የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስራ አመራር ቦርድ ህዳር 25 ቀን 2017 ዓ/ም ባደረገው ስብሰባ ለአምስት የዩኒቨርሲቲያችን ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጠ፡፡ በዚህም መሰረት:-
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስራ አመራር ቦርድ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ''ስለ ራስገዝ ዩኒቨርሰቲ ለመደንገግ በወጣ'' አዋጅ ቁጥር 1294/2015 በተሰጠው ስልጣን መሠረት ነው በዩኒቨርሲቲው ሴኔት የቀረቡለትን የማዕረግ እድገት ያጸደቀው፡፡
👉 ዶ/ር አለማየሁ ተ/ማርያም በስፔሻል ኒድስ ኢጁኬሽን
👉 ዶ/ር አስራት ወርቁ በጂኦቴክኒካል ኢንጂነሪንግ
👉 ዶ/ር መኮንን እሸቴ በፕላስቲክ ሰርጀሪ
👉 ዶ/ር ሚርጊሳ ካባ በፐብሊክ ሄልዝ
👉 ዶ/ር ተባረክ ልካ በዴቨሎፕሜንት ጂኦግራፊ
መስኮች ከላይ ከተጠቀሰው ቀን ጀምሮ ምሁራኑ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ የተሰጣቸው መሆኑን እንገልፃለን፡፡
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስራ አመራር ቦርድ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ''ስለ ራስገዝ ዩኒቨርሰቲ ለመደንገግ በወጣ'' አዋጅ ቁጥር 1294/2015 በተሰጠው ስልጣን መሠረት ነው በዩኒቨርሲቲው ሴኔት የቀረቡለትን የማዕረግ እድገት ያጸደቀው፡፡