የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፋይናንስ የሚያደርጋቸው ፕሮጀክቶች የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ትርፋማና ጠንካራ ተቋማት እንዲሆኑ መስራት እንደሚገባ በኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አሳሰበ።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሀገሪቱን የግብርና ሜካናይዜሽን ከማዘመንና ከማስፋፋት እንዲሁም የስራ ዕድሎችን ከመፍጠር አኳያ ሚናው የጎላ ነው ያለው ቋሚ ኮሚቴው፤ የህብረተሰቡን የኑሮ ደረጃ ማሻሻል የሚያስችሉ አምራች እና አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን በአካባቢው ከሚገኙ ዩንቨርሲቲዎች፣ ኢንዱስትሪ ፓርኮች እና የግብርና ምርምር ተቋማት ጋር በመቀናጀት እንዲሁም የገበያ ትስስር በመፍጠር ሁሉም ባለድርሻ አካላት ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ዕድል መፍጠር ይገባል ብሏል።
የቋሚ ኮሚቴ አባላት አክለውም፤ ባንኩ በዋናነት በሚሰጣቸው የሊዝ ፋይናንስ፣ የፕሮጀክት ፋይናንስ እና የተለየ የቢዝነስ ሀሳብ ላላቸው ግለሰቦች የሚሰጠውን የፋይናንስ አቅርቦት ለሀገር ኢኮኖሚያዊ እድገትና ብልጽግና የማይተካ ሚና እንዳለው በመገንዘብ የተጀመሩ የሪፎርም ስራዎችን ማጠናከር ይገባል ብለዋል።
ባንኩ ፋይናንስ የሚያደርጋቸው አምራችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እየሰሯቸው የሚገኙ ዘርፈ ብዙ ተግባራት በሀገሪቱ የሚከሰተውን የኑሮ ውድነት በመቀነስ የገበያ መረጋጋት ለመፍጠር ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳላቸው በመገንዘብ ተጨማሪ ፕሮጀክቶችን ወደ ስራ ማስገባት እንደሚገባ የቋሚ ኮሚቴው አባላት ገልጸዋል።
የመንግስት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሰቢ የተከበሩ ስለሺ ኮሬ (ዶ/ር) የግብርና ፕሮጀክቶች የተቀናጀ የግብርና ዘዴዎችን ተጠቅመው ምርታማነት ከመጨመር በሻገር የአካባቢ ስነ-ምህዳር ለመጠበቅ የሚያስችል የተፈጥሮ ማዳበሪያ ዝግጅት በጥናት እና ምርምር በማስደገፍ የማህበረሰቡ የምግብ ዋስትና እንዲረጋገጥ አጠናክሮ መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
በኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሐዋሳ ዲስትሪክት ስራ አስኪያጅ አቶ ተሾመ ጌታነህ በበኩላቸው፤ባንኩ የሚደግፋቸው የተለያዩ ተቋማት ውጤታማ ሲሆኑ የባንኩም ትርፋማነት የሚጨምር መሆኑን በመረዳት፤ ተቋማቱ ለሚያጋጥማቸው ማንኛውም አይነት ችግር ፈጥኖ መፍትሔ በመስጠት እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ በመስራት ምርትና ምርታማነትን ለመጨመር እየሰራ መሆኑን አስረድተዋል።
ተጨማሪም ሁሉም የሀገሪቱ ዜጎች ባንኩ በሚሰጣቸው የልማት ስራዎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል ከወለድ ነጻ የሆነ የፋይናንስ አገልግሎትን ወደ ስራ ማስገባቱንም ጠቁመዋል፡፡
ቋሚ ኮሚቴው በክልሉ ውስጥ በኢትዮጵያ በልማት ባንክ የሚደገፉ የእርሻ ልማት፣ የዱቄት ፋብሪካ፣የቴራዞን ማምረቻ እና ፈርኒቸርና የውስጥ ዲዛይንን የስራ እንቅስቃሴን ተዘዋውሮ ተመልክቷል።