ድጋሜ ሌላ መልእክት።
አለመኖሬን ማስተዋልህ ገርሞኛል እኔኮ ማታ ማታ እዛ ስቆም ብርድ መቶኝ ታምሜ ተኝቼ ነበሮ ከስራም ተባረርኩ ታምሜ ብዙ ቀን በመቅረቴ አባረሩኝ።
በጣም ከፍቶኝ ነበር መልእክትህን ሳየው ልቤ እንዴት እንደመታ
ይላል።
መልእክት ተከታታይ ስትልክ ደበረኝና ደና ደሪ ብዬ ላኩላት።
ደና ደር ከቻልክ ነገ ስራ ከሌለህ እንገናኝ እኔ ማታ መጥቼ እንዳልጠብቅህ ድጋሜ በሽታዬ ይነሳብኛል አለችኝ።
ሲመቸኝ አሳውቅሻለሁ በቃ ድጋሜ መልእክት እንዳትልኪልኝ ብዬ ላኩላት።
በዛው አመረረችና ለሳምንት ያህል ዝም ስትለኝ ድጋሜ በኔ ምክንያት ታማ ይሆን እንዴ ብዬ ሲጨንቀኝ ነገ ቅዳሜ ስለሆነ ከሰአት ስራ አንገባም ከሰአት ላግኝሽ ብዬ መልእክት ላኩላት እሺ ስንት ሰአት አለችኝ 8 ሰአት ብዬ መለስኩላት።
በነጋታው 6.30 ሲል ስራ ቦታህጋ መጥቻለሁ እስክትወጣ እየጠበኩህ ነው ብላ ላከችልኝ።
ስምንስት ሰአት እንደተቀጣጠርንና አሁን ለምን እንደመጣች ጠየኳት።
አይ የምር ልታገኘኝ መሆኑን ስላላመንኩ እዚህ ተቀምጬ ልጠብቅህ ብዬኮ ነው ሀሰብ እንዳትቀይር ፈራሁ ችግር የለም እስከ ስምንት ሰአት እጠብቅሀለሁ ብላ መለሰችልኝ።
ሳቄ መጣ ያማታል እንዴ ይቺ ደሞ ከሁሉም የባሰች ናት ብዬ ከራሴጋ አወራሁና ልብሴን ቀያይሬ ተጣጥቤ ወጣሁ እዛው ቅርብ የነበረ ቤት ይዣት ሄድኩ ፊት ለፊት ለፊት ለፊት ተቀመጥን አይን አይኔን ስታየኝ እኔም ትኩር ብዬ አየኋት።
በጣም ቆንጆ ናት ድርብ ጥርስም አላት ፀጉሯም የራሷ ነው በዛ ላይ በጣም እረጅም ነው በውስጤ እሷን እያደናነኩ ለማውራት ግን ጅንን አልኩባት።
በዛ መሀል አስተናጋጇ መጥታ ምን ልታዘዝ አለችኝ እኔ ምንም አልፈልግም አልኳት እሷ ግን አረ ምሳኮ አልበላሁም አትበላም እንዴ አለችኝ
ውጭ ምግብ በልቼ እንደማላቅ ነገርኳት እሺ በቃ እኔም አልበላም አመሰግናለሁ አለች።
ያምሻል እንዴ አሁን ምሳ አልበላሁም አላልሽም መልሰሽ አልበላም ማለት ምን ማለት ነው አልኳት።
አይ እኔኮ አብረን እንበላለን ብዬ አስቤ ስለመጣሁ ነው አሁን ግን በቃኝ አልበላም አለች።
ለማንኛውም ፈጣሪ ያመመሽን ህመም ያርቅልሽ ደና መሆንሽን ለማወቅ ነው ዛሬ የቀጠርኩሽ በኔ ምክንያት የታመመሽ መስሎኝ ጥሩ ስሜት ስላልተሰማኝ ነው ደና ከሆንሽ ደና ሁኚ በቃ ድጋሜ እንዳትደውይ እኔም መልእክት አልክልሽም በዚህ ሰአት ስራዬ ላይ ማተኮር ነው ምፈልገው አንቺ ደሞ ነፃነቴን እያሳጣሽኝ ነው ብያት በተቀመጠችበት ጥያት ወጣሁ።
አልተከተለችኝም መኪና ውስጥ እየሄድኹ ግን ከራሴጋ ክርክር ጀመርኩ አንዱ ልቤ ደግ አደረክ ይለኛል ሌላኛው ልቤ ደሞ ልክ አላደረክም ወንድ የሆንክ መስሎህ ነው ይለኛል
ይቀጥላል...
✎ክፍል 3 ነገ ማታ 2:30 ይቀጥላል♥️ ቶሎ እንዲ🀄️ጥል LIKE♥️ እና Share አድርጉ።
ይ🀄️ላ🀄️ሉን
https://t.me/+4dGFaH_mUnExZjg8
https://t.me/+4dGFaH_mUnExZjg8
💝የዩቲዩ ገፃችን💝
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333