በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ወረዳ የሠላምን ጥሪ የተቀበሉ ታጣቂዎች እጅ ሠጥተዋል።
የሰሜን ጎንደር ዞን ኮማንድ ፖሰት ሰብሳቢ ሜጄር ጄኔራል አማረ ገብሩ እንደገለፁት በአካባቢው ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ እና በህብረተሰቡ ላይ ችግር ሲፈጥሩ የቆዩ ቡድኖች የመንግስትን የሠላም ጥሪ በመቀበል እጃቸውን እየሠጡ ይገኛሉ።
የመከላከያ ሠራዊቱ ከአካባቢው የፀጥታ ሀይል ጋር በመቀናጀት ባደረገው የሚያቋርጥ ስምሪት ቡድኑ ላይ ተከታታይ እርምጃ በመወሰዱ አካባቢው የሰላም ቀጠና ሊሆን መቻሉንም አሥረድተዋል።
ሠራዊቱን በማሰማራትና ጠላት እሰከሚሸሸግባቸው በርሃዎች ዘልቆ በመግባት በተወሰደው ተከታታይ እርምጃ አመርቂ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን ሜጄር ጄኔራል አማረ ገብሩ ገልፀዋል።
ህብረተሠቡም ለሰላም በመምከር በተሳሳተ አጀንዳ ወደ ታጣቂ ቡድን የተቀላቀሉት ወደ ሠላም እንዲመለሱ ሠፊ ሥራ መሥራቱን የገለፁት ጄኔራል መኮንኑ አሁንም በተሳሳተ መንገድ ጫካ የሚገኙትን መምከርና ወደ ሠላም መመለስ እንደሚገባ አመላክተዋል።
እጅ የሰጡት ታጣቂዎች የሰጡት ሃሳብ ከግጭት እና ከጦርነት የሚገኝ ትርፍ አለመኖሩን ተገንዝበው የሠላም አማራጭን መቀበላቸው ለክልሉ ህዝብ ሠላም ያላቸውን ቁርጠኝነት ያመለክታል።
ወደ ሠላም የተመለሱ ታጣቂዎች በሀሰት ፕሮፖጋንዳ ተታለው ወደ ጫካ እንደገቡ ገልፀው ሲበድሉት የቆዩትን ህዝብ ለመካስ ከፀጥታ ሃይሉና ከህብረተሰቡ ጋር በቅንጅት እንደሚሠሩ ተናግረዋል።
ምንጭ ፦የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት