በሰራባ የስልጠና ማዕከል የመንግሥትን የሠላም ጥሪ ተቀብለው የተሃድሶ ስልጠና ሲሠለጥኑ የቆዩ ታጣቂዎች ተመረቁ።
አማራ ፖሊስ ፦ጥር 18/2017 ዓ.ም
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጭልጋ ወረዳ በሰራባ የስልጠና ማዕከል የመንግሥትን የሠላም ጥሪ የተቀበሉ ከ1 ሽህ 490 በላይ ታጥቀው በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች ወደ ተሃድሶ ስልጠና መግባታቸው ይታወሳል። ስልጠናውን በማጠናቀቅም ተመርቀዋል።
ሰልጣኞቹ ከአንድ ዓመት በላይ በተሻገረው የአማራ ክልል ግጭት ሰባዊ ቀውስና ቁሳዊ ውድመት መድረሱን ጠቅሰው ፤ በድርጊቱም መፀፀታቸውን ተናግረዋል።
የተፈጠረው ግጭት የአማራን ሕዝብ የማይገባ ዋጋ አስከፍሎታል የሚሉት የተሃድሶ ሰልጣኝ ተመራቂዎቹ የአማራ ሕዝብ የሰላም ረፍት እንዲያገኝ የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።
የተበደለውን ሕዝብ ለመካስና ሠላምን ለማረጋገጥ እንሠራለን ብለዋል።
በምረቃው የተገኙት የሀገር ሽማግሌዎችም የሰላም ጥሪን የተቀበሉ ወጣቶች በሰራባ የስልጠና ማዕከል የተሃድሶ ስልጠና ወስደው በመመረቅ ወደ ሠላምና ልማት መመለሳቸው የሚበረታታና ለሌሎች ትምህርት የሚሰጥ ነው ብለዋል።
በስልጠና ማዕከሉ ለተሃድሶ ሰልጣኞች አስፈላጊው አቅርቦት ሲከናወን መቆየቱን ያነሱት የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ትምህርት መምሪያ ምክትል ኃላፊና የስልጠና ማዕከሉ አስተባባሪ ነጋ ብርሃኑ ስልጠናው የሠልጣኞችን አቅም ለመገንባት ያስቻለ መሆኑን ገልጸዋል።
የርእሰ መሥተዳደር ጽሕፈት ቤት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊና የሰራባ ስልጠና ማዕከል አስተባባሪ አበባው አምባዬ የመንግሥትን የሠላም ጥሪ የተቀበሉ ታጣቂዎች የተሃድሶ ስልጠናቸውን በአግባቡ መውሰዳቸውን ገልጸዋል።
አስተባባሪው ሠልጣኞች የክልሉን ሕዝብና መንግሥት መካስ የሚያስችል ተግባር ለመከወን መዘጋጀታቸውንና ለዚህም መተማመን ላይ መደረሱን አስገንዝበዋል።
#አሚኮ