Forward from: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ሲዩጢ፣ የመውሊድ ደጋፊዎች ሌላኛው ምርኩዝ
~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~~
የመውሊድ ደጋፊዎች ለዚህ ቢድዐቸው ከሚያጧቅሷቸው “ጠንካራ ማስረጃዎቻቸው” ውስጥ አንዱ “እነ ኢብኑ ሐጀርና እነ ሲዩጢኮ ደግፈውታል” የሚል ነው። ይሄ ወይ ሞኝነታቸውን ወይ አታላይነታቸውን ነው የሚያሳየው። ምክንያቱም የዑለማእ ንግግር ማብራሪያ ወይም አጋዥ ሆኖ ቢቀርብም በእንዲህ አይነት ጉዳይ ላይ ከሌሎች ዑለማዎች ንግግር በተለየ ማስረጃ የመሆን አቅም የለውምና። ሌላው ቀርቶ የሚጠቀሱት ዑለማዎች ከነ ኢብኑ ሐጀር፣ ከነ ሲዩጢ፣ ... የበለጡም፣ የቀደሙም ቢሆኑ እንኳ። ያለበለዚያማ ሌላውም ወገን ዑለማእ ያጣቅሳልኮ! በዚህን ጊዜ ዳኛው ምን ሊሆን ነው? አንዳንዶቹ ሲበዛ ሞኞች ናቸው። “የኛ ዓሊም ከናንተ ይበልጣሉ” አይነት የልጅ ፉክክር ውስጥ ይገባሉ። በዑለማእ መካከል ደረጃ የሚመድበው ጃሂል አይደለም። ደግሞም መረጃ ያለው በቁርኣን፣ በሐዲሥ፣ በሰለፎች ኢጅማዕና በጤናማ ቂያስ ውስጥ ነው። በነዚህ ውስጥ ደግሞ ለመውሊድ ድጋፍ የሚሆን ምንም ማስረጃ የለም። ይልቁንም ተቃራኒው ነው ያለው።
እርግጥ ነው ለመውሊድ ድጋፍ ከሰጡ ዓሊሞች ውስጥ አንዱ ሲዩጢ ናቸው። እንዲያውም መውሊድን አጥብቆ በሚኮንነው የፋኪሃኒ ሪሳላ ላይ ምላሽ ሰጥተዋል። ይሄ ምላሽ (ረድ) የመውሊድ ደጋፊዎችን ሲያስፈነድቅ፣ በተጋነነ መልኩ ሲሰቃቅሉት ማየት የተለመደ ነው። ሐቂቃው ግን፦
1. ምላሻቸው ውሃ አያነሳም!
የሲዩጢ ምላሽ ሚዛናዊ ሆኖ ለተመለከተው የፋኪሃኒን ብርቱ ሂሶች የሚያነቃንቅ አይደለም። “መውሊድን የጀመረው ፍትሃዊና ዓሊም ንጉስ ነው”፣ “የፈለገውም ወደ አላህ መቃረብ ነው”፣ “ኢብኑ ዲሕያም ወዶለታል”፣ “ለዚህም ሲል ኪታብ ፅፎለታል”፣ “ቢድዐ ለሁለት ይከፈላል”፣ “ለአምስት ይከፈላል” እና መሰል ብዥታዎችን ማንሳት የሚያስፈነድቅ ሳይሆን የሚያሸማቅቅ ምላሽ ነው። ደግሞ ከመቼ ጀምሮ ነው የንጉሳን ድርጊት በሙግት ላይ ማሳመኛ ሆኖ መቅረብ የጀመረው?! አቡል ሙዞፈር አሰምዓኒ “የአህሉ ሱና መታወቂያ መልካም ቀደምቶችን መከተልና ቢድዐና መጤ የሆነን ነገር መተው ነው” ይላሉ። [አልኢንቲሷር ሊአስሓቢል ሐዲሥ፡ 31] ጀማሪ ነው በሚባለው ንጉስ ፍትሃዊ መሆን አለመሆን ላይ፣ የመውሊድ ድግሱን አድንቆ ኪታብ የፃፈው ኢብኑ ዲሕያ ታማኝ መሆን አለመሆን ላይ ብዙ ማለት ይቻል ነበር። ግን የሚቀይረው እውነታ ስለሌለ ይህንን ጉዳይ አንስቼ ፅሁፌን አላስረዝምም።
2. ዐቂቃና መውሊድን ምን አገናኘው?
ምንም ግንኙነት የሌለውን ዐቂቃ ጋር የተገናኘውን አወዛጋቢ ሐዲሥ ለመውሊድ ማስረጃ ማድረጋቸውን በተመለከተም ሸውካኒ እንዲህ ሲሉ ነበር የሰላ ሂስ የሰነዘሩባቸው፦
“ሲዩጢ እንዳደረገው ‘ነብዩ ﷺ ከነብይነታቸው በኋላ ለራሳቸው ዐቂቃ አውጥተዋል’ የሚለውን ሐዲሥ መጠቀሙ ግን ቢድዐን የማፅናት ፍቅር እንዲህ አይነት ጥፋት ላይ እንደሚጥል ከሚያሳዩ አስገራሚ ነገሮች ውስጥ ነው። በተጨባጭ ሲታይ የመውሊድ ፈቃጆች ከከልካዮቹ ጋር ሲነፃፀሩ ጥቂቶች ከመሆናቸው ጋር ለምግብና ለዚክር ብቻ በሚል መስፈርት ካልሆነ በስተቀር እንደማይቻል ተስማምተዋል። ለብዙ ጥፋቶች መዳረሻ እንደሆነ ደግሞ ይሄው አሳውቀንሃል። ይህን ከግምት በማስገባት ላይ አንድም አይፃረርም። ዛሬ የሚከሰተው የዚህ አይነቱ (ጥፋቱ የበዛበት) መውሊድ ግን በወጥ ስምምነት (ኢጅማዕ) የተከለከለ ነው። አጀንዳው የፈቃጆቹን ንግግሮችና መልሶቻቸውን ያጠቃለለ ሰፋ ያለ ስራ የሚፈልግ ቢሆንም ለጊዜው እዚህ ላይ ይበቃናል።” [አልፈትሑ ረባኒ፡ 2/1087-1099]
3. የሲዩጢ ፍቃድ በጣም የተገደበ ነው!
የሲዩጢ ስራ አሁን ላሉ የመውሊድ ድግሶች ድጋፍ የመሆን አቅም የለውም። ለምን? ይህንን የሲዩጢን ንግግር ተመልከቱ፡-
“ሰዎች ተሰባስበው ከቁርኣን የተወሰነ ቢቀሩ፣ ስለ ነብዩ ﷺ ሁኔታ አጀማመርና ሲወለዱ የነበሩ ተአምራትን የሚያወሱ ዘገባዎችን ቢያወሱ ከዚያም ማእድ ቀርቦ ተመግበው ቢመለሱና በዚህ ላይ ምንም ካልጨመሩ ይሄ ባለቤቱ የሚመነዳበት ከመልካም ቢድዐ ነው።…” [አልሓዊ፡ 1/220-221]
“ቢድዐ ነው” ማለታቸውን አስምሩበት። ከዚያ ባለፈ አሁን ያለው መውሊድ እና ሲዩጢ የሚገልፁት መውሊድ እጅጉን የተራራቁ ናቸው። እሳቸው “በዚህ ላይ ምንም ካልጨመሩ” እያሉ ነው። ዛሬ ግን ሽርኩ፣ ብልግናው፣ ሌሎችም ኮተቶች ይቅሩና በድቤ፣ በጭብጨባና በውዝዋዜ የመስጂድ ክብር መደፈሩ ብቻ በቂ ጥፋት ነው።
4. እንደ ሲዩጢ ፍርድ ቢሆን ዱላ ነበር የሚገባችሁ!
ለመውሊድ ድጋፍ የምታጣቅሷቸው ሲዩጢ በመስጂዶች ውስጥ የሚፈፀምን ጭፈራ አስመልክቶ እንዲህ ብለዋል፡-
“ከነዚህም (ከቢድዐዎች) ውስጥ የሆነው በመስጂድ ውስጥ የሚፈፀም ጭፈራ፣ ዘፈን፣ ድቤ መምታት፣ ረባብና ሌሎችም የሙዚቃ መሳሪያዎች ናቸው። ይህንን ከመስጂድ ውስጥ የፈፀመ ሊባረርና ሊደበደብ የሚገባው ጠማማ ሙብተዲዕ ነው። ምክንያቱም አላህ እንዲላቅ ያዘዘውን ነገር እያቃለለ ነውና። … (ከመስጂድ ውስጥ) የዘፈነ ወይም የጨፈረ ቅጣት የሚገባው የሆነ ጠሞ አጥማሚ ሙብተዲዕ ነው።” [ሐቂቀቱ ሱና ወልቢድዐ፡ 191]
ዛሬ ታዲያ ይህንን ተግባር የሚፈፅመው ማነው? ደግሞ ጭራሽ ሳያፍሩ ሲዩጢ ብለው ያጣቅሳሉ። የሲዩጢ ፍርድ በናንተ ላይ ቢፈፀም ኖሮኮ በዱላ እየተደበደባችሁ ነበር ከመስጂድ የምትባረሩት። በዚያ ላይ ይህንን እናንተ የምትፈፅሙትን የሚፈፅምን ሰው “ቅጣት የሚገባው የሆነ ጠሞ አጥማሚ ሙብተዲዕ ነው” እያሉ ነው። ስለዚህ ሑክማችሁን ከሲዩጢ ውሰዱ!
5. ሲዩጢ ማስፈራሪያ አይደሉም!
ምናልባት “እነዚህ ጥፋቶች ከሌሉስ ፈትዋቸው መውሊድ እንደሚፈቀድ አይጠቁምም ወይ?” ከተባለ እኛ መቼ “ሲዩጢ መውሊድ ይፈቅዳሉ ወይስ አይፈቅዱም?” የሚል ክርክር ውስጥ ገባን? ምን ሊጠቅመን ምንስ ሊጎዳን? ግና የሳቸውን ንግግር ከሌሎች በተለየ ገላጋይ ዳኛ የሚያደርገው ምን አለ ነው የምንለው? “እንዴ እሳቸው ማለትኮ ...” እያለ ከሌሎች ዑለማዎች በገዘፈ መልኩ የተለየ ስብእና፣ ንግግራቸውንም እንደ ወሕይ ሊያደርግ የሚዳዳው ካለ በሚገባው ቋንቋ ልናናግረው እንገደዳለን። እንዴት? እራሱም የማይቀበላቸው ከእውነታ ያፈነገጡ ከሆኑ የሲዩጢ ንግግሮች ጋር እናጋፍጠዋልን። ለምሳሌ ሲዩጢ እንዲህ ብለዋል፦
“ሶላቱን በሻፊዒያ መዝሀብ የሰገደ ትክክል ለመሆኑ እርግጠኛ ነው። ከዚያ ውጭ ባሉ መዝሀቦች መሰረት የሰገደ ትክክል በመሆኑ ላይ ውዝግብ አለበት” ይላሉ። [ጀዚሉል መዋሂብ ፊኽቲላፊል መዛሂብ፡ 14] ይሄ ንፁህ ህሊና የማይቀበለው ግልፅ የሆነ የመዝሀብ ጎጠኝነት ነው። የመውሊድ አቋማቸውን እንደ ቁርኣን አንቀፅና እንደ ሐዲሥ ሊቆጥር የሚዳዳው ካለ ይህንን ብይናቸውን ይውሰድ። ሌላም ንግግራቸውን ልጥቀስ፦
“ሩዝ በሚበልላ ጊዜ በነብዩ ﷺ ላይ ሶላት ማብዛት ይወደዳል። ምክንያቱም እሱ የሙሐመድ ﷺ ብርሃን የተቀመጠበት ጌጥ ነበርና። ብርሃኑ በወጣ ጊዜ ተበታተነና ፍሬ ሆነ” ይላሉ። [አልሓዊ፡ 2/49] በዚህም ውስጥ ንብርብር የሆነ ስህተት ነው የሚታየው። ከመሆኑም ጋር ሱፍዮች በሰለፊያ ዑለማዎች ላይ አደብ የቀለለው ንግግር እንደሚናገሩት አድርጌ መናገር አልፈልግም። የዑለማዎችን ትችት አቀርባለሁ። ለምሳሌ ያክል ሲዩጢ በነብዩ ﷺ ወላጆች ላይ የሰጡትን የተምታታ ብይን አስመልክተው ሙላ ዐሊ ቃሪ እንዲህ ሲሉ ነቅፈዋቸዋል፡-