በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ አሜን።
ወትባርክ አክሊለ ዓመተ ምህረትከ
መርጌታ ከፍተኛ የባህል ሐኪም
እንቁጣጣሽ፥ ፍቅር የወለደው ቃል
እንቁጣጣሽ፣ ቅዱስ ዮሐንስ ዓውደ ዓመት፣ ዘመን
መለወጫ፣ ዘመነ ማቴዎስ፣ ዘመነ ማርቆስ፣ ዘመነ
ሉቃስ /ከአራቱ ወንጌላውያን አንዱን/ እየተባለ
ቢጠራም ሁሉም ያው አዲስ ዓመትን ከታሪክና
ከትርጉም ጋር የሚገልጹ ስያሜዎች ሆነው
እናገኛቸዋለን።
ሀገራችን ኢትዮጵያ በሦስት ሕግጋት ማለትም፦ በሕገ
ልቡና፣ በሕገ ኦሪት /ብሉይ ኪዳን/ እና በሕገ ወንጌል /
አዲስ ኪዳን/ ውስጥ ያለፈች ብቸኛ ሀገር ሆና በመገኘቷ
ጥንታዊትና ታሪካዊት ሀገር ለመሆን በቅታለች። ሕገ
ልቡና ማለት የሰው ልጆች ከእግዚአብሔር የተሰጣቸው
የሚጠብቁትና የሚመሩበት የተጻፈ ሕግ ሳይኖራቸው
ግን በልቡናቸው ማስተዋል ብቻ ይኖሩበት የነበረው
ዘመን ሲሆን ይህም ከአዳም እስከ ሙሴ የነበረውን
ዘመን የሚያካትት ነው። ሕገ ኦሪት ማለት ደግሞ
እግዚአብሔር ለሰው ልጆች መመሪያ የሚሆን የጽሑፍ
ትዕዛዝና ሕግ በሙሴ አማካይነት የሰጠበትና ሰዎችም
በተሰጣቸው ሕግ መሠረት መኖር የጀመሩበት ዘመን
ሲሆን ይኸውም ከሙሴ እስከ ጌታ ወደዚህ ዓለም
በሥጋ መምጣት ጊዜ ድረስ ነበር። ሕገ ወንጌል ማለት
ደግሞ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዓለም ቆይታው
ያስተማረው ትምህርት፣ የሰው ሥርዓት፣ ያደረገው ቃል
የሰማችሁት በእናንተ ጸንቶ ይኑር። ከመጀመሪያ
የሰማችሁት በእናንተ ቢኖር እናንተ ደግሞ በወልድና
በአብ ትኖራላችሁ። እርሱም የሰጠን ተስፋ ይህ
የዘላለም ሕይወት ነው።” /፩ኛ ዮሐ. ፪፥፳፬/ ተብሎ
እየተነገረን ምቀኞቻችን ግን እነሆ የዘላለም ሕይወት
ሊያሳጡን እየታገሉ ይገኛሉ። የመውጊያውን ብረት
መቃወም ለማን እንደሚብስበት ማየት ከፈለጉ
ይቀጥሉ እንኳንስ ተዋሕዶ ሃይማኖታችን ሊለወጥ
ሊታደስ ቀርቶ ተፈጥሮ እንኳ እየታደሰ ወደ ሌላ
ነገር ሲቀየር አልታየም። እነሆ አዲስ ዘመን
እንቁጣጣሽ በየዓመቱ ሲመጣ ለሜዳ ተራራው
ውበት የሚያጐናጽፉት አደይ አበቦች እንኳ ቢጫነት
ቀለማቸውን ቀይረው ጽጌረዳ ወደ መሆን
አይለወጡም በየዓመቱ ያው ናቸውና። እንግዲያስ
ሊለወጥ ሊታደስ የሚገባው ወይም ተሐድሶ
የሚያስፈልገው ለማን ነው? ቢባል ሐዋርያው ቅዱስ
ጳውሎስ እንደሚነግረን በኃጢአት መንፈሳዊ
ሕይወቱ ላረጀ ለደቀቀ የሰው ልጅ ሁሉና በተለይ
ደግሞ በሐሰትና በማታለል ትምህርት ተጠልፎ
የሚጠልፈውን ሁሉ /ኤፌ. ፬፥፲፬/ ሲሆን በምክሩም
መጨረሻ “ፊተኛ ኑሯችሁን እያሰባችሁ
እንደሚያታልል ምኞት የሚጠፋውን አሮጌውን ሰው
አስወግዱ በአእምሯችሁም መንፈስ ታደሱ” /ኤፌ.
፬፥፳፪/ በማለት ይነግረናል።
በመሆኑም በኃጢአት ያረጀው፣ በክህደት
የጎሰቆለው፣ በገንዘብ ጥቅም የታወረው ሁሉ
ካለፈው ዘንድሮ ከዘንድሮውም በሚመጣው ዓመት
ጉድለቱን እያስተካከለ በመንፈሱ፣ በኑሮ ዕቅዱ
እየተሻሻለና እየታደሰ ሊመጣ የሚገባው እርሱ ነው
እንጂ ቤተ ክርስቲያን አይደለችም። ዛሬ በዓለም
ዙሪያ እንደሚታየውና እንደሚሰማው ከአንዲቷ
ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን ተለይተው ወጥተው
እንደ አሸን የፈሉት የክርስትና ድርጅቶች ነን ባዮች
ሁሉ እምነታቸውን አድሰው አድሰው የደረሱበት
ደረጃ ቢኖር ከተፈጥሮ ሥርዓት ውጭ ወጥተው
በግብረ ሰዶም የሚኖሩትን ከማጋባታቸውም
በተጨማሪ እንስሳትንም “የክርስትና ጥምቀት”
በማጥመቅ ላይ ባሉበት ዘመን ላይ ደርሰዋል።
እንግዲህ የዛሬ ተሐድሶዎች ለእኛም የደገሱልን
ይህንን ዕጣ ነው። የጌቶቻቸው ዕድገት እዚህ ድረስ
መድረሱን እየሰማንና እያየን ነውና።
ይልቁኑስ የራቀው ቀርቦ፣ የከዳው አምኖ፣ በጥቅም
የሰከረው ሰክኖ፣ ፍቅር ያጣው ፍቅርን ገንዘብ አድርጎ፣
የበደለው ንስሐ ገብቶ፣ ቤተ ክርስቲያኑን ሊሸጥ
የሚያስማማው እርሱን ትቶ በማያወላውል አቋም
ቆርጦ ቢነሳ የጥንቷን ኢትዮጵያ ከነሃይማኖታዊ
መገለጫዋ በትዝታ ብቻ ሳይሆን በእውነታው ዓለም
ውስጥ በገሀድና በደስታ ይኖርባታል፣ ይኮራባታል፣
ይመካባታል። የዚያን ጊዜ እንደቀድሞዎቹ
ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ሁሉ መንግሥት ከሕዝብ
ጋር፣ ቤተ ክህነቱም ከምዕመናን ጋር የጠበቀ ፍቅርና
መተሳሰብ ስለሚኖረው ይሄም ትውልድ በተራው
እንቁጣጣሽን የመሰለ ፍቅር የወለደውን ሌላ አዲስ
ቃል በመፍጠር ለትውልድ ሊያበረክት ይችላል።
እግዚአብሔር በጽኑ ሥልጣኑ ቤተ ክርስቲያናችንን እና
ሀገራችን ኢትዮጵያን ይጠብቅልን። አሜን።
እንኳን ከዘመነ ዮሐንስ ወደ ዘመነ ማቴዎስ በሰላም
አሸጋገረን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወትባርክ አክሊለ ዓመተ ምህረትከ
መሪጌታ ሊቅ ወጠቢብ 🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
☎️☎️0917468918
አምላክ አሜን።
ወትባርክ አክሊለ ዓመተ ምህረትከ
መርጌታ ከፍተኛ የባህል ሐኪም
እንቁጣጣሽ፥ ፍቅር የወለደው ቃል
እንቁጣጣሽ፣ ቅዱስ ዮሐንስ ዓውደ ዓመት፣ ዘመን
መለወጫ፣ ዘመነ ማቴዎስ፣ ዘመነ ማርቆስ፣ ዘመነ
ሉቃስ /ከአራቱ ወንጌላውያን አንዱን/ እየተባለ
ቢጠራም ሁሉም ያው አዲስ ዓመትን ከታሪክና
ከትርጉም ጋር የሚገልጹ ስያሜዎች ሆነው
እናገኛቸዋለን።
ሀገራችን ኢትዮጵያ በሦስት ሕግጋት ማለትም፦ በሕገ
ልቡና፣ በሕገ ኦሪት /ብሉይ ኪዳን/ እና በሕገ ወንጌል /
አዲስ ኪዳን/ ውስጥ ያለፈች ብቸኛ ሀገር ሆና በመገኘቷ
ጥንታዊትና ታሪካዊት ሀገር ለመሆን በቅታለች። ሕገ
ልቡና ማለት የሰው ልጆች ከእግዚአብሔር የተሰጣቸው
የሚጠብቁትና የሚመሩበት የተጻፈ ሕግ ሳይኖራቸው
ግን በልቡናቸው ማስተዋል ብቻ ይኖሩበት የነበረው
ዘመን ሲሆን ይህም ከአዳም እስከ ሙሴ የነበረውን
ዘመን የሚያካትት ነው። ሕገ ኦሪት ማለት ደግሞ
እግዚአብሔር ለሰው ልጆች መመሪያ የሚሆን የጽሑፍ
ትዕዛዝና ሕግ በሙሴ አማካይነት የሰጠበትና ሰዎችም
በተሰጣቸው ሕግ መሠረት መኖር የጀመሩበት ዘመን
ሲሆን ይኸውም ከሙሴ እስከ ጌታ ወደዚህ ዓለም
በሥጋ መምጣት ጊዜ ድረስ ነበር። ሕገ ወንጌል ማለት
ደግሞ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዓለም ቆይታው
ያስተማረው ትምህርት፣ የሰው ሥርዓት፣ ያደረገው ቃል
የሰማችሁት በእናንተ ጸንቶ ይኑር። ከመጀመሪያ
የሰማችሁት በእናንተ ቢኖር እናንተ ደግሞ በወልድና
በአብ ትኖራላችሁ። እርሱም የሰጠን ተስፋ ይህ
የዘላለም ሕይወት ነው።” /፩ኛ ዮሐ. ፪፥፳፬/ ተብሎ
እየተነገረን ምቀኞቻችን ግን እነሆ የዘላለም ሕይወት
ሊያሳጡን እየታገሉ ይገኛሉ። የመውጊያውን ብረት
መቃወም ለማን እንደሚብስበት ማየት ከፈለጉ
ይቀጥሉ እንኳንስ ተዋሕዶ ሃይማኖታችን ሊለወጥ
ሊታደስ ቀርቶ ተፈጥሮ እንኳ እየታደሰ ወደ ሌላ
ነገር ሲቀየር አልታየም። እነሆ አዲስ ዘመን
እንቁጣጣሽ በየዓመቱ ሲመጣ ለሜዳ ተራራው
ውበት የሚያጐናጽፉት አደይ አበቦች እንኳ ቢጫነት
ቀለማቸውን ቀይረው ጽጌረዳ ወደ መሆን
አይለወጡም በየዓመቱ ያው ናቸውና። እንግዲያስ
ሊለወጥ ሊታደስ የሚገባው ወይም ተሐድሶ
የሚያስፈልገው ለማን ነው? ቢባል ሐዋርያው ቅዱስ
ጳውሎስ እንደሚነግረን በኃጢአት መንፈሳዊ
ሕይወቱ ላረጀ ለደቀቀ የሰው ልጅ ሁሉና በተለይ
ደግሞ በሐሰትና በማታለል ትምህርት ተጠልፎ
የሚጠልፈውን ሁሉ /ኤፌ. ፬፥፲፬/ ሲሆን በምክሩም
መጨረሻ “ፊተኛ ኑሯችሁን እያሰባችሁ
እንደሚያታልል ምኞት የሚጠፋውን አሮጌውን ሰው
አስወግዱ በአእምሯችሁም መንፈስ ታደሱ” /ኤፌ.
፬፥፳፪/ በማለት ይነግረናል።
በመሆኑም በኃጢአት ያረጀው፣ በክህደት
የጎሰቆለው፣ በገንዘብ ጥቅም የታወረው ሁሉ
ካለፈው ዘንድሮ ከዘንድሮውም በሚመጣው ዓመት
ጉድለቱን እያስተካከለ በመንፈሱ፣ በኑሮ ዕቅዱ
እየተሻሻለና እየታደሰ ሊመጣ የሚገባው እርሱ ነው
እንጂ ቤተ ክርስቲያን አይደለችም። ዛሬ በዓለም
ዙሪያ እንደሚታየውና እንደሚሰማው ከአንዲቷ
ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን ተለይተው ወጥተው
እንደ አሸን የፈሉት የክርስትና ድርጅቶች ነን ባዮች
ሁሉ እምነታቸውን አድሰው አድሰው የደረሱበት
ደረጃ ቢኖር ከተፈጥሮ ሥርዓት ውጭ ወጥተው
በግብረ ሰዶም የሚኖሩትን ከማጋባታቸውም
በተጨማሪ እንስሳትንም “የክርስትና ጥምቀት”
በማጥመቅ ላይ ባሉበት ዘመን ላይ ደርሰዋል።
እንግዲህ የዛሬ ተሐድሶዎች ለእኛም የደገሱልን
ይህንን ዕጣ ነው። የጌቶቻቸው ዕድገት እዚህ ድረስ
መድረሱን እየሰማንና እያየን ነውና።
ይልቁኑስ የራቀው ቀርቦ፣ የከዳው አምኖ፣ በጥቅም
የሰከረው ሰክኖ፣ ፍቅር ያጣው ፍቅርን ገንዘብ አድርጎ፣
የበደለው ንስሐ ገብቶ፣ ቤተ ክርስቲያኑን ሊሸጥ
የሚያስማማው እርሱን ትቶ በማያወላውል አቋም
ቆርጦ ቢነሳ የጥንቷን ኢትዮጵያ ከነሃይማኖታዊ
መገለጫዋ በትዝታ ብቻ ሳይሆን በእውነታው ዓለም
ውስጥ በገሀድና በደስታ ይኖርባታል፣ ይኮራባታል፣
ይመካባታል። የዚያን ጊዜ እንደቀድሞዎቹ
ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ሁሉ መንግሥት ከሕዝብ
ጋር፣ ቤተ ክህነቱም ከምዕመናን ጋር የጠበቀ ፍቅርና
መተሳሰብ ስለሚኖረው ይሄም ትውልድ በተራው
እንቁጣጣሽን የመሰለ ፍቅር የወለደውን ሌላ አዲስ
ቃል በመፍጠር ለትውልድ ሊያበረክት ይችላል።
እግዚአብሔር በጽኑ ሥልጣኑ ቤተ ክርስቲያናችንን እና
ሀገራችን ኢትዮጵያን ይጠብቅልን። አሜን።
እንኳን ከዘመነ ዮሐንስ ወደ ዘመነ ማቴዎስ በሰላም
አሸጋገረን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወትባርክ አክሊለ ዓመተ ምህረትከ
መሪጌታ ሊቅ ወጠቢብ 🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
☎️☎️0917468918