ያለሰምሪት ሲንቀሳቀሱ የተገኙ ባጃጆች እና በተለያዩ የሰርቆት ወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የደሴ ከተማ አሰተዳደር ፖሊሰ መምሪያ ገለፀ።
አማራ ፖሊስ ታህሳስ 28/2017 ዓ/ም
የደሴ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ የሰሞኑን በዓላትን አሰመለክቶ በተሰራ ልዩ ክትትል ከሌላ ከተማች የገቡ በህገ ወጥ መንግድ ያለሰምሪት ሲንቀሳቀሱ የተገኙ ባጃጆች እና በተለያዩ የስርቆት ወንጀሎች የተጠረጠሩ ግለሰቦች እና የተሰረቁ እቃዎችን በመግዛት የተጠርጠሩ ግለሰቦችን በልዩ ኦፕሬሽን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የደሴ ከተማ አሰተዳደር ፖሊሰ መምሪያ ሃላፊ ኮማንደር አበባው አሻግሬ ገለፀዋል።
እንዴ ኮማንደር አበባው ገለፃ በደሴ ከተማ ከሌሎች አካባቢዎች ወደ ከተማዋ በመግባትና በስርቆት የተሰማሩ ያለ ሰሌዳ የሚያሽከረክሩ፣ስምሪት የለላቸው፣ አንፀባራቂ የደንብ ልብስ ሳይለብሱ የሚያሽከረክሩ በድምሩ ከ28 በላይ የሶስት እግር ተሽከርካሪዎችና በተለያዩ የስርቆት ወንጀሎች እና በተለይ የተሰረቁ እቃዎችን በመግዛት የተጠረጠሩ 34 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ተናግረዋል።
ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበራከተ የመጣዉን ስርቆት ወንጀል ለመከላከል መምሪያው እቅድ በማውጣት እና የተለያዩ የኦፕሬሽን ስራዎች ሲሰራ መቆዬቱን እና በዚህ ልዩ ኦፕሬሽንም በቁጥር ከ7 በላይ የተንቀሳቃሽ ስልኮች፣ 3 ቴሌቪዥኖች እና ሌሎች በርካታ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችች መያዛቸውን በመግለፅ ምርመራ እየተጣራ መሆኑን ኮማንደሩ አብራርተዋል።
የከተማውን ማህበረሰብ ሰላም ለማስጠበቅና ከየትኛውም ዘርፊያና ስርቆት ለመከላከል የከተማው ፖሊስ አሁንም በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ተገልፆል።
የከተማው ነዋሪ አሁንም በማንኛውም ጉዳይ አጠራጣሪ ነገሮችን ሲመለከተ ጥቆማውን ለከተማው ፖሊስ በመስጠት የተለመደ ትብብሩን እንዲያደርግ ኮማንደር አበባው ጥሪ አቅርበዋል።
መረጃው፦ደሴ ከተማ አሰተዳደር ፖሊሰ መምሪያ ህዝብ ግንኙነት ነው።