የክርስትና እውነቶች


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Религия


📖መጽሐፍ ቅዱሳዊ📖 የሆኑ መንፈሳዊ ጽሑፎችን የሚያገኙበት ቻናል ነው❗
📲Join/Subscribe📲 ብለው ይቀላቀሉና ቤተሰብ ይሁኑ!👥
↪Share↩ በማድረግም "የክርስትና እውነቶችን" ለወዳጅዎ ያጋሩ!👇
https://t.me/Cchristiantruth

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Религия
Статистика
Фильтр публикаций




ክፍል አራት
#የመኖሪያ_አቅም

ፀጋ እና ሰላም

መኖር ፈልገህ ለመኖር አቅም ታጣለህ ። ሰላም ፈልገህ ሰላም መልሶ ይርብሃል ።በቅድስና ለመኖር ቆርጠህ ሳለ መልሰህ በሰራከው የቀደመ ሐጢያት ትወድቃለህ ። ይህን ነገር አላደርገውም ብለህ ምለህ ተገዝተህ መልሰህ ማትወደውን ስታደርግ ራስህን ታገኛለህ ። ምን ይሻለኛል ? ብለህ ትጠይቃለህ ሰዎች ያለህበት ቦታ ተመችቶህ ያለህበት መስሏቸው ያሙሃል የደላው እያሉ ይናገሩሃል ። የውስጥህን ስብራት ከቶ ማንም አያውቀውም ። ለመውጣት እየታገልክ ነገር ግን አቅም እንዳጣህ ይሰማሃል ።

ዛሬ የምስራች እነግራችኋለሁ የመኖር አቅም የሚሰጥ ስጦታ ተሰጥቶናል ።ይህን ማወቅ ያሳርፋል ።

ጳውሎስ እንዲህ ይላል ።

‹‹ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታችንም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።›› ገላ 1:3

ይህ የተለመደ የጳውሎስ የምኞት አዘል ሰላምታ ነው ፡፡ በተለያዩ ክፍሎች ይህንን ሰላምታ ይጠቀማል ፡፡ በ ሮሜ 1፡7 በ1ኛ ቆሮ 1፡1፡3 ፣2ኛ 1ቆሮ 1፡2 ኤፌ 1፡2 …… ጳውሎስ በመግቢያ ንግግሩ ብቻ ሳይሆን በመልዕክቱ መጨረሻ ላይም ይህንን ቃል በተደጋጋሚ ይጠቀማል ፡፡ በገላ 1፡3 ላይ በእዚሁ መንገድ ሰላም እያለ በመግባት ላይ ሆኖ የፀጋ እና የሰላም መገኛ #ማን እንደሆነም ይነግረናል ፡፡

ይህም አባታችን እግዚአብሄርና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ይለናል ፡፡ ይህ ፀጋ እና ሰላም የአማኞች መተዳደሪያ በጀታችው ጭምር ነው በብራቸው ገዝተው መብላት ያልቻሉ ብዙ ባለ ሃብቶች አሉ በልተውም የማይደሰቱ በሕይወታቸው ደስተኛ ያለሆኑ አሉ ስለለህ ብቻ ሁሉ አይሰምርም አያሳርፍም ፡፡ በእግዚአብሄር ፀጋ የሚኖሩ ግን በጌታችንም ፀጋ እና ሰላም የሚመላለሱ በመሆናቸው የእረፍት ሕይወት ይበዛላቸዋል ።ለእነርሱም ከእነዚህ ውጪ ለመኖር እጅጉን ከባድ እና የማይቻል ነው፡፡ የፀጋው ባለቤት ሁከት በሆነ ሁኔታ እንኳን የራሱን ሰላም እየሰጠ ያረጋጋቸዋል ። አሜን🙏

በእዚህ ክፍል አስገራሚው ነገር የመገኛው ጉዳይ ነው ፡፡ የት ይገኛሉ የሚለው ሌላ ቦታ በመፈለግ እንዳንደክም በእዚህ ክፍል ውስጥ ይመሳል ፡፡ #ከአባታችን_ከእግዚአብሄር_አብና_ከጌታችን_ከኢየሱስ ክርስቶስ ይላል ወደ ሌላ ቦታ በመሄድ የሚገኙ አይደሉም ፡፡ ስፍራቸው እዚህ ነው። የፀጋ እና የሰላም መገኛው ወዲህ ነው ሰው ሌላ ቦታ ቢፈልግ አያገኘውም ፡፡ የፀጋ መገኛ በመለኮት ስር ነው የቀረበ ያገኘዋል።

የዕብራውያን መፅሐፍ ፀሐፊ አማኞች ፀጋ ከፈለጉ ወዴት መምጣት እንዳለባቸው ሲናገር እንዲህ ይላል ፡፡

‹‹ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ እንደ እኛ የተፈተነ ነው እንጂ፥ በድካማችን ሊራራልን የማይችል ሊቀ ካህናት የለንም።እንግዲህ ምሕረትን እንድንቀበል በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ።››
ዕብ 4፡15-16

ይህ ፀጋ ምን ያደርጋል
🔸በሚያስፈልገን ጊዜ ይረዳናል። ነገሮች በሚያስፈልጉን ጊዜ ዞር የሚል በበዛበት በእዚህ ዘመን የአምላካችን እና የጌታ ፀጋ ግን በእዚህ ሰአት ይረዳናል ። ሀሌ ሉያ!!

አቅሙ የደከመ ሰው ካለ አንድ የምስራች አለለት እርሱም ወደ ፀጋው ዙፋን በመቅረብ ይህን የሚረዳ ፀጋ እንዲቀበል መንገዱ ተመረቆ ተከፍቶለታል ፡፡

🔸ይህ ፀጋ መቆሚያ ነው
🔸ይህ ፀጋ መበርቻ ነው ፡፡
🔸ይህ ፀጋ እንደገና መነሻ ድጋፍ ነው ጳውሎስ በሚያምር ቋንቋ እንዲህ ይገልፀዋል ፡፡

‹‹ሰዎችን ሁሉ የሚያድን #የእግዚአብሔር_ጸጋ ተገልጦአልና፤ #ይህም_ጸጋ፥ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን፥ የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል፤››
ቲቶ 2፡11-13

ይህ ፀጋ ተመልከቱት
🔸ሰውን ሁሉ ያድናል ይላል ።
🔸ኀጢያተኝነትን እና አለማዊ ምኞትን ያስክዳል
🔸የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እንድጠብቅ ያግዘናል
🔸ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ደግሞ ያስተምረናል ፡፡

ታዲያ ከእዚህ በላይ ምን ያስፈልገናል?
🔸 ለመዳን
🔸በፅድቅ ለመኖር
🔸ሐጢተኝነትን ለመካድ
🔸የጌታችን የኢየሱስን ክብር መገለጥ ለመጠብቅ ..... ይህ ፀጋ ያስፈልጋል ።

ተወዳጆች በእውነት እግዚአብሄር ይህንን ፀጋ ያብዛላችሁ ይብዛልን ፡፡

አሜን🙏

ይቀጥላል

✍️Girum Difek




ክፍል ሶስት

#ምንጩ_ያልታወቀን_ለማመን_ከባድ_ነው !!

ከእግዚአብሔር ነው ከሰው አይደለም።

🔸ጳውሎስን ማን ሐዋርያ አደረግው?

በምድር ስርአት እንኳ ምንጬ ያልታወቀ ሐብት በመንግስትም በማህበረሰብም ደረጃ ጥርጣሬን ይፈጥራል ፡፡ ከሙስና እና ከተለያዩ ወንጀሎች ጋር ሊገናኝ ይችላል ተብሎ ይታሰባል ፡፡ ምንጩ አይታወቅማ !!

በእዚህም ጉዳይ በጥርጣሬ የታሰበ አካል ካለ የምንጭ ማጣራት ስራ በህግ ባለሙያዎች ይካሄዳል ፡፡ ጳውሎስ ሐዋሪያን የሚያክል ሹመት ከማን ያገኘው ? በእሱ ትምህርት ላይ ህይወታችንን ልንገነባ ስለሆነ ምንጩን ማወቅ እጅግ አስፈላጊ ነገር ነው ፡፡ ለዚህም ነው ጰውሎስ ምንጩን በሚገርም መንገድ የሚጠቅሰው!!!

ያዕቆብ በመልዕክቱ

“በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው፥”
ያዕቆብ 1፥17 እንደሚል ጳውሎስ ወደ ሰማይ አቅንቶ ከላይ ነው ይላል፡፡

ጳውሎስ ማን ሐዋሪያ #እንዳደረገው እና ማን ሐዋሪያ #እንዳላደረገው ይናግራል ሁለቱንም መሳ ለመሳ ይከትባል ።

🔸1ኛ እግዚአብሄር ነው ፤- ኢየሱስ ክርስቶስን ከሙታን ያስነሳው እግዚአብሄርን አብ ሐዋርያ ያደረገኝ ይላል፡፡

🔸2ኛ ሰው አይደለም ፤- ከሰዎች ወይም በሰው አይደለም ፡፡ይህ ማለት ሰዎች ስለፈለጉ አይደለም ተሰብሰበው ሐዋሪያ ያደረጉኝ ሲቀጥልም ደግሞ እግዚአብሄር በሰው በኩል አይደለም ሐዋርያ ያደረገኝ ይላል ።

‹‹በኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታንም ባነሣው በእግዚአብሔር አብ ሐዋርያ የሆነ እንጂ ከሰዎች ወይም በሰው ያልሆነ ጳውሎስ ከእኔም ጋር ያሉት ወንድሞች ሁሉ፥ ወደ ገላትያ አብያተ ክርስቲያናት›› ገላ 1፡1

ሁለት ነገር እናስተውል !!

በሚገርም ሁኔታ ጳውሎስ በመግቢያው ስለ ሐዋሪያነቱ እንዲህ ተናግሮ የሚጀምረው

በእዚህም ዘመን ከእዚህ ምንባብ ማስተዋል ያሉብን ሁለት ነገሮች አሉ ፡፡

🔸1ኛ ከእዚህ ውስጥ ዋነኛው ማወቅ ያለብን ጉዳይ አገልግሎት የሚሰጠው የሚቸረው ፣ ፀጋ የሚሰጠው የሚቸረው ከእግዚአብሄር ዘንድ እንደሆነ ነው ፡፡ ወዳጆች ፀጋ ከላይ ነው ። ቤተ ክርስቲያንም ብትሆን እንኳ ፀጋ አትሰጥም ነገር ግን ቤተ ክርስቲያን ፀጋ ያለባቸው ሰዎች ትለያለች!! የፀጋ ምንጭ ግን እግዚአብሄር ነው ፡፡

ጳውሎስ በቆሮንቶስ መልዕክቱ እንዲህ ይላል

‹‹እግዚአብሔር በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አንደኛ #ሐዋርያትን፣ ሁለተኛ #ነቢያትን፣ ሦስተኛ #መምህራንን፣ ቀጥሎም #ታምራት_አድራጊዎችን፣ #የመፈወስ ስጦታዎች ያላቸውን፣ ሌሎችን #የመርዳት ስጦታ ያላቸውን፣ #የማስተዳደር ስጦታ ያላቸውንና በልዩ ልዩ #ልሳን የመናገር ስጦታ ያላቸውን ሰዎች መድቦአል። ››
1 ቆሮንቶስ 12:28 አ.መ.ት

ስለዚህ የፀጋ ምንጭ እግዚአብሄር ነው !! እንደወደደ እርሱ እንደፈቀደ ለሰዎች ፀጋን ይሰጣል ፡፡

2ኛ ማወቅ ያለብን ነገር ሰው የሚሾማቸው ወይም ራሳቸውን የሚሾሙ እንዳሉ ነው፡፡

ጳውሎስ ግን እንደዛ አይደለም ፡፡ ሁል ጊዜ ይህንን መጠንቀቅ ያለብን ይመስለኛል ፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ራሳቸውን የሾሙ ወይም በሰው የተሾሙ ሰዎች ሸክም አልባ እና ለመንጋ የማይራሩ ጨካኞች ይሆናሉና ፡፡ በእዚህም ብዙ ትውልድ ይጠፋል ፡፡ ጳውሎስ በቤተ ክስርቲያን ውስጥ ያሉ ነገር ግን ቤተ ክርስቲያናዊ ያልሆኑ ሰዎችን እጅግ የሚጠነቀቃቸው እና የሚታገላቸው ነበሩ ፡፡ አይ ጳውሎስ ገራሚው ሰው እኮ ነው ።

ለቤተ ክርስቲያን መሪዎች አደራ የሚላቸው ጉዳይም ይህንን ነው ፡፡ በሰው የሚሾሙ ያለ እግዚአብሄር የፀጋ ስጦታ ራሳቸውን የሚሾሙ ሰዎች ጳውሎስን እንቅልፍ አሳጥተውታል ረጅም ሰአት አስነብተውታል የምሩን አልቅሷል ። አይ ጳውሎስ የምር አገልጋይ እኮ ነው ። እኛስ እስከምን ድረስ እንታገላለን ፍቅር እና እውነት እስከምን ድረስ አብረን ይዘናቸው እንዘልቃለን።

የሐዋ ስራ 20፡28-30

‹‹በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ #ተጠንቀቁ። ከሄድሁ በኋላ ለመንጋው #የማይራሩ_ጨካኞች_ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ፥ ደቀ መዛሙርትንም #ወደ_ኋላቸው_ይስቡ ዘንድ ጠማማ ነገርን የሚናገሩ ሰዎች በመካከላችሁ እንዲነሡ እኔ አውቃለሁ። ስለዚህ ሦስት ዓመት ሌሊትና ቀን #በእንባ እያንዳንዳችሁን ከመገሠጽ እንዳላቋረጥሁ እያሰባችሁ ትጉ።››

እነዚህን ማስተዋል ከእኛ ይጠበቃል ፡፡

ከእግዚአብሔር ያልተሾመ ጨካኝ ነው። ወደ ኃላ ይስባል ደግሞ ለመንጋው አይራራም ። ጳውሎስ ግን ሐሰተኛ ተቃውሞ አያበቃም እውነተኞችን ያበረታታል ያስታጥቃል ።

🔸ወዳጆቼ እውነተኞቹ ምን እየጠበቃችሁ ነው?
🔸 ይህንን ትውልድ የማስታጠቅ ሐላፊነት የእናንተ አይደለምን?
🔸የኢየሱስ ስፍራ የሚያስመልሱ ሰዎች ማፍራት አትፈልጉም?
🔸 መድረኩን በክርስቶስ መአዛ የሚያውዱ ጀግኖች አልናፈቋቹም?
🔸የፀሎት ሰዎች በመንፈስ የሚቀጣጠሉ አላማ ያላቸው ሰዎች አልናፈቃቹም?

አምናለሁ እግዚአብሔር በዘመናችን ይህንን ያሳየናል አሜን

ፀጋ ይብዛላችሁ!!

ይቀጥላል

✍️Girum Difek


ሰብስክራይብ አድርጉ በጣም ድንቅ ስራ እየሰራ ነውና ትጠቀማላችሁ








ክፍል ሁለት

#የጳውሎስ_የሰላምታ_እጅ_ውስጥ

ጳውሎስ ሰላምተኛው ያለ ሰላምታ አይጀምርም ጳውሎስን ትኩር ብላችሁ ተመልከቱት፡፡ ተቆጥቶም ሰላምታ ሰጥቶ ነው የሚጀምው መቆጣቱ ሰላምታ እንዳይሰጥ አይከለክለውም ፡፡

ጳውሎስ በመልእክቶቹ ውስጥ ሁሉ መግቢያ እና መውጫ አለው ፡፡ ሲገባ ሰላም ሰጥቶ ተደራሲያኑን ጨብጦ ነው የሚገባው፡፡ በሰላምታ ውስጥ ሊያወራ የፈለገውን መልዕክት ብልጭ አድርጎ ገበሬ ዘር ለመዝራት መሬት እንደሚያለሰልስ እንደዛ የመልዕክት ተቀባዮችን ልብ ያለሰልሳል ለዘር ያዘጋጃቸዋል ፡፡ በኤፌ በሮሜ በገላቲያ በፊሊጲስዮስ …… በለሌሎቹም መልዕክቶች ውስጥ ይህ ሁሉ አለ !! በእውነት ጳውሎስን በጥንቃቄ ያየ ብዙ ያተርፋል ፡፡

ጳውሎስ ለሰላምታ እጁን ሲዘረጋ እነዚህ ቃላት
ይፅፋል ገላ 1፡1-5

‹‹በኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታንም ባነሣው በእግዚአብሔር አብ ሐዋርያ የሆነ እንጂ ከሰዎች ወይም በሰው ያልሆነ ጳውሎስ ከእኔም ጋር ያሉት ወንድሞች ሁሉ፥ ወደ ገላትያ አብያተ ክርስቲያናት፤ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታችንም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።ክፉ ከሆነ ከአሁኑ ዓለም ያድነን ዘንድ እንደ አምላካችንና እንደ አባታችን ፈቃድ ስለ ኃጢአታችን ራሱን ሰጠ።ለአብ ከዘላለም እስከ ዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን።›› ገላ 1፡1-5

ጳውሎስ መልዕክታቱን ሲፅፍ በሰላምታ ነው የሚጀምረው አንዳንድ ጊዜ አጠር ያለ ሰላምታ በማቅረብ ወደ ጉዳዩ ይፈጥናል አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ረጀም ሰላምታ ያቀርባል ፡፡ ምናልባት ይህንን የሚወስነው ተደራሲያኑ ወይም ሊፅፍ ያሰበው ጉዳይ አገብጋቢነት ነው ፡፡ በገላቲያ አጠር ያለ ሰላምታ ሲያቀርብ በሮሜ ደግሞ ረዘም ያለ ሰላምታ ያቀርባል ፡፡ ሮሜ 1፡1-7 ገላ 1፡1-3

በገላቲያ መፅሐፍ ውስጥ ጳውሎስ የተቆጣበት ወይም የተበሳጨበት ጉዳይ ስላለ በፍጥነት ወደ መልዕክቱ ይገባል ፡፡ ሁል ጊዜ ጳውሎስ የሚያበሳጨው ነገር የመዳን እውነት ሲነካ ሰዎች አይናቸው ከክርስቶስ ላይ ሲቅሉ ለመዳኛ ሌላ አማራጭ ሲፈልጉ ነው ፡፡

የገላቲያ ሰዎች እንዲህ አይነት ነበሩ ስለዚህ በቁጣ ቃል ይናገራል ፡፡ 👉አይጠቅማቹሁም ፣ ከጸጋ ትወድቃላችሁ ፣ ከክርስቶስ ትላያላችሁ እያከ ከባድ ማስጠንቀቂያ ያስጠነቅቃቸዋል ፡፡ ገላ 5፡1-1-5 ገላ 3፡1

ጳውሎስ ብዕር እና ወረቀት አዋዶ የሚፅፋቸው የሚከትባቸው ፅሁፎች እጅግ ውድ ንብረቶች ናቸው ፡፡ እንደ ቀልድ አይቶ የሚፅፋቸው ነገሮች የሉትም ፡፡ ሰላምታዎች እንኳ ለጳውሎስ መልዕክት ማስተላለፊ መንገዶች ናቸው ፡፡

በጳውሎስ የመግቢያ ሰላምታ ንግግሮች ውስጥ ያሉ እውነታዎች እኚህ ናቸው ።

🔸1ኛ የሐዋሪያነት ምንጭ ቁ 1-2
🔸2ኛ የተደራሲያን ስፍራ ቁ 1-2
🔸3ኛ ፀጋ እና ሰላም ቁ 3
🔸4ኛ ለመዳናችን የሆነው ነገር ቁ 4
🔸5ኛ ምስጋና ቁ- 5

እነዚህ ሃሳቦች በዝርዝር እንመልከት
1ኛ የሐዋሪያነት ምንጭ ቁ 1-2

‹‹በኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታንም ባነሣው በእግዚአብሔር አብ ሐዋርያ የሆነ እንጂ ከሰዎች ወይም በሰው ያልሆነ ጳውሎስ ከእኔም ጋር ያሉት ወንድሞች ሁሉ፥ ወደ ገላትያ አብያተ ክርስቲያናት ››

ጳውሎስን ሐዋሪያ ያደረገው ማነው ?

ይሄ ጥያቄ ለጳውሎስ አንገብጋቢ ጥያቄ እና መልስ የሚያሻው ጥያቄ ነው ፡፡ ምክንያቱም ጳውሎስ የሚያስተምረውን ትምህርት ላለመቀበል የጳውሎስ ሐዋሪያነት ላይ ጥያቄ የሚያነሱ ሰዎች ነበሩ ፡፡ ጳውሎስ ሐዋሪያ አይደለም ይሉት ነበር ፡፡ ይህ በገላቲያ ብቻ ሳይሆን በሌሎችም አብያተ ክርስቲያናት የተከሰተ ጥያቄ ነበር ።
የጳውሎስን አገልግሎት ላለመቀበል ጥያቄ ያነሱ ስለነበር በተደጋጋሚ ጳውሎስ ምላሽ ይሰጣል ፡፡1ኛ ቆሮ 1፡1 ሮሜ 1፤5

እዚህ ጋር መረዳት ያለብን እውነት ይህ ነው። ብዙዎች እውነተኛ ሆነክ እንኳ አንተን ላለመቀበል ይታገላሉ ፡፡ ነገር ግን ሰው አልተቀበለህም ማለት ሐሰተኛ ነህ ማለት አይደለም ፡፡ ሁል ጊዜ ራስህ መጠየቅ ያለብህ ከእግዚአብሄር ጋር ያለህ ግንኙነት ምን እንደሚመስል ለቅዱሳት መፅሐፍት ታማኝ ነኝ ወይ ? የሚለውን ነው፡፡ጳውሎስን በአብዛኛው ቤተ ክርስቲያን እሱን ላለመቀበል ምክንያት የሚደረድሩ ልበ ሻካራ ሰዎች ነበሩ ፡፡ በተለይም ሐዋሪያነቱ ላይ ጥያቄ እያነሱ ነበር ፡፡ ብዙ የሙግት ነጥቦችን በማንሳት እራሱን ቢከላከልም በ1ኛ ቆሮ መልክቱ ግን ጠንከር ያለ ሙግት ያቀርባል ፡፡

1ኛ ቆሮ 9፡1-5
‹‹እኔ ነጻ አይደለሁምን? ሐዋርያስ አይደለሁምን? ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስንስ አላየሁትምን? እናንተስ በጌታ ሥራዬ አይደላችሁምን?የሐዋርያነቴ ማኅተም በጌታ እናንተ ናችሁና ለሌሎች ሐዋርያ ባልሆን ለእናንተስ ምንም ቢሆን ሐዋርያ ነኝ።ለሚመረምሩኝ መልሴ ይህ ነው። ልንበላና ልንጠጣ መብት የለንምን?እንደ ሌሎቹ ሐዋርያትና እንደ ጌታ ወንድሞች እንደ ኬፋም፥ እኅት ሚስታችንን ይዘን ልንዞር መብት የለንምን?››

በአዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲህ ይላል

‹‹ እኔ ነፃ ሰው አይደለሁምን ? ሐዋርያስ አይደለሁምን ? ጌታችን ኢየሱስን አላየሁትምን? እናንተስ በጌታ የድካሜ ፍሬዎች አይደላችሁምን ? ለሌሎች ሐዋርያ ባልሆን እንኳ ለእናንተ ሐዋርያ ነኝ ምክንያቱም በጌታ የሐዋሪያነቴ ማኅተምእናንተ ናችሁ …..፡፡››

ስለዚህ ጳውሎስ ሐዋርያ መሆኑን በተለያየ መንገድ ለማሳያት ይሞክራል ፡፡ ጳውሎስ ሐዋርያ መሆኑን ብቻ ሳይሆን የሐዋርያነት ምንጩንም ይናገራል ፡፡ የሱ ሐዋሪያነት ከየት መጣ? ማን ሰጠው? የመስጠትስ ስልጣን የማን ነው? ጳውሎስ ይህንን በገላቲያ መግቢያ ላይ ይመልሳል ፡፡

የእውነት ሐዋሪያ ስለነበር የእውነት ይመልሳል ፡፡ ይህ የሁላችንም ገንዘብ መሆን አለበት እውነት ሰፈር አለመጥፋት ውሸት ሰፈር አለመገነት ።

በእርግጥ እግዚአብሔር እንደጠራን እናምናለን? በእኛ መስራት የሚፈልገው ነገር እንዳለስ እርግጠኞች ነን? አንድ እውነት ልንገራቹ እግዚአብሔር ሊጠቀምባት የማይፈልገው አማኝ የለም እናንተ ለእግዚአብሔር የጨለማን ሰፈር የሚያብራባችሁ ውዶቹ ናችሁ ። ስለዚህ አለም የሚለጥፍባቹን የውሸት ስያሜ በእውነት ብርሃን ገልጣችሁ ለትልቁ አላማ ተነሱ ።

የጌታ ፀጋ ይብዛላችሁ !!! አሜን

ይቀጥላል.......




የመጨመር ጣጣ
#ገላቲያዊነት
ገላቲያ ክፍል አንድ

ስለ ነገ የማያስብ ስለ ነገ የማይጨነቅ ሰው አለ ብሎ ማሰብ ከባድ ነው ፡፡ ነገን የማይፈራ ጀግና ማግኘት ከጭድ ውስጥ መርፌ ፈልጎ የማግኘት ያህል ከባድ ነው ፡፡ ነገ ግዙፍ ነው ነገ ሃያል ነው ነገ ገናና ነው ፡፡ ወላጆች ልጆቻቸውን ነጋቸውን አስበው በጨቅላ ወራት የተመጣተነ ምግብ ያበሏቸዋል ትምህርት ቤት ያስገቧቸዋል ሌላም ሌላም ...የጎረመሱ ሰዎች ስነ ነገ ማሰብ ይጀምራሉ ስለ ስራ፣ ስለ ትዳር፣ ነገ ስለሚሳካ የዛሬ አላማቸው ሌላም ሌላም … ለዚህም ነው የነገው ጌታ ኢየሱስ ስለ ነገ አትጨነቁ ከመጠን በላይ አታስቡ የሚል ማበረታቻ አዘል ቃላት የተናገረው ሰው መጨነቁ አይቀርማ !! ነገ ያስፈራል አዎ ግን

#ዘላለምስ???

ገላቲያ ቤተ ክስርቲያን ውስጥ በክርስትና ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ አጠቃላይ ስብሰባ ያስጠራ ጉባዬ ያዘረጋ ችግር ተፈጠረ ዘመኑ በ 49 አ.ም አከባቢ ነው ፡፡ ጳውሎስ በመጀመሪያው የሐዋሪያዊ ጉዞ የመሰረታት ቤተ ክርስቲያን ዛሬ ልብ የሚያናውጥ፣ በደቀ መዝሙር ጫንቃ ላይ ቀንበር በሚያከብድ ጉዳይ የተነሳ ቤተ ክርስቲያ በሁለት ጎራዎች ተወጥራ ተጨንቃለች ይህ ጭንቅ ጉባዬን ወለደ ፡፡ የመጀመሪያው የሐዋርያት ጉባዬ ተብሎ ይጠራል ።

የመጀመሪያው ጉባዬ በኢየሩሳሌም ተጠራ የሐዋ ስራ ምዕራፍ አስራ አምስት የእዚህ ጉዳይ ሪፖርት ነው ፡፡

የመጨመር ጣጣ የወለደው ጉባዬ

የችግሩ ምንጭ እንዲህ ይነበባል ፡፡

የሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 15፡1-2
‹‹አንዳንዶችም ከይሁዳ ወረዱና። እንደ ሙሴ ሥርዓት ካልተገረዛችሁ #ትድኑ ዘንድ አትችሉም ብለው ወንድሞችን ያስተምሩ ነበር። በእነርሱና በጳውሎስ በበርናባስም መካከል ብዙ ጥልና ክርክር በሆነ ጊዜ፥ ስለዚህ ክርክር ጳውስና በርናባስ ከእነርሱም አንዳንዶች ሌሎች ሰዎች ወደ ሐዋርያት ወደ ሽማግሌዎችም ወደ ኢየሩሳሌም ይወጡ ዘንድ ተቈረጠ።››

ጉዳዩን አንገብጋቢ የሚያደርገው #የመዳን ጉዳይ መሆኑ ነው ፡፡

🔸 እንደ ሙሴ ስርአት ካልተገረዛችሁ ትድኑ ዘንድ አትችሉም ቁ 1

በድጋሚ ይህንን ሃሳብ የሚያጠናክር ቃል ቁጥር አምስት ላይ እናገኛለን

‹‹ከፈሪሳውያን ወገን ግን ያመኑት አንዳንዶቹ ተነሥተው። ትገርዙአቸው ዘንድና የሙሴን ሕግ እንዲጠብቁ ታዙአቸው ዘንድ ይገባል አሉ።›› ሐዋ ስራ 15፡5

ለምን እንዲህ አሉ ብለን የጠየቅን እንደሆነ ፡- መልሱ ትድኑ ዘንድ ነው ፡፡ ለመዳን ተገረዙ የሙሴን ሕግ ጠብቁ !!

ችግሩ ይህ ነው !!

በክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከክርስቶስ ውጪ
🔸የመዳንን መንገድ የመፈለግ እና የመዳከር ሕይወት
🔸ክርስቶስ አይበቃኝም የሚል የመቅመዝበዝ ጉዞ
🔸ለባህሌ አደላለው በማለት የተፈጠረ በሰዎች መዳን ላይ የተጋረጠ አደጋ !!!
ኢየሱስ ሲደመር ሕግ

ክርስቶስ ላይ መጨመር መዘዙ ከባድ ነው ፡፡

ጳውሎስ በእዚህ ጊዜ እንደ አራስ ነብር ተናዷል ጭራዋ እንደተረገጠ ድመት ተቆጥቷል ፡፡ መልዕክቱን ሲፅፍ ሰላምታ እንኳን አያስረዝምም ፡፡ ወደ ጉዳዩ ለመግባት ይጣደፈል ፡፡

ለምን ?
🔸 የተነካው የመዳን ጉዳይ ነው ፡፡
🔸ከይሁዳ የወረዱት ሰዎች በዘላለም ጉዳይ ላይ ነው የተጋረጡት

ይሄ ለእኛ ትምህርት ነው
መቼ ነው ምንናደደው ?

🔸በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ክብራችን ሲነካ ወይስ የዘላለም አጀንዳ ሲነካ
🔸እኛ ስንደፈር ወይስ የእግዚአብሄር እውነት ሲደፈር
🔸እኛ በምክንያት ገለል ስንደረግ ወይስ የመለኮት ሀሳብ ከመድረኩ ገለል በመድረጉ

የገላቲያ መፅሐፍ በ49 ዓ.ም አከባቢ በአህዛቡ ሐዋርያ የተፃፈ በስድስት ምዕራፎች የተዋቀረ በ149 ቁጥሮች የተደረደረ በደቡብ ገላትያ ላለች አብያተ ክርስቲያት የተፃፈ ለመጀመሪያ ጊዜ የተከበ የአዲስ ኪዳን መፅሐፍ ነው ፡፡

ታዲያ ጳውሎስ የመጀመሪውን ደብዳቤ ለመፃፍ ሲነሳ የተነሳው በክርስቶስ የሚገኘው መዳን ሲደፈር ሲነካ ነው ፡፡

ለእግዚአብሄር እውነት መቆም ይሁንልን አሜን!!

ይቀጥላል .....


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
#girum በፀጋ ድናቹኃል




መነሳቱ መሰረታችንም ተስፋችንም ነው!!

ክርስትና ልዩ የሚያደርጉት ብዙ ነገሮች አሉ ከእነዛ ውስጥ አንዱ የሐይማታችን ሐዋሪያ እና ሊቀ ካህናት የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት መነሳቱ ነው ።ይህም ለሚከተሉት ሁሉ የሁሉ ነገራቸው መሰረት ነው ።

ጳውሎስ እንዲህ ይላል !!

“ክርስቶስም ካልተነሣ እንግዲያስ ስብከታችን ከንቱ ነው እምነታችሁም ደግሞ ከንቱ ናት፤”
— 1ኛ ቆሮንቶስ 15፥14

መነሳቱ የስብከታችን የእምነታችን መሰረት ነው።። የምንኖረውም ለተነሳልን ነው ።

“በሕይወትም ያሉት ስለ እነርሱ ለሞተውና ለተነሣው እንጂ ወደ ፊት ለራሳቸው እንዳይኖሩ ስለ ሁሉ ሞተ።”
— 2ኛ ቆሮ 5፥15

ይህ ብቻ አይደለም የመነሳታችን ተስፋም ነው!!

“ትንሣኤ ሙታንስ ከሌለ ክርስቶስ አልተነሣማ፤”
— 1ኛ ቆሮንቶስ 15፥13

ኢየሱስ ግን እንደተናገረው ተነስቷል

“እንደ ተናገረ ተነሥቶአልና በዚህ የለም፤ የተኛበትን ስፍራ ኑና እዩ።”
— ማቴዎስ 28፥6

እንኳን አደረሳችሁ!!


ፋሲካችን❤






----------------------------------------
  “የመስቀሉንም ውርደት ንቆ በእግዚአብሔር
   ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአል” (ዕብ 12:2)
----------------------------------------

2. አቤት የውርደት ቀን - በውርደት የተከወነ ስርየት

ስለ ክርስቶስ መከራ ስናንስብ ወደ ልባችን ፈጥኖ የሚመጣው የተቀበለው ሥቃይ ነው። እውነት ነው። ከዚህ በኋላ የምጽፈው ነገር የሞቱን አሠቃቂ ሥቃይ በምንም መልኵ አይቀንሰውም። ግን ከሥቃዩ አንድ ክፍል የኾነውን የዘነጋነው ይመስለኛል። የተሰቀለበት ቀን ታላቅ የውርደት ቀን ነበር።

ጌታችን ኢየሱስ በምድራዊ አገልግሎቱ በሰዎች መሰደብና መዋረድ ይባስም ብሎ “ብዔልዜቡል ያለብህ” እስከ መባል መድረስ ለእርሱ ብርቅ ነገር አልነበረም። ሆኖም ይህች ከዕለታት አንድ ቀን የነበረችው አርብ ግን፥ ከሌሎች አርቦች ሁሉ የተለየች የውርደት ቀን ነበረች። በዚህች ቀን ላይ እንደ ደረሰበት ያለ ውርደት ደርሶበት አያውቅም። ውርደቱ የቤዝዎታዊ ሥራው ገጽታ ነው እያልኳችሁ ነው።

አዲስ ኪዳን በበቀለበት በሜድትራኒያኑ ባህል ውስጥ፥ ውርደትና ከበሬታ (Honor and Shame) የሞትና የሕይወት ጕዳይ ነበር። ዲሲልቫ የተሰኘ ጸሐፊ (David deSilva) እንደሚነገረን ከኾነ፥ በዚህ ባህል ውስጥ የተገኘ አንድ ወጣት የሚጠበቅበት ግዴታ ውርደትን በማስወገድና ክብርን በመፈለግ የማኅበረሰቡን እሴት መላበስ ነው። ከዚህ የተነሣ፣ ውርደት በምንም ዓይነት ዐውድ አግባብነት አልነበረውም። እንዲያውም ከሞት የከፋ ነገር ቢኖር ውርደት በመኾኑ ‘ከመዋረድ ይልቅ መሞት ይሻላል’ ይሉ ነበር። ለምሳሌ ዕውቍ ሰኔካ እንዲህ ይላል፦

“የተከበረው ነገር የተከበረ ነው የምንለው የተከበረ ስለሆነ እንጂ በሌላ ምክንያት አይደለም” (that which is honorable is held dear for no other reason than because it is honorable”።

በዚህ ባህል ውስጥ፣ ከበሬታ በራሱ የሚፈለግ እሴት ነው። በአንጻሩ ደግሞ፣ ውርደት እስከ ሞት ድረስ እንኳ መፋለም ያስፈልጋል። ብሂሉ “ከምዋረድስ ልሙት” ነው። ለዚህ ነው፣ በዚህ ባህል ውስጥ ያሉ አባቶችና እናቶች በማኅበረሰቡ ዘንድ ተዋርደው ከመገኘት ይልቅ ልጆቻቸውን መግደል የቀለላቸው። ከበሬት-ውርደት እውን ኀይል ነው።

እናም፣ እያንዳንዱ ባህል ‘መዋረድ ይገባዋል’ ብሎ የፈረጀበትን ሰው ለማዋረድ የሚጠቀማቸው ግልጽና ስውር ስልቶች አሉት። ከእነዚህ መካከል ለምሳሌ ያህል፣ ጭንቅላትን መምታት አንዱ ነበር። ፊትን በጥፊ ማጮል፣ ጭንቅላትን በዱላ መቀጥቀጥ ተመቺውን ከክብር ያዋርዳል። በኢየሱስ ላይ፣ የሰውን ክብር የሚገፉ አዋራጅ ተግዳሮቶች በሙሉ በዚህች ቀን ደርሰዉበታል። ይህች ቀን ለጌታችን ታላቅ የውርደት ቀን ነበረች!

“ከእሾህም አክሊል ጎንጉነው በራሱ ላይ፥ በቀኝ እጁም መቃ አኖሩ፥ በፊቱም ተንበርክከው። የአይሁድ ንጉሥ ሆይ፥ ሰላም ለአንተ ይሁን እያሉ ዘበቱበት፤ 30ተፉበትም መቃውንም ይዘው ራሱን መቱት። 31ከዘበቱበትም በኋላ ቀዩን ልብስ ገፈፉት፥ ልብሱንም አለበሱት ሊሰቅሉትም ወሰዱት።” (ማቴ 27:29–31)።

አቤት አዋረዱት። የኛ ክብር ዕንቍ በአፈር ላይ አንደበለሉህ፣ ረገጡህ፣ ተፉብህ፣ ልብስህን ገፈው ዕርቃንህን ገለጡ፣ ለንጉሥ እንደሚሰገድ እየሰገዱ አላገጡብህ፣ አሾፉብህ። አንተም ዝም አልህ። የውርደትን ጽዋ ጨለጥኻት። የኔ ውብ! የኔ ትሁት። ይህ ሁሉ እኮ ለእኛ ነው! ተዋርደህ የተዋረደውን ሰው አከበርህ። ያዋረዱህን አከበርህ። የውርደትን ጥግ ነክተህ፥ ክቡር ሥጋህን እንመስል ዘንድ እጩዎች አደረግኸን። ምስጋና ይግባህ እንላለን!

በርግጥ ጳውሎስ ሰው ኾኖ መገለጡ በራሱ ውርደት ሆኖ ሳለ፥ ኢየሱስ የወረደበትን የውርደት ልክ ሲያመላክተን እንዲህ ይለናል፦ የባሪያን መልክ ይዞ “እስከ ሞት፣ ያውም በመስቀል ላይ እስከ መሞት ድረስ ታዛዥ ሆነ”። ከክብር ልእልናው ወርዶ፥ ኀጢአተኞች በዐመጽ በጸቀየ እጃቸው ንጹሁን እርሱን እንዲያዋርዱት ፈቀደላቸው። እኛ ያንተን ያኽል ክብር የሌለን በአንተ የደረሰው ውርደት አንዲቷ እንኳ ብትደርስብን፥ አምባጋሮውን ማን ይችል ነበር?

የእብራውያንም ጸሐፊ እንዲኹ፣ ኢየሱስ የደረሰበትን መከራ ‘ውርደት’ በማለት ይገልጠዋል፦ “ኢየሱስን እንመልከት... የመስቀሉንም ውርደት ንቆ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአል” (ዕብ 12:2)። እኛም የተጠራነው የእርሱን ፈለግ ልንከተል ነው። ስለዚህ ስለ እርሱ መመስከር ውርደት ሳይኾን ክብር ነው “በእኔና በቃሌ የሚያፍር ሁሉ፣ የሰው ልጅም በአባቱ ግርማ፣ ከቅዱሳን መላእክት ጋር ሲመጣ ያፍርበታል” (ማር 8:38)። “ስለ ጌታችን ለመመስከር ወይም የእርሱ እስረኛ በሆንሁት በእኔ አትፈር” (2 ጢሞ 1:8)።

ይህንን ውርደት ከመስቀሉ ላይ አንስተን፥ ኢየሱስን ዝነኛ ልናደርገው አንችልም። መልካሙ ዜና ውርደትን ገንዘቡ ያደረገ ነው። የምናመልከው ጌታ የተሰቀለ-ክርስቶስ ነው። ይህ ለሰው ጥበብ አይመችም። ለሥጋችን አይመችም። ይህ የኢየሱስ መስቀል ለዚህ ዓለም ገዢዎች አይመችም። ስለዚህ ነው፣ ‘ኢየሱስ አይፖተለክም’ ወይም ድምፅ መስጫ ሳጥን ለማግኘት ሲባል ለፖለቲካ ፍጆታ አይውልም የሚባለው። መንገዱ እጅግ ጠባብ ነውና። ማንም ሊከተለኝ የሚወድ ‘መስቀሉን ተሸክሞ ይከተለኝ’ አይደል ያለው? ስለዚህ በእነዚህ ቀናት የኢየሱስን ውርደትና ክብር እናውጅ።

በመጨረሻም የእብራውያን ጸሐፊ እንዲህ እያለ መልእክቱን ይዘጋል፦

“እርሱ የተሸከመውን ውርደት ተሸክመን ከሰፈር ውጭ ወደ እርሱ እንውጣ። ምክንያቱም በዚህ ቋሚ ከተማ የለንም፤ ነገር ግን ወደ ፊት የምትመጣዋን ከተማ እንጠብቃለን።” (ዕብ 13:13–14)

የህማማቱ ሰሞን
_____
[1] David A. deSilva, Honor, Patronage, Kinship & Purity: Unlocking New Testament Culture (Westmont, IL: InterVarsity Press, 2012), 22–23

✍️ Samson Tilahun


መንፈስ ቅዱስ


1. ስድብን የጠገበው፥ መስቀለኛው ንጉሥ (ማቴ. 27፡32-44)
ከአልበርት አንስታይን አጠገብ የተቀመጠ አንድ ተማሪ አንስታይንን “ምን እያጠናህ ነው?” ብሎ ይጠይቀዋል። አልበርት አንስታይንም “የፊዝክስ ተማሪ ነኝ” ብሎ ይመልስለታል። ከዚያም ያ ተማሪ “ኦ ፊዚክስ... እኔስ ባለፈው ዓመት አጥንቼው ጨርሻለሁ” አለው ይባላል። ይህ ምልልስ ምጸት አዘል የሚኾነው ታሪክን የኋሊት የሔድን እንደኾን ነው። አንስታይን ፊዝክስን ማጥናት ብቻ ሳይኾን ራሱ ፊዝክስን ለውጦታልና።

ልክ እንዲሁ፥ ኢየሱስ ሲሰቀል አራት ቡድኖች አንገታቸውን እየነቀነቁ ይሳለቁበት እንደነበር ማቴዎስ ከቍ.32-44 ባለው ያስመለክተናል።

1. 27፡27-31 በሮማውያን ወታደሮች ተሰደበ
  የእሾህ አክሊል ደፍተው የአይሁድ ንጉሥ እያሉ
  አሾፉበት (ቍ. 29)

2. 27፡27-31 በአላፊ አግዳሚው ሕዝብ ተሰደበ
  [ሕዝቡ] በኀይል እየተሳደቡና ራሳቸውን እየነቀነቁ
  አሾፉበት (ቍ. 40)

3. 27፡41-42 በአይሁድ መሪዎች ተሰደበ
  የካህናት አለቆች፣ ጸሐፍትና የአይሁድ ሽማግሌዎች
  አሾፉበት "ሌሎችን አዳነ፥ ራሱን ሊያድን አይችልም፤
  የእስራኤል ንጉሥ ከሆነ፥ አሁን ከመስቀል ይውረድ...
  በእግዚአብሔር ታምኖአል... ከወደደውስ አሁን ያድነው"
  (ቍ. 42-43)

4. 27:43 አብረውት በተሰቀሉ ወንበዴዎች እንዲሁ
  የስድብ ናዳ ያወርዱበት ነበር

ይህንን እኔ ብቻ ያየሁት አይደለም፣ ብዙ የአዲስ ኪዳን ነባብያን ያስተዋሉት ጕዳይ ነው። እኛም ከትንሳኤው፣ ከዕርገቱና በአብ ቀኝ ከመቀመጡ ባሻገር ያለን አማኞች ታሪክን የኋሊት ስንቃኝ፥ ማቴዎስ እንድንመለከት የሚፈልገውን ምጸት እንመለከታለን።

► “ንጉሥ ከሆንክ ከመስቀሉ ውረድ?” አሉት?
    ንጉሥ ቢኾንሳ፣ ጭራሽ
    እንዲያውም በመስቀሉ እየነገሠ ቢኾንስ?

► “እስቲ ራስህን አድን?” አሉት?
    አዳኝ ቢኾንሳ? ጭራሹንም ከመስቀሉ ባለመውረዱ
    ቢኾንስ ድነትን የሚፈጽመው? ይባስ ብሎም፣ መስቀሉ
    ወደ ምጡቅ ዙፋን የሚወጣበትና “ባሪያዬ እጅግ ከፍ ከፍ ይላል”
    እንደሚል የሚነግሥበት መንገድ ቢኾንሳ?

አይ ሰው! ሰው ሆይ፥ ከጥበብህ በላይ “የእግዚአብሔር ሞኝነት ይጠበባልና፥ የእግዚአብሔርም ድካም ከሰው ይልቅ ይበረታልና።” (1 ቆሮ. 1:25)
“የጌታን ልብ ማን አውቆት ነው? እኛ ግን የክርስቶስ ልብ አለን።” (1 ቆሮ. 2:16)

የህማማቱ ሰሞን

Samson Tilahun

Показано 20 последних публикаций.