ዋግ እና "ብርኩተ "
ሰቆጣ : ታኅሣሥ 14/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር በበርካታ ባሕሎች የሚታወቅ አካባቢ ነው። ከባሕላዊ ጨዋታዎች ውስጥ ሻደይ፣ ለውፈረ ለውፈ፣ ቕየ ቕየ እና ሌሎች ባሕላዊ ጨዋታዎች ይገኙበታል።
የአካባቢው ማኅበረሰብ በዋናነት የ"ኽምጣና" ቋንቋ ተናጋሪ ሲኾን አማርኛ እና ትግረኛም ተናጋሪ ናቸው። ዋግ ኽምራ ባሕላዊ ምግቦች እና መጠጦች ያሏት ሲኾን ከእነዚኽም ውስጥ አንዱ የኾነውን የ"ብርኩተ" ምግብ አሠራር ይጠቀሳል።
"ብርኩተ" በስንዴ ዱቄት ወይም በማሽላ ዱቄት ሊሠራ የሚችል ሲኾን በዋናነት ፍየል በማርባት በርሃ የሚውሉ እረኞች ዘንድ የሚዘወተር የምግብ ዓይነት ነው።
እረኞች በርሃ ስለሚውሉ እሳት ለማንደድ የዘመኑን ክብሪት የማግኘት ዕድላቸው ጠባብ ነበር። እናም እንጨት በእንጨት በማጋጨት እሳት የመፍጠር ዘዴን ይከውናሉ።
https://ameco.et/tourism/738/