የመንግሥትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው በቡርቃ የተሃድሶ ማዕከል ስልጠና የወሰዱ ታጣቂዎች ተመረቁ።
አማራ ፖሊስ፦ጥር 18/2017 ዓ.ም
የመንግሥትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው በቡርቃ የተሃድሶ ማዕከል ስልጠና ሲወስዱ የቆዩት ታጣቂዎች በተሳሳተ መንገድ የበደልነውን ማኅበረሰብ ለመካስ ተዘጋጅተናል ብለዋል።
በክልሉ ከአንድ ዓመት በላይ በዘለቀው ግጭት ታጥቀው ወደ ጫካ የገቡ ታጣቂዎች ወደ ሰላም እንዲመጡ ሕዝብ እና መንግሥት ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪ ሲያቀርቡ ቆይተዋል። በተለያዩ አካባቢዎች ሲንቀሳቀሱ የነበሩ በርካታ ታጣቂዎችም የሰላም ጥሪውን ተቀብለው ወደ ተሃድሶ ማዕከላት መግባታቸው ይታወሳል።
በአማራ ክልል ከሰሜን ወሎ፣ ከደቡብ ወሎ፣ ከሰሜን ሸዋ፣ ከዋግ ኽምራ ብሔረሰብ እና ከኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የነበሩት ታጣቂዎች በቡርቃ የተሃድሶ ማሰልጠኛ ማዕከል በመግባት ስልጠናቸውን አጠናቅቀው ተመርቀዋል።
ታጣቂዎቹ የአማራን ሕዝብ ጥያቄዎች ለማስመለስ በሚል ወደ ጫካ መግባታቸውን ጠቅሰው የተከተሉት መንገድ ግን የተሳሳተ እንደ ነበር አመላክተዋል። በትጥቅ ትግሉ ምክንያት የመጀመሪያው ተጎጂ የክልሉ ሕዝብ በመኾኑ የሰላም መንገድን እንደመረጡም ተናግረዋል።
በስልጠና ቆይታችንም የሕዝብ ጥያቄ በዚህ ሁኔታ እንደማይመለስ ተገንዝበናል ብለዋል። በቀጣይ እስከዛሬ የበደልነውን ማኅበረሰብ ለመካስ ተዘጋጅተናል ያሉት ታጣቂዎቹ የክልሉ መንግሥት ስልጠናውን በማመቻቸት ላደረገላቸው ድጋፍም አመስግነዋል።
የአማራ ክልል ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ኀላፊ ደጀኔ ልመንህ የክልሉን መንግሥት እና ሕዝብ የሰላም ጥሪ ተከትሎ በርካታ ታጣቂዎች ወደ ስልጠና ማዕከል እንዲገቡ እየተደረገ መኾኑን ገልጸዋል።
ስልጠናውን ያጠናቀቁ የቀድሞ ታጣቂዎችም በቀጣይ ወደ ማኅበረሰቡ ሲቀላቀሉ የሰላም አምባሳደር ኾነው እንዲሰሩ የሚደረግ መኾኑን ያነሱት ምክትል ቢሮ ኀላፊው በጫካ የሚገኙ ሌሎች የታጠቁ ወገኖችም የሰላም አማራጭን እንዲቀበሉ ጥሪ አቅርበዋል።
በስልጠናው ማጠቃለያ መርሐ ግብር ላይ የተገኙት በሀገር መከላከያ ሰራዊት የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል አሰፋ ቸኮል በበኩላቸው ሰላምን መምረጥ የታላቅነት መገለጫ መኾኑን ጠቁመዋል።
ሌተናል ጄኔራል አሰፋ ቸኮል በጫካ የሚገኙ ሌሎች ታጣቂዎችም የሰላምን መንገድ መርጠው ለሕዝብ እፎይታ እንዲሰሩ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
#አሚኮ