ለጌታ ምናችሁን ታወልቃላችሁ?
በዛሬው ቆይታችን እግዚአብሔር ስለ ቅድስና መጀመርያ ያወራበትን ክፍል አንስተን በጣም አጭር ደቂቃ አብረን እናሳልፋለን። ዘጸአት ምዕራፍ 3 ላይ ሙሴ የእሳት ነበልባል ውስጥ ቁጥቋጦ ሳይቃጠል በማየቱ ወደ ኮሬብ ተራራ ወጥቶ ከእግዚአብሔር መልአክ ጋር ሲገናኝ እና ወደ ግብፅ እንዲሄድ እስራኤላዊያንን ነፃ እንዲያወጣ ምሪት ሲቀበል ያሳየናል።[ሙሉ ክፍሉን አንብቡትማ]
ለዛሬ ግን ቁጥር 5 ልቤን ሳበው። እንዲህ ያላል።
". . . አንተ የቆምህባት ስፍራ የተቀደሰች መሬት ናትና ጫማህን ከእግርህ አውጣ አለው።"
••• እግዚአብሔር ቅዱስ ነው። ለዚህ ነው እኛም ከእርሱ ጋር ህብረት አለን የምንል መቀደስ ያለብን። ዛሬ ላይ እግዚአብሔር እኛን እኔ ያለሁበት ስፍራ ቅዱስ ነውና ብሎ ልክ እንደ ሙሴ የእግራችሁን ጫማ አውልቁ ይላል ብዬ አላስብም።[ምናልባት ሊልም ይችላል] ግን ከጫማ ይልቅ የአሁን ዘመን ክርስቲያኖች እኛ አውልቀን መጣል ያለብን ብዙ ነገር አለ። እመኑኝ እኛ የአዲስ ኪዳን ትውልዶች ከሙሴ በበለጠ ከእግዚአብሔር ጋር ህብረት እንድናደርግ በክርስቶስ ሞት በኩል ታላቅ እድል ያገኘን ነን። በብሉይ ኪዳን ቅዱሳን ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሲሔዱ ማድረግ ያለባቸው ነገሮች። ራሳቸውን ቢያረከሱ ማድረግ አለባቸው ብሎ እግዚ አብሔር የሰጣቸው ህግ አለ።[ስለሱ ሌላ ጊዜ እናወራለን]
°°° ዛሬ ግን እኛ ራሳችን የመንፈሱ ማደሪያ የሆንን ከስላሴ ጋር ህብረት አለን የምንል ራሳችንን በብዙ ቀድሰን መንቀሳቀስ ያለብን ዘመን።
፠ እግዚአብሔር ለሙሴ የእግርህን ጫማ አውልቅ አለው። እኛን ፊት ለፊት ቢያወራን እግዜብሔር ምናችንን አውልቁ ሊል የሚችል ይመስላችኋል?
°°° የሀጢያት ማንነትን?
°°° ትዕቢትን?
°°° እምቢተኝነትን?
°°° ርኩሰትን?
°°° ዘረኝነትን?
°°° የልምምድ ህይወትን?
°°° አስመሳይነትን?
ወይስ ሁለንተናችንን አራቁተን ከእግሩ ስር እንድንወድቅ ያዘናል?
••• ሁላችንም ብናስተውል ለጌታ ክብር ማውለቅ ያለብን እጅግ ብዙ ነገር ይኖራል።
አስተውሉ! አውላቂውም አስታጣቂው ህያው መንፈስ ቅዱስ ነው። ስለዚህ ጥበባችንን ወዲያ ብለን ሁለንተናችንን ለእርሱ ሰጥተን ቡቱቷችንን እንዲያወልቅ እና ቅዱስ ማንነትን እንዲያለብሰን እድል እንስጠው።
ቅድስና ለእግዚአብሔር!!