የክረምት ጭቃ
ዝናቡ ዘነበ መሬት በሰበሰ ፣
ብርዱም እያየለ እሸት አሰጠበሰ ፣
የተጣለውንም Rain ኮት አስነሳ ፣
በትሸርት ሃጁን ጃኬት አስለበሰ ፣
ነገርግን ኣንዳንድ ሚያሳልፍ አለ ከዚህም የባሰ ፣
ዝናብ ማይበግረው ቢዘንብበትም ዶፍ ፣
ብርዱ የሚሞቀው እሳት ሚመስለው ጎርፍ ፣
የክረምቱ ጭቃ የሚመስለው ምንጣፍ ፣
አለ የሚዋኝም ፍቅር በሚሉት ወልፍ ፣
ለኣፍቃሪ ሰዎች ሁሌም ክርምት ነው ፣
ብርድ ብርድ ይለዋል ተፈቃሪን ሲያጣው ፣
ጃኬቱን ቢደርብ እሳቱን ቢሞቀው ፣
ከአካሉ አልፎ ለልቡ አይደርሰው ፣
ሻዩንም ቢጠጣ ቡናውን ቢደግመው ፣
ከአካሉ አልፎ ልቡን አያሞቀው ፣
ሁሌም ይበርደዋል በፎንቃ ያለ ሰው ፣
ባካችሁ ተረዱ የተፈቀራቹ ፣
በብርድ አይገረፍ ሰው ያሳዝናቹ ፣
በክረምቱ ጭቃ እያስዘፈቃቹ ፣
ብቻውን እንዲስቅ ስንቱን ጋበዛቹ ፣
ስንቱንስ ጤነኛ እብድ አስመሰላቹ ፣
ክርምቱን በጋ ነው ማለት ጀምረዋል ኣሁን ኣንዳንዶቹ ፣
እያለ ያወራል የክረምቱ ጭቃ ፣
ልቡ ነጉዶበት ተይዞ በፎንቃ ፣
ያንን ነጩን ወተት ያለውን በእቃ ፣
ጥቁር ነው እያለ በአራት ነጥብ ደምድሟል በቃ ፣
ግጥም
Semer muhidin /Almeshan
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን 🙏
Join us 👇👇👇 https://t.me/joinchat/AAAAAE-H14mYFGMHTdYugA
ዝናቡ ዘነበ መሬት በሰበሰ ፣
ብርዱም እያየለ እሸት አሰጠበሰ ፣
የተጣለውንም Rain ኮት አስነሳ ፣
በትሸርት ሃጁን ጃኬት አስለበሰ ፣
ነገርግን ኣንዳንድ ሚያሳልፍ አለ ከዚህም የባሰ ፣
ዝናብ ማይበግረው ቢዘንብበትም ዶፍ ፣
ብርዱ የሚሞቀው እሳት ሚመስለው ጎርፍ ፣
የክረምቱ ጭቃ የሚመስለው ምንጣፍ ፣
አለ የሚዋኝም ፍቅር በሚሉት ወልፍ ፣
ለኣፍቃሪ ሰዎች ሁሌም ክርምት ነው ፣
ብርድ ብርድ ይለዋል ተፈቃሪን ሲያጣው ፣
ጃኬቱን ቢደርብ እሳቱን ቢሞቀው ፣
ከአካሉ አልፎ ለልቡ አይደርሰው ፣
ሻዩንም ቢጠጣ ቡናውን ቢደግመው ፣
ከአካሉ አልፎ ልቡን አያሞቀው ፣
ሁሌም ይበርደዋል በፎንቃ ያለ ሰው ፣
ባካችሁ ተረዱ የተፈቀራቹ ፣
በብርድ አይገረፍ ሰው ያሳዝናቹ ፣
በክረምቱ ጭቃ እያስዘፈቃቹ ፣
ብቻውን እንዲስቅ ስንቱን ጋበዛቹ ፣
ስንቱንስ ጤነኛ እብድ አስመሰላቹ ፣
ክርምቱን በጋ ነው ማለት ጀምረዋል ኣሁን ኣንዳንዶቹ ፣
እያለ ያወራል የክረምቱ ጭቃ ፣
ልቡ ነጉዶበት ተይዞ በፎንቃ ፣
ያንን ነጩን ወተት ያለውን በእቃ ፣
ጥቁር ነው እያለ በአራት ነጥብ ደምድሟል በቃ ፣
ግጥም
Semer muhidin /Almeshan
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን 🙏
Join us 👇👇👇 https://t.me/joinchat/AAAAAE-H14mYFGMHTdYugA