ፅጌሬዳ
ክፍል 40
ስራ ጨራርሼ ምሳ ሰአት ላይ ሄድኩኝና ምሳ በላን በዛው አብረን ከማሂጋ ልጅቷ ወደምትኖርበት ጎዳና ሄድን አገኘናት እያጨሰች ነበር።
ማሂን ስታያት ሲጋራውን በፍጥነት ጣለችውና ወደኛጋ መጣች ።
አቀፈቻትና ሰላም አለቻት።
ለአንድ ጉዳይ ፈልጌሽ ነበር ማለቴ የስራ ጉዳይ ነው ከኔጋ አብረን መስራት ከቻልን ብዬ አስቤ ነበር ከዚህ በፊት ስለራስሽ የነገርሽኝን አስታውሼ ይሄንን እድል እንደምትጠቀሚበት ስለማምን ነው አለቻት ።
ልጅቷ በደስታ ተሞልታ እሺ አለችና ስለስራው ጠየቀቻት።
ማሂ ወደ መኪናው አስገባቻትና ስለስራው ነገረቻት እና ሰው ፊት አቀራረቧ እንዲያምር ደና ልብስ እንድትለብስ አብረው ልብሱን መግዛት እንዲችሉ ጠየቀቻት እሺ አለችና አብራን ሄደች ነገ ምሳ ሰአት ላይ ሱቅ እንድትመጣ ሱቁን አሳይተን ልብሱን ሰጥተናት ሄደች።
እኔም ማሂን ተሰናብቼ በፍጥነት እየነዳሁ ወደ አቶ ሳሙኤልጋ ሄድኩ።
በነጋታው ልጅቷ በተባለችበት ሰአት ሱቅ መጣች ።
ትንሿን ጠቅ ጠቅ ስልክ ሰጥታ የሰዎችን ስልክ እና ቦታውንም ፅፋ 5 እቃዎችን ሰጥታ ለእያንዳንዱ እቃ የሚከፈላትን ብር ሰጥታ መልካም እድል ተመኝታላት ላከቻት።
አይገርማችሁም አንዳንድ ተራ ሰዎች ለማደግ ለመቀየር የሚከፈትላቸውን መንገድ እየዘጉ ፈጣሪን ለምን አላደረክልኝም እያሉ ያማርራሉ።
ጭንቅላታቸው ጠባቧን የክፋቱን መንገድ ብቻ ነው መመልከት የሚችልው እግራቸው ስራ ካለው መሬት ውጭ አርቀው የወደፊቱን መመልከት አይችሉም ።
ልጅቷም ከነዛ ጠባብ አስተሳሰባቸው ኑሯቸውን ካሽቆለቆላቸው ሰዎች ውስጥ አንዷ ነበረችና ማሂ የሰጠቻትን እቃ እና ስልክ ይዛ ጠፋች።
እቃውን ብትሸጠው በጣም በእርካሽ ነው ብሩ ዛሬና ነገን ጠጥተው ተዝናንተውበት ከነገወዲያ ባዶ እጇን ልትቀር ትችላለች።
ልቧ ውስጥ ትንሽ የቀረ ርህራሄና ማስተዋል ያለ ብትሆን ኖሮ ከዛሬዋ ትንሽ ብር የነገውን ከማሂ ምታገኘውን ጥቅምና የምትቀይረውን ህይወቷን ታስብ ነበር።
ብቻ ማሂ በጣም ተበሳጭታ ደውላ እንባ እየተናነቃት ነገረችኝ እና ሁለተኛ ዴሊቬሪ ሚባል ነገር እንደማትሰራ በጣም እንደተናደደች የልጅቷ ተግባር በጣም እንዳበሸቃት ነገረችኝ።
እንድትረጋጋ ደጋግሜ ነገርኳትና ከስራ ስወጣ እንደምንገናኝ ነግሪያት ንግግራችን ተቋረጠ።
ቀስ እያልኩ ሳስበው ግን ነገሩ ከሷ በላይ እኔ አናደደኝ።
ብቻ ነገሩን ለማብረድ እራት ጋብዣት ወደቤት ገባን።
በነጋታው አቶ ሳሙኤልን ስራ ቦታ እያደረስኳቸው በአሁኑ እሁድ ማሂን ሰርፕራይዝ እንደምናደርጋት እና እኔም የራሴን እንድዘጋጅ እሳቸውም የራሳቸውን ትልቅ ሰርፕራይዝ እንዳሰቡ ነገሩኝ።
እሺ አልኳቸው ከነገሩኝ ቀን ጀምሮ ማሂን ጣል ጣል ማድረግ ጀመርኩ ማታ በራሷ እንድትመጣ ጠዋትም እንቸኩላለን እያልን ቀድመናት መውጣቱን ተያያዝነው።
እሁድ ደረሰ የገዳም ጉዞ እንዳለብን ነግረናት በሌሊት ከቤት ወጣን አቶ ሳሙኤል ቀድመው ቦታ መርጠው ሁሉንም ሚሰሩትን ልጆች አናግረው ጨርሰው ነበርና ስራውን ከጠዋት ጀመርን ማሂ እሷን ጥለን መሄዳችን አስገርሟት ነበር።
ቀኑን ሙሉ እየደወለችልኝ ስልክ አላነሳ አልኳት ።
የኔ ቤተሰቦች ሁሉም እየመጡ ነበርና ወደ 9 ሰአት አካባቢ ደረሱ ሁላችንም ተሰባሰብን አባቴ ጠጋ አለና ልጄ እያላበህኮ ነው ቆፍጠን በል እንጂ አለኝ አረ አባቴ ገና መች አየህና ስትመጣማ ምን እንደምሆን አላውቅም አልኩት።
እየጨራረስን ስንመጣ አቶ ሳሙኤል ለማሂ ደወሉና እኔ ወደሀዋሳ እንደሄድኩ እሳቸው ቶሎ ስለተመለሱ ውጪ እራት ሊጋብዟት እንዳሰቡ ቆንጆ የእራት ልብስ ለብሳ እንድትመጣ ነገሯት።
ማሂ እንኳን ቆንጆ ልብስ ልበሺ ተብላ እንዲሁም ዘናጭ ናት።
ሁሉም ነገር አልቆ እኔም ልብስ ቀይሬ አቶ ሳሙኤልም ልብስ ቀይረው እሷ እስክትመጣ መጠበቅ ጀመረን የቆምኩበት ቦታ በራሱ እየሸሸኝ ያለ እስኪመስለኝ ድረስ ነበር እየተሰማኝ የነበረው።
ማሂ ደወለችና ልትደርስ እንደሆነና ወጥተው እንዲቀበሏት ለአቶ ሳሙኤል ነገረቻቸው።
የኔ ቤተሰቦች እና አቶ ሳሙኤል የጋበዟቸው ሰዎች ሁሉም መምጣቷን በጉጉት እየጠበቁ ነበር ።
እኔ እንዴት መንበርከክ እንዳለብኝ ሁላ ግራ ገብቶኝ ነበር።
ማሂ ንግስት መስላ እጆቿን የአባቷ እጆች ውስጥ ከትታ በኩራት እየተራመድች ስትመጣ አየኋት።
ከዛን ቡሀላ የማደርገው ሁላ ጠፋኝ እናቴ እጄን ጥብቅ አድርጋ ያዘችኝና ልጄ ምን ሆነሀል ወደራስህ ተመለስ እንጂ አለችኝ ለራሷ እየተናነቀ ያስቸገራትን እንባ ለመደበቅ እየሞከረች።
ማሂ በጭራሽ እንዳልጠበቀች ግልፅ ነው ከታች መጥተው ልክ ቀና ስትል ስታየን መጀመሪያ ለሷ የተዘጋጀ አልመሰላትም ይሁን ወይ ምን ይሁን አላቅም ብቻ ዝም አለች ወደ ።
ድንገት ከእንቅልፉ እንደነቃ ሰው እኔን ስታየኝ ወደታች ፊቷን አዙራ ቆመች እኔ ሳያት ነገር አለሙ ሁላ ዞሮበኝ በእግራ እግር ይሁን በቀኝ እግር መንበርከክ ያለብኝ ግራ ገባኝ።
እያላበኝም እንባ እየተናነቀኝ ብዥ እያለብኝም ነበር ብቻ እናቴ በደስታ ስታነባ እያየኋት ።
ማሂ ወደኔ ለመምጣት ፈራች አባቷ እየጎተቱ በሚመስል መልኩ ሊያመጧት ቢሞክሩም እጇ እየተንቀጠቀጠ ሰውነቷ መራመድ አቅቶት ነበር።
አጠገቤ ስትደርስ ገና ታገቢኛለሽ የሚለው ቃል ካፌ ሳይወጣ ቀድማ እጇን ዘረጋች።
ቆይ ይጠይቅሽ እንጂ ብለው አንባረቁባት እሷ የሚንቀጠቀጠውን እጇን ለመመለስ እየሞከረች ከተንበረከከ ጠየቀኝ ማለት አደል አለች።
እኔ ታገቢኛለሽ ወይ የሚለውን ቃል ለማውጣት ምጥ ሆነብኝ ቃላቶቹ ካፌ ላይ ተሰወሩ።
እንደምንም ብዬ ታገቢኛለሽ አልኳት አዎ አለች እጇን እየዘረጋች ሁሉም በጩኸትና በጭብጨባ ደስታቸውን ገለፁ ከተንበረከኩበት ተነሳሁና ጭምቅ አድርጌ አቅፊያት ማልቀስ ጀመርኩ።
እሷም ከኔጋ መነፋረቁን ተያያዘችው።
እኔ ሚያስለቅሰኝ ለካ እንደዚህ ቤተሰብ ፈቅዶ ወዶ በሰው መሀል ተንበርክኬ የኔ የምላትን ሴት ለጋብቻ መጠየቅ እችላለሁ ወይ የሚለው ነበር።
እናቴ ልብሷ እስኪበሰብስ ታለቅሳለች።
የሷንና የማሂን ለቅሶ ሳይ ደሞ ጭራሽ ባሰብኝ አቶ ሳሙኤል እንባቸውን ዋጥ አደረጉት ደም ስራቸው አስኪወጣጠር ድረስ ነበር ዋጥጥጥ ያደረጉት።
✎ክፍል 41 የመጨረሻው ክፍል ነገ ማታ 2:30 ይቀጥላል♥️ ቶሎ እንዲ🀄️ጥል LIKE♥️ እና Share አድርጉ።
ይ🀄️ላ🀄️ሉን
https://t.me/+4dGFaH_mUnExZjg8
https://t.me/+4dGFaH_mUnExZjg8
💝የዩቲዩ ገፃችን💝
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333