ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
አዲስ አበባ
ጉዳዩ፦በቅርቡ የተሰጠ የህወሓት ምዝገባ በማስመልከት ያለን ቅሬታ ማቅረብን ይመለከታል
ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ነሐሴ 03 ቀን 2016ዓ.ም ለህወሓት በልዩ ሁኔታ የምዝገባና የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት መስጠቱን ይታወቃል።
ቦርዱ ይህንን በማስመልከት በተመሳሳይ ቀን በሰጠው መግለጫ በተራ ቁጥር 2 ደግሞ ህወሓት የፓርትው ኃላፊዎች ስምና ፊርማ የያዘ ሰነድ ማቅረቡን ይፋ አድርጓል።ይሁንና ይህ የምዝገባ ጥያቄ ህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ የማያውቀው እና እኛ ደግሞ ለዚሁ ምዝገባ ብለን የፈረምነው ምንም ዓይነት ሰነድ ሳይኖር ግለሰዎች ብቡድን ተደራጅተው ከድርጅቱ አሰራር ውጭ የፈፀሙት ያልተገባ ተግባር መሆኑን ማሳወቅ እንወዳለን።
በመሆኑም ይህ ድርጊት እኛ የማናውቀው መሆኑን እየገለፅን በድርጅቱ ስም ምዝገባ የጠየቁ ግለሰዎችም እኛን ሳያስፈቅዱ የፈፀሙት መሆኑን እየገለፅን ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለነዝህ ግለሰዎች የሰጠው ምዝገባ በተጭበረበረ ማስረጃ መሰረት የተሰጠ በመሆኑ መልሶ እንዲመረምረው እንጠይቃለን።
የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ስም ዝርዝር እና ፊርማ ቀጥለን የምናቀርብ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ከሰላምታ ጋር
ጌታቸው ረዳ