ህገ-ወጥ መድኃኒት ሲያዘዋውር የተገኘው ግለሰብ መቀጣቱን ፖሊስ ገለፀ።
ባህርዳር፦ጥር 5 ቀን 2017 ዓ.ም (አማራ ፖሊስ ሚዲያ)
በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ሰሃላ ሰየምት ወረዳ 06 ቀበሌ ታኅሳስ 24 ቀን 2017 ዓ/ም አዲሡ አዳነ ወረታ የተባለ ግለሰብ አዳኝነቱና ፈዋሽነቱ ያልተረጋገጠ ህገወጥ መድሀኒት በ2011 የወጣውን የምግብና መዳኃኒት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1112/2011 አንቀፅ 2/44/ እና አንቀፅ 67/4/ስር የተመለከተውን በመተላለፍ በህገወጥ መንገድ ለማዘዋወር ሲሞክር በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል።
የወረዳው ፖሊስም ምርመራውን በማጣራት መዝገቡን ለወረዳው ዐቃቤ ህግ ጽ/ቤት ልኳል።
ክሱ የቀረበለት የስሃላ ሰየምት ወረዳ ፍርድ ቤትም በተፋጠነ የፍርድ ሂደት የግለሰቡን ጥፈትኝነ በማረጋገጥ ጥር 2 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት እሱን ያርማል ሌላውንም ያስተምራል ያለውን በ1ዓመት ከ8 ወር እስራት እና በ3,000(ሶስት ሽህ ) ብር የገንዘብ መቀጮ እንድቀጣ ወስኖበታል ሲል የሰሀላ ሰየምት ወረዳ ፖሊስ ዘግቧል።