Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
ትብብሮችን ማጠናከር ቀጣይነት ያለው ውይይት ይጠይቃል። በ38ኛው የአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ ሁለተኛ ቀን ጎን ከሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሃሙድ ጋር ዳግም በቁልፍ ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተናል። በተጨማሪም የጋና ፕሬዝዳንት ጆን ማሃማን እና የቡሩንዲ ፕሬዝዳንት ኢቫሪስቴ ንዳይሺምዬን አግኘኝቼ የበለጠ ትብብራችንን ማጥበቃችንን ባረጋገጠ ሁኔታ በጋራ እድሎች እና ፈተናዎች ላይ ተነጋግረናል።
የኢትዮጵያ የአለም የንግድ ድርጅት መቀላቀል ቅድሚያ ከምንሰጣቸው ጉዳዮች አንዱ ነው። ከድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ንጎዚ ኦኮንጆ ኢዊአላ ጋር የደረስንበትን ደረሃ እና ቀጣይ ርምጃዎች አስመልክቶ ውይይት አድርገናል። በሀገር በቀል ኢኮኖሚ ሪፎርም ፕሮግራም ካለን እድገት አንፃር ብሔራዊ ጥቅማችንን በሚያስጠብቅ መንገድ ወደ አለም አቀፍ የንግድ ሥርዓት ለመቀላቀል እንሰራለን።
በተጨማሪም ከፕሮፌሰር ጄፈሪ ዲ. ሳክስ ጋርም ተገናኝቼ በተለያዩ የልማት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ተነጋግረናል። የእርሳቸው የቀጠለ ድጋፍ እና ሃሳብ ለኢትዮጵያ የልማት ጉዞ ጠቃሚ ነው።