የኮምቦልቻ ከተማ ትራፊክ ፖሊስ ከትራንስፖርት ቢሮ ጋር በመተባበር ከተለያዩ ትምህርት ቤቶች ለተውጣጡ የተማሪ ትራፊክ ፖሊሶች ስልጠና ሰጠ።
የኮምቦልቻ ከተማ ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክ ሃላፊ አቶ ዳንኤል ኃይሌ እንዳሉት የትራፊክ አደጋ እያደረሰ ያለውን ጉዳት ለመቀነስ የሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ተሳትፎ እንደተጠበቀ ሆኖ የተማሪዎች ሚና ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል።
የኮምቦልቻ ከተማ ፖሊስ የትራፊክ ደህንነት ግንዛቤ ማስጨበጫ ክፍል ሃላፊ ኢንስፔክተር ሙሃመድ አደም ትምህርት እና ስልጠናው ስለ ችግሩ የጋራ መረዳትን በመያዝ ለመፍትኤው በትብብር ለመስራት የሚያግዝ መሆኑን አንስተዋል።
የስልጠናው ተሳታፊዎች በበኩላቸው በወሰዱትን ግንዛቤ አግባብ እንደሚሰሩ አሳስበዋል።
በዋና ሳጅን ሙሃመድ አህመድ