ፅጌሬዳ
ክፍል 39
ካባቴ ቀጥሎ ምድር ላይ ትልቁን ቦታ ምሰጠው ሰው አንተ ትሆናለህ።
በየትኛውም ሁኔታ የሰጠኸኝን እምነት አልሰብረውም ።
በምንም ሁኔታ ውስጥ ብትሆን አልተውህም ይኼ ቃሌ ነው ቃሌ ደሞ ከልቤ ነው አለችኝ።
ግን ማሂ ማለቴ የኔስ ቤተሰቦች ችግር የለባቸውም እጅሽን ስመው ነው ሚቀበሉሽ ያንቺ አባት ግን እሺ ሚለን ይመስልሻል ማለቴ እኔን የልጁ ባል አድርጎ ሚቀበል ይመስልሻል አልኳት።
ይቀበላል አባቴ እንኳን አንተን የቀድሞ ባሌንም ተቀብሏል እኔ እስካመንኩበት ድረስ እንቢ አይልም ከራሱ ስሜት የኔን ነው ሚያስቀድመው አታስብ
አሁን ግን ህመም እየተሰማኝ ስለሆነ እባኮትን አቶ ባል አቅፈው ወደ ቤት ሊያስገቡኝ ይችላሉ አለችኝ።
ኦኦኦኦ ይቅር በይኝ ወይዘሮ ሚስት እኔኮ ደስታ ቀልቤን አጥፍቶት ነው ብዬ አቀፍኳት ።
ተሸክሚያት አይኗን አየሁት አየችኝ አሁንኮ ፍቅረኛሞች ሆነናል አትስመኝም እንዴ አለች።
አረ እኔ አፍራለሁ አልኳት ከት ብዬ እየሳኩ
ሳቄ ተጋብቶባት መሰለኝ እሷም ሳቀች።
ግን ዛሬ አልሰማህም አሁን ትስመኛለህ አትስመኝም እእ ወይስ እንደለመድኩት ላኩርፍ አለችኝ።
አይ እንግዴ እንዳትጨማለቂ ካኮረፍሽ አለቀልሽ መቼም ይቅር አልልሽም አልኳት።
ጥሩ እንደውም አውርደኝ ድሮም እኔ ነኝ ጥፋተኛ ካንተጋ ፍቅር ፍቅር ማለቴ አለችኝ።
አፈጠጥኩባትና ሳታስበው ሳምኳት
በቃ አሁን ደስ አለኝ በቃ እንግባ ብርዱ እጄን እየተሰማኝ ነው አለችኝና ይዣት ገባሁ ።
በር ላይ ስደርስ አወረድኳትና ደግፌ ይዣት ገባሁ።
አቶ ሳሙኤል በረንዳ ላይ እጃቸውን በደረታቸው አድርገው ቆመው ይንጎራደዳሉ።
ምነው ቆያችሁኮ ብዙ መራመድኮ አልነበረብሽም ለማንኛውም ቶሎ ከብርድ ላይ ግቡ አሉና ገቡ።
ተያየንና ተከትለናቸው ገባን።
በነጋታው አቶ ሳሙኤል ትናት ያልጨረስኩት ጉዳይ አለኝ እስካልተያዘና እስር ቤት እስካልገባ ድረስ አርፌ አልቀመጥም ብለው በሌሊት ሄዱ ።
እኛ ቁርሳችንን በላላንና እናቴና እህቴ ተያይዘው ወደገበያ ሄዱ ።
አባቴ እኔና ማሂ ብቻ ቀረን።
ካባቴጋ እጇን እየፈታንላት ድጋሜ እያሰርንላት ማፍታታት ጀመርን።
አባቴም ደፈር እያደረገ አበረታታትና የተወሰነ ሳይታሰር እንዲቀመጥ ለማንቀሳቀስ እንድትሞክር አደረጋትና ተመስገን የኔ ልጅ በቅርቡ ይሄ ሁሉ ተፈቶልሽ እንደሚስተካከል ተስፋ አደርጋለሁ አላት።
እኔም ተስፋ አደርጋለሁ ወደስራዬ ወደቀድሞ ህይወቴ መመለስ እፈልጋለሁ በስማም አመት የታመምኩ ያህል ነው የተሰማኝ አለች እጇን እያየች።
ማሂ ቀን በቀን እጇ እየተሻላት አቶ ሳሙኤልም ከአዲስ አበባ ሀዋሳ ቀን በቀን እየተመላለሱ ሲያስታምሟት እናቴም እንክብካቤዋን እንዳጧጧፈችው እኔና ማሂም ፍቅቅሮሻችንን በሚስጥር ዋጥ አድርገን ይዘን ቀናቶች ተቆጦሩ።
ማሂ እጇ ሳይታሰር መንቀሳቀስ ጀመረች ልብሷን በራሷ መቀየር መታጠብ ቻለች።
እቃ ማንሳትና ማስቀመጥ ብቻ ነበር ትንሽ አዳጋች የሆነባት ።
ሀሙስ ቀን ነበር ወደ ምሳ ሰአት አካባቢ እናቴና ማሂ እየተጨዋወቱ እናቴ ምሳ እየሰራች ማሂ በወሬ እያገዘቻት እኔ ከእናቴ ስር ስር እያልኩ እያሽቃበጥኩ
ማሂ እናቴን ፈገግ ብላ አየቻትና እኔ ግን ፈጣሪ ይቅር ይበለኝ እንጂ ምናለ ድጋሜ በታመምኩ እያልኩ ነው አለቻት።
እናቴ ድንግጥ ብላ በስማም የኔ ልጅ ምነው ለምን እንደዛ አልሽ ከዛ ሁላ ልብስ ለመቀየር እንኳን ስቃይሽን የበላሽበትን ጊዜ ባሳለፈልሽ ምነው ባልተሻለኝ ትያለሽ?? አለቻት
አደለምኮ እንክብካቢያችሁ ፍቅራችሁ በቃ ይሄ ምግብ ስንበላ ስብስብ ብለን ብዙ ሆነን ምንበላው ነገር አባቴ ዛሬ አዲስ አበባ ሄዶ ነገ እስኪመጣ ምናፍቀው ነገር አረ ሁሉም ነገር ነው ደስ የሚለው ህመሜን እንድናፍቅ ነው ያደረጋችሁኝ አለች።
አይ የኔ ልጅ አንቺ ደስ ካለሽና ከፈለግሽው ጤነኛ ሆነሽስ ማን ይከለክልሻል ደሞ ገና ይሄ ጅማሪያችን ነው ገና ስንት ሚያስደስቱሽን ቀናቶች አብረን እናሳልፋለን አለቻትና ዞር ብላ እኔን ጠቀስ አደረገችኝ።
እኔም በተራዬ ማሂን ጠቀስ አደረኳትና ሶስታችንም እኩል ሳቅን።
አባቴ የስራ ጉዳይ ኖሮት ከቤት ወጥቶ ለምሳ እስኪመጣ እየጠበቅነው እያለ ለእናቴ ደወለና አቶ ሳሙኤል እየመጡ እንደሆነ ቤቱን ቆንጆ ድባብ እንዲኖረው አድርገን እንድጠብቃቸው ነገረን።
ሶስታችንም በየራሳችን ስራ መስራት ጀመርን እህቴም መጣች ።
ብዙም ሳይቆዩ አቶ ሳሙኤልና አባቴም አብረው መጡ።
ማሂ እየሮጠች ወጣችና ያባቷ ትከሻ ላይ ተጠመጠመች።
እነሱም በደስታ ተሞልተው እየተፍለቀለቁ ነበር።
እኔ በረንዳ ላይ ቆሜ ወደቤት እስኪገቡ እየጠበኩ ምነው ምን ተገኝቶ ነው እንደዚህ ደስታ ያሰከራችሁ አልኳቸው ፊታቸው ላይ የማየው ደስታ እየተጋባብኝ።
አቶ ሳሙኤል ፈገግ አሉና ና እቀፈኝ ልጄ ጠላቴን ልክ አስገብቼው መጣሁ ሳሙኤልንና የሳሙኤልን ልጅ መንካት የሚያስከፍለውን ዋጋ አሳየሁት እያሉ መጥተው አቀፉኝ።
ማሂ እየጮኸች ተያዘ እንዳትለኝ አባቴ እኔ አላምንህም አለች።
እመኚኝ ልጄ መያዝ ብቻ አደለም እድሜ ልኩን የሚፀፀትበትን ቅጣት ነው የሰጡት አሉን ።
እኔና ማሂም በደስታ ተቃቀፍን አባቴም አያችሁ ለዚህ ነው ቤቱን አሳማምራችሁ ጠብቁን ያልኳችሁ አለን።
ሁላችንም ተያይዘን ወደውስጥ ገባን ለእናቴም ለእህቴም ነገርናቸውና ደስታችንን አጋራናቸው።
አቶ ሳሙኤል ቁጭ ሳይሉ በቆሙበት
እንግዲህ ዛሬ ይሄንን ደስታ ምክንያት በማድረግ ማሂ ልጄም እንደዚህ ተሽሏት ስትቦርቅ ማየቴንም አስመልክቶ ትልቅ የቤተሰብ ፕሮግራም እንዲኖረን አስቢያለሁ።
እና እንደለመድነው እቤት ገዝተን መጥተን አርደን እዚሁ ከምናከብር ለምን እንደቤተሰብ ወጣ አንልም እራት ለምን ውጪ አንበላም ዛሬ በቃ የኛ ቤተሰብ ቀን እናድርገው አሉ።
ሁላችንም በደስታ ተስማማን እህቴ ግን ባሌ ሳይመጣ ንቅንቅ አልልም ካለሱ ከሆነ እኔን ተውኝ አለች።
አባቴ እያያት
አይ የኔ ልጅ ታኮሪኛለሽኮ ሚስት ባሏን በዚህ ልክ ስትወድና ስታከብር ደስ ይላል በደስታሽም በሀዘንሽም ቀን እሱን ካሰብሽ በቃ ይሄን ትዳር እግዚአብሔር ይጎበኘዋል አላት።
እህቴም እቅፍ እያደረገችው ካንተና ከናቴ ነው የተማርኩት አባቴ አለች።
✎ክፍል 40 ነገ ማታ 2:30 ይቀጥላል♥️ ቶሎ እንዲ🀄️ጥል LIKE♥️ እና Share አድርጉ።
ይ🀄️ላ🀄️ሉን
https://t.me/+4dGFaH_mUnExZjg8
https://t.me/+4dGFaH_mUnExZjg8
💝የዩቲዩ ገፃችን💝
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333