የኢትዮጵያ ልማት ባንክ መሰረታዊ የሰራተኞች ማህበር ከባንኩ ሰራተኞች ጋር በጋራ በመሆን ለቀድሞ የባንኩ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው የሽኝት እና የምስጋና መርሃ ግብር አካሄደ፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ መሰረታዊ የሰራተኞች ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ዮሴፍ ተስፋዬ በመክፈቻ ስነስርአቱ ወቅት እንዳሉት ለባንኩ የዛሬ ስኬት ቁልፍ የአመራር ሚና የተጫወቱትን የቀድሞ የባንኩ ፕሬዘዳንት ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው በክብር ለመሸኘት እንዲሁም በቅርቡ የተመደቡትን የባንኩ ፕሬዘዳንት ዶ/ር እመቤት መለሰ እንኳን ደህና መጡ ለማለት ያለመ ፕሮግራም መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በፕሮግራሙ ለቀድሞ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው እውቅናና ስጦታ ከሰራተኛው ተበርክቶላቸዋል፡፡
የሄደውን አመስግኖ መሸኘት እንዲሁም አዲስ የመጣውን በመልካም ተቀብሎ ምቹ የስራ አካባቢ ፈጥሮ ውጤታማ ስራ መስራት ያስፈልጋል ያሉት አቶ ዮሴፍ አዲስ ተመድበው በመስራት ላይ ለሚገኙት የባንኩ ፕሬዝዳንት ዶ/ር እመቤት መለሰ የእንኳን ደህና መጡ ስጦታ ከሰራተኞች ተበርክቶላቸዋል፡፡
ባንኩ በርካታ ውጤቶችን እንዲያስመዘግብ ከዶ/ር ዮሐንስ ጋር በመሆን ላገለገሉ የባንኩ ምክትል ፕሬዝዳንቶችም ስጦታ ከሰራተኛው ተበርክቶላቸዋል፡፡
በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ የፋይናንስ ተቋማት ሰራተኛ ማህበር ኢንዱስትሪ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ደስታ በርሄ እንዳሉት ዶ/ር ዮሐንስ በፈታኝ ሁኔታ ውስጥ የነበረውን ባንክ መላውን ሰራተኛ አስተባብረው በመስራታቸው በርካታ ስኬቶችን እንዲያስመዘግብ በማድረጋቸው መመስገን ይገባቸዋል ያሉ ሲሆን፣ ለሰራተኛውም የደመወዝ ጭማሪ እና ጥቅማጥቅም መንግስት እንዲፈቅድ በማድረግ የበኩላቸውን ተወጥተዋል ብለዋል፡፡
አዲስ ለተሾሙት የባንኩ ፕሬዝዳንትም ባንኩ ስኬቶችን እንዲያስመዘግብ ከሰራተኛው ጋር በቅንጅት ውጤታማ ስራ እንዲሰሩ አቶ ደስታ በርሄ አደራ ብለዋል፡፡ ባንኩ ከዚህ በፊት እንደ ተቋም የሽኝትና የምስጋና እንዲሁም አዲስ ለተሾሙት ፕሬዚዳንት ደግሞ አቀባበል ያደረገ ሲሆን፣ የአሁኑ መርሃ ግብር ሰራተኛውን በማስተባበር በማህበሩ አማካኝነት የተዘጋጀ ነው።