"ወቅቱን የዋጀ የፖሊስ ተቋም እንዲኖር የጋራ ጥረት ይጠይቃል" ኮሚሽነር ደስዬ ደጀን
የአማራ ፖሊስ በተቋማዊ አገልገሎት አሰጣጡና የለውጥ ሂደቶቹ ዙሪያ በተዘጋጁ ሰነዶች ከአመራሮቹ ጋር መክሯል።
በኮሚሽኑ በልዩ ልዩ የሥራ ክፍሎች ለሚገኙ አመራርና ባለሙያዎች፣ በባህርዳር ከተማና አካባቢው ተመድበው ለሚሰሩ የአድማ መከላከል አመራሮች፣ ለቪአይፒ ተቋም ጥበቃ አመራሮች፣ የሰሜን ጎጃም ፖሊስ መምሪያ አመራሮች በተገኙበት ተቋማዊ የለውጥ ሥራዎቻችን አስመልክቶ እስካሁን በተዘጋጁ አራት ሰነዶች ላይ ውይይት ተካህዷል።
ፖሊስ ዓለም አቀፋዊና ህዝባዊ ተቋም ነው። የሀገራችን በተለይም የአማራ ፖሊስ በዚህ እሳቤ የህብረተሰቡን ፍላጎት ያማከለ ተደራሽ አገልግሎት ለመስጠት ጥረት ቢያደርግም በተደራራቢ ምክንያቶች የታሰበውን ያህል አገልግሎት እየሰጠ አይደለም። አሁን በክልሉ የገጠመው የፀጥታ ችግር ደግሞ የአገልግሎት አሰጣጡን ፈትኖታል። ይህንን ታሳቢ በማድረግ ከአደረጃጀት እስከ የመፈፀም ብቃት ሂደት የተስተዋሉ ችግሮች ዙሪያ ኮሚሽኑ ጥናት አስጠንቷል።
በጥናቱ ግኝቶች መነሻነት የተዘጋጀውን የለውጥ ፍኖተ ካርታ የሪፎርሙን አስፈላጊነት፣ ምቹ ዕድሎች፣ እንዲሁም የሚጋጥሙ ሥጋቶች አስመልክቶ ለውይይቱ በቀረቡ ሰነዶች ላይ ተሣታፊዎች ግልፅ ግንዛቤ እንዲይዙ እና የራሳቸውን ተጨማሪ ሐሳብ አስተያዬቶች በግብዓትነት እንዲሰጡባቸው ተደርጓል።
የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደስዬ ደጀን በውይይቱ ወቅት እንዳሉት ተቋም ለትውልድ ለጋራ አንድነትና ፍትሀዊነት ማረጋገጫ ሆኖ እንዲገነባ እና ወቅቱን የዋጀ የፖሊስ ተቋም እንዲኖር የጋራ ጥረት ይጠይቃል ብለዋል።
የመድረኩ ተሣታፊዎች በበኩላቸው የተጀመረው ውይይት የሪፎርም ሥራውን ካማሳለጥ ባሻገር በተቋም ግንባታ ሊታለፍ የማይገባቸውን ቁልፍ ጉዳዮች የሚያግዝ በመሆኑ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበው በተቻለ መጠን የተሰጡ የግብዓት አስተያየቶችን በፍጥነት አካቶ ወደ ተግባር እንዲገባ ጠይቀዋል።
ተቋሙ በምን ጉዳዮች ለውጥ እዲያደርግ ትፈልጋላችሁ?