የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በትግራይ ክልል ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ እንዲሻሻል የሚያደረገውን ጥረት አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተጠቆመ፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የመቐለ ዲስትሪክት የሚያቀርበውን የብድር አገልግሎት በማሳደግ የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያደርገው ጥረት ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አሳስቧል።
ቋሚ ኮሚቴው በመቐለ ዲስትሪት በመገኘት በባንኩ ፋይናንስ የተደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ያሉበትን ደረጃ ተዘዋውሮ ጎብኝቷል፡፡
በዚህም ባንኩ ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የሊዝ ፋይናንሲንግ ሥልጠና በመስጠትና ወደ ሥራ በመመለስ የክልሉን ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ለማነቃቃት የሚደረገው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የቡድኑ ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ አዲስ ዓለማየሁ ተጠቁመዋል።
በጥናትና በዕቅድ ላይ የተመሰረተ የብድር አሰባሰብ ላይ ትኩረት በማድረግ ኃብትን በአግባቡ መሰብሰብ እንደሚገባ የቡድኑ ሰብሳቢ በዚሁ ወቅት አሳስበዋል።
በክልሉ ከነበረው ጦርነት ጋር ተያይዞ ለመሰብሰብ አዳጋች የሆነ ኃብት ለመሰብሰብ ጥረት በመደረግ ላይ እንደሚገኝ የዲስትሪክቱ ኃላፊ አቶ ዮሐንስ አማረ ገልጸዋል።
የብድርና የወለድ ክፍያ ጊዜ ማራዘሚያ እንዲሁም የውጪ ምንዛሬና የጥሬ ዕቃ በቅድሚያ እንዲያገኙ መደረጉንም ተናግረዋል።
በጦርነቱ የወደሙና የተዘረፉ ፕሮጀክቶችና ኢንዱስትሪዎች መኖራቸው፣ የኃይል መቆራረጥና ዕጥረት እና ለብድር አመላለስ መዘግየት በምክንያትነት ተነስቷል።