በታጣቂዎች በተፈፀመ ጥቃት ንፁሀን ተገደሉ።
በሰሜን ወሎ ዞን መቄት ወረዳ ገበያ ውለው ሀገር አማን ነው ብለው ወደ ቤታቸው በሚመለሱ ንፁሀን ሰወች ላይ በታጣቂ ሀይሎች በተፈፀመ ጥቃት የ2 ሰወች ህይወት ሲያልፍ በ11 ሰወች ላይ ደግሞ የአካል ጉዳት ደርሷል።
ገበያ ውለው ወደ ቤታቸው እየተመለሱ ባሉ ንፁሀን ሰወች ላይ በመቄት ወረዳ አግሪት 05 ቀበሌ ልዩ ቦታው ላይ በታጣቂዎች ቡድን መሪነት ጭካኔ በተሞላበት መንገድ በተፈፀመ ጥቃት የታርጋ ቁጥር ኮድ 3 አማ 11758 አነስተኛ የህዝብ ማመላለሻ መኪና ውስጥ በነበሩ ንፁሀን ሰወች ላይ የሞት እና የአካል ጉዳት ደርሷል።
በጉዳቱም ሴቶች እና ህፃናት የሚገኙ ሲሆን የ2 ሰወች ህይወት ወዲያው ሲያልፍ 11 ሰወች ላይ ደግሞ ከባድ እና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል። የቆሰሉ ሰወችም የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል።