ለሄቨን እናት ...🙏❤
ለሕጻን ሄቨን እናት በአዲስ አበባ የመኖሪያ ቤት ተበረከተላት
#Ethiopia | ለሕጻን ሄቨን እናት በአዲስ አበባ ከተማ የመኖሪያ ቤት እንዲሁም በሙያዋ በከተማዋ ውስጥ እንድትሰራ እድል ተመቻቸላት።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ዛሬ የሄቨን እናትን በማግኘት አጽናንተዋል።
ልጇን በግፍ ተነጥቃ ባለፈው አንድ ዓመት ፍትህ ሳታገኝ ለቆየችው የሄቨን እናት የፍትህ ሂደቱን ለመከታተል፣ ያለችበት ሁኔታ የተሻለ እንዲሆንላት እና ተጋላጭነቷን ለመቀነስ እንዲመች የከተማ አስተዳደሩ አንድ የመንግስት የመኖሪያ ቤት እንዲሁም በሙያዋ እዚሁ አዲስ አበባ ውስጥ እንድትሰራ መመቻቸቱን ከንቲባ አዳነች ተናግረዋል።
ከንቲባዋ የህፃን ሄቨን ጉዳይ የሁላችንም ጉዳይ በመሆኑ ድርጊቱ ተገቢውን ፍትህ ማግኘቱ የሌሎች ህፃናት ተጋላጭነትን ለመቀነስ አስተዋፅዖ ያለው ነው ማለታቸውን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።
የዚህ አይነት ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት እንዳይፈፀም የማህበረሰቡ የአመለካከት ለውጥ እንዲመጣ እና ችግሩ የጋራ ጉዳይ በመሆኑ ሁላችንም ኃላፊነታችንን ልንወጣ ይገባልም ብለዋል።
@YemzngnaDeset