Forward from: ሂዳያ መልቲሚዲያ | ʜɪᴅᴀʏᴀ ᴍᴜʟᴛɪᴍᴇᴅɪᴀ
የመካ እና የመዲና ሱራዎች
ጥቂት ስለ ቁርኣን
~
ቁርኣን ነብያችን ﷺ መካ እያሉ በሚወርድ ጊዜ የሙስሊሞች ቁጥር አናሳ ነበር። አጋሪዎች ብዙሃን ነበሩ። መዲና ውስጥ በነበሩ ጊዜ ደግሞ የሙስሊሙ ኃይል ተጠናክሯል። መካና መዲና የነበሩት ተቃራኒ ኃይሎች በብዛት ከእምነትም፣ ከንቃተ ህሊናም አንፃር ልዩነት አላቸው። በነዚህና መሰል ልዩነቶች የተነሳ በሁለቱ ዘመኖች የወረዱ ሱራዎች ትኩረትና ይዘት ልዩነት ይታይበታል። ይሄ የተወሰነ ሰፋ ያለ ትንታኔ ይፈልጋል።
ከወረዱበት ዘመን አንፃር ሲታይ ከ114 የቁርኣን ምእራፎች ውስጥ 20ዎቹ መደኒያ ናቸው፣ በዘመነ መዲና የወረዱ። 12ቱ ኺላፍ አለባቸው። ቀሪዎቹ መኪያ ናቸው። ስለዚህ ከቁጥር አንፃር አብዛኞቹ የቁርኣን ምእራፎች መካ የወረዱ ናቸው ማለት ነው።
በነገራችን ላይ የመካ እና የመዲና ሱራዎች የሚታወቁባቸው መለያዎች አሉ።
1 - የመካ ሱራዎች፦
⓵ - "ከልላ" (كلا) የሚለው ቃል ያለባቸው ሱራዎች ሁሉ መኪያ ናቸው።
⓶ - ሰጅደተ ቲላዋ ያለባቸው ሱራዎች ሁሉ መኪያ ናቸው። እነዚህም 14 ሱራዎች ናቸው።
⓷ - በመሀላ የሚጀምሩ ሱራዎች ሁሉ መኪያ ናቸው። እነዚህም 14 ሱራዎች ናቸው።
⓸ - በሑሩፉ ተሀጂ (ሑሩፉል ሙቀጠዐ) የሚጀምሩ ሱራዎችም ከበቀረህ እና ኣሊ ዒምራን ውጭ መኪያ ናቸው። በቀረህ እና ኣሊ ዒምራን መደኒያህ ናቸው። ሱረቱ ረዕድ ኺላፍ አለባት።
⓹ - በውስጣቸው "ያ አዩሀ ናሱ" (یَـٰۤأَیُّهَا ٱلنَّاسُ) የሚል ያለባቸው እና "ያ አዩሀለዚነ ኣመኑ" (یَـٰۤأَیُّهَا ٱلَّذِینَ ءَامَنُوا۟) የሚል የሌለባቸው ሱራዎች መኪያ ናቸው።
⓺ - በ "አልሐምዱ" የሚጀምሩ ሱራዎች መኪያ ናቸው። እነሱም አምስት ሱራዎች ናቸው።
⓻ - ከሱረቱል በቀረህ ውጭ "ቀሶሱል አንቢያእ" የያዙ ሱራዎች መኪያ ናቸው።
2 - የመዲና ሱራዎች፦
❶ - በውስጣቸው "ያ አዩሀለዚነ ኣመኑ" (یَـٰۤأَیُّهَا ٱلَّذِینَ ءَامَنُوا۟) የሚል ያለባቸው እና "ያ አዩሀ ናሱ" (یَـٰۤأَیُّهَا ٱلنَّاسُ) የሚል የሌለባቸው ሱራዎች መደኒያ ናቸው።
❷ - ስለ ሙናፊቆች የተወሳባቸው ሱራዎች ሁሉ መደኒያ ናቸው። አልዐንከቡት ስትቀር። እሷ ግን መኪያ ነች። ይሁን እንጂ በውስጧ ስለ ሙናፊቆች የሚያወሳው ክፍል መደኒይ ነው።
❸ - ሑዱድ እር ፈራኢድ የተወሳባቸው ሱራዎች ሁሉ መደኒያ ናቸው።
ምንጭ፦ ዲራሰህ ፊ ዑሉሚል ቁርኣኒል ከሪም፣ ፈህድ አሩሚይ
© IbnuMunewor