዎች እንደሚነሱና ለዚህም በርካታ ምክንያቶች ስለመኖራቸው ገልፀዋል።
" አንዱና መሠረታዊዉ ምክንያት ከዚህ ቀደም 80 በመቶ የሚሆነዉ የሀገራችንን የነዳጅ ፍጆታ ይሸፍን የነበረዉ በሱዳን ወደብ የሚገባዉ ቢሆንም አሁን ላይ ሙሉ በሙሉ ወደ ጅቡቲ ዞሯል " ብለዋል።
" ወደቡ ላይ ከፍተኛ መጨናነቆች ይስተዋላሉ የጅቡቲዉ ወደብ ከ20 ዓመታት በፊት የነበረን የሀገራችንን የነዳጅ ፍላጎትና አቅርቦትን ለማስተናገድ ታስቦ የተሰራ ስለነበር በቴርሚናሉ ላይ ያለዉ መጨናነቅ መንግስት በከፍተኛ ድጎማ የሚያስገባቸዉ የነዳጅ ምርቶች በተለይም በቤንዚን አቅርቦትና ስርጭት ላይ አሉታዊ ተፅእኖ አሳድሯል " ሰሉ ገልፀዋል።
መንግስት አሁንም ድረስ ከፍተኛ የገንዘብ ድጎማ በማድረግ ወደ ሀገር ዉስጥ በሚያስገባቸዉ የነዳጅ ምርቶች ላይ አንዳንድ አከባቢዎች ሰዉ ሰራሽ አቅርቦት እጥረት እንዲፈጠር በማድረግ የግል ጥቅማቸዉን ለማካበት የሚጥሩ አካላት መኖራቸዉን ማረጋገጣቸውን ወ/ሮ ሰሃረላ ተናግረዋል።
በቴክኖሎጂ የታገዘ ቁጥጥርና የአሠራር ስርዓት በመዘርጋት ሕገወጥ ግብይቱን የመከላከልና በህገወጦች ላይ እርምጃ የመዉሰዱ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።
" ከአቅርቦቱ ባሻገር ወደ ሀገር ዉስጥ የገባዉን ቤንዚን በአግባቡ በማሰራጨቱ በኩል በየክልሉ የተለያዩ ክፍተቶች አሉ " ያሉት ዋና ዳይሬክተሯ በተለይ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በሁሉም ማዕቀፎች ጥብቅ ቁጥጥርና ክትትል መወሰድ በመጀመሩ በርከት ያሉ የንግድና ገበያ ልማት ባለሙያዎች ማደያዎችን ጨምሮ በሕገወጥ ግብይቱ ሰንሰለቱ ተሳታፊ የሆኑ አካላት ላይ በየደረጃው እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን አብራርተዋል።
ለአብነትም በሲዳማ ክልል ብቻ የግብይት ስርዓቱ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ በመፍጠር ሰዉ ሰራሽ እጥረት እንዲስፋፋ ያደረጉ 9 ማደያዎች ላይ ነዳጅ እንዳያገኙ እገዳ እንደተላለፈባቸው ገልፀዋል።
በሌሎችም ክልልሎች በዚህ ረገድ እየተከናወኑ ያሉ የቁጥጥርና ክትትል ተግባራት በቅርቡ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከፀደቀዉ አዲሱ የነዳጅ ምርቶች ቁጥጥር አዋጅ ጋር ተዳምረዉ በዘርፉ የሚስተዋለዉን ችግር በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚቀንሰዉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
@zena_ethiopia24