ያሬዳውያን


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


የየበዓላቱ ስርአተ #ዋዜማ ፤ #ማህሌት ፤ #ወረብ ከ7 ቀናት እንዲሁም የየሳምንቱ መዝሙራት እና ምስባክ በጽሑፍ እና በድምጽ የሚቀርቡበት ቻናል ነው
#ሁሉም_ነገር_ስለ_ማህሌት
ማህሌታውያን ቻናሉን share ያርጉ
ጥያቄ አስተያየት በግሩፓችን ይላኩ 🙏
እናመሰግናለን

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


እናት አለኝ

እናት አለኝ የምታብስ እንባ
አያታለሁ ስወጣ ስገባ
ኪዳነምሕረት/3/ አምባ መጠጊያ ናት
አዝ
ሔዋን ሰጥታኝ ከበለሱ ፍሬ
እራቁቴን ብቆምም አፍሬ
ልብሴን ይዘሽ ወደኔ መጥተሻል
ደጓ እናቴ ቤቴን አድምቀሻል
ኪዳነምሕረት/3/ አምባ መጠጊያ ናት
አዝ
ለዘላለም ንፅሕት በመሆኗ
ከእኔ ጋር ነው ሕያው ቃልኪዳኗ
ደስተኛ ነኝ ሐዘኔን አልፌ
አፅናኝ ሆናኝ የመስቀል ስር ትርፌ
ኪዳነምሕረት/3/ አምባ መጠጊያ ናት
አዝ
ከጥፋት ውሃ ማረፊያዬ
መርከቤ ነሽ ከሞት ማምለጫዬ
የአምላክ እናት ምልጃሽ ሆኖኝ ክብሬ
በሕይወት አለሁ ጥልቁን ተሻግሬ
ኪዳነምሕረት/3/ አምባ መጠጊያ ናት
አዝ
በእናትነት ሕይወቴን ጎብኝታ
ልቤ አረፈ ተነቅሎ በሽታ
ሰንሰለቴ ከእግሬ ተቆረጠ
መራራዬ በልጅሽ ጣፈጠ
ኪዳነምሕረት/3/ አምባ መጠጊያ ናት
አዝ
ሔዋን ሰጥታኝ ከበለሱ ፍሬ
እራቁቴን ብቆምም አፍሬ
ልብሴን ይዘሽ ወደኔ መጥተሻል
ደጓ እናቴ ቤቴን አድምቀሻል
ኪዳነምሕረት/3/ አምባ መጠጊያ ናት

ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ

11.3k 0 148 29 236

እኅቴ ሙሽራዬ 

እኅቴ ሙሽራዬ ሰሎሞን ያለሽ
እኔም ልበልሽ እናቴ
እመ አምላክ ግቢ ከቤቴ
እኔም ልበልሽ እናቴ
ማርያም ግቢ ከቤቴ


ሁሉም ሰው ለራሱ ወንበር ሲዘረጋ
የክብርን ሽልማት ለራሱ ሲያስጠጋ
ድንግል እንደ ባሪያ ውሃ ተሸክመሽ
ጌታን በትህትና ታገለግያለሽ

ነይ በደመና (3)
እመቤታችን ርኅርኅተ ሕሊና

ወርቀዘቦ ለብሰው በቤቱ ከሞሉት
በሐር እና በእንቁ ከተንቆጠቆጡት
በሰው ፊት ያማሩ ብዙ ሆነው ሳለ
ጌታ ግን ወደደሽ እናቴ ነሽ አለ

ነይ በደመና (3)
እመቤታችን ርኅርኅተ ሕሊና

አሳድጎሽ ሳለ መልአኩ መግቦ
ተሸልመሽ ሳለ በዝቶልሽ ተውቦ
እጅግ በትህትና ስላገለገልሽው
እንደ ኪሩብ መልአክ ጌታን ተቀበልሽው

ነይ በደመና (3)
እመቤታችን ርኅርኅተ ሕሊና

የባሪያውን ውርደት ተመልክቷልና
የወለድሽው ንጉሥ ይድረሰው ምስጋና
ከልብ የወጣ እንጂ ከንቱ ሆኖ አይደለም
ንጽሕት እንላለን እኛም ለዘላለም


በዘማሪ ቀሲስ አሸናፊ ገብረ ማርያም

10k 0 111 2 69



✝ክርስቶስ ተንስአ እሙታን
በዐቢይ ኃይል ወስልጣን
አሠሮ ለሰይጣን
አግዐዞ ለአዳም
ሰላም
እምይእዜሰ
ኮነ
ፍሥሓ ወሰላም

ከዓመታዊ በዓላት በተጨማሪ የተመረጡ ወርኃዊ በዓላት ስርዓተ ማኅሌት ማለትም

👉12 ቅዱስ ሚካኤል
👉16 ኪዳነ ምህረት
👉19 ቅዱስ ገብርኤል
👉21 እመቤታችን
👉27 መድኃኔዓለም
👉29 በዓለ ወልድ ማኅሌት

በአገልግሎታችን ላይ ይካተታል ብለናል

ከሚያዝያ 21 ማርያም ወርሃዊ ማህሌት እንቀጥላለን


ሰላም ሰላም/2/
እምይእዜሰ ይኩን ሰላም እምይእዜሰ ይኩን ሰላም/2/


Репост из: ግእዝ ለኵሉ
ሰላምታ

✔️ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
✔️በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን

✔️አሰሮ ለሰይጣን
✔️አግዐዞ ለአዳም

✔️ሰላም
✔️እምይእዜሰ

✔️ኮነ
✔️ፍሥሓ ወሰላም

@geeZzlekulu




🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓

“እግዚአብሔር የሠራት ቀን ይህች ናት፤ ሐሤትን እናድርግ፥ በእርስዋም ደስ ይበለን።”  መዝ ፩፲፰÷፳፬

የምርቃት ጥሪ

"በጳውሎስ ኦንላይን ቅኔ ቤት"

➡️ባሕረ ሐሳብ ቀዳማይ...16
➡️ባሕረ ሐሳብ ካልዓይ.....17
➡️ግእዝ ቀዳማይ.............7
➡️ግእዝ ካልዓይ..............10
➡️ቅኔ............................7
በድምሩ 57 ተማሪዎች ይመረቃሉ።
ሚያዝያ 19/2017 ዓ.ም ከቀኑ 2:00-6:00
አራዳ ጊዮርጊስ፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

ከኢትዮጵያ ውጭ ያላችኹ እና መርሐ ግብሩን መሳተፍ ያልቻላችኹ በዚኹ ዕለት ማታ ከምሽቱ 3:00-6:00 በቴሌግራም ቀጥታ ሥርጭት በድጋሚ ስለሚቀርብ መከታተል ትችላላችኹ።

ለበለጠ መረጃ
በቴሌግራም @pawli37
በስልክ +251915642585

✝✝✝✝✝✝✝
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
❤️ዐዲሱ ቻናል ጠቃሚ ነው
❤️⬇️⬇️⬇️
https://t.me/GeezPoetry

❤️ኹሉንም ትምህርቶች በቅደም
❤️ ተከተል የሚላክበት ስለኾነ
❤️ ይቀላቀሉ። ቅኔ በቀላሉ ይወቁ




ቤዛ

ቤዛ ማለት ቃሉ የግእዝ ሲሆን ትርጉሙም አዳነ ተቤዠ ብሎ ይፈታል። ስለዚህም በየመጻሕፍቶቻችን ማዳን፣መቤዠት ለሚሉ ትርጉሞች ቤዛ...ቤዛ ሲል ይገኛል ለምሳሌ ፦

....በቈጠርሃቸው ጊዜ ከእነርሱ ሰው ሁሉ እንደ ቍጥራቸው መጠን የነፍሱን ቤዛ ለእግዚአብሔር ይስጥ
                                     *ዘጸ 30:12

° እዚህ ጋር ቤዛ ገንዘብ ተብሎ ተፈቷል ሙሴ ሕዝቡን በሚቆጥርበት ጊዜ በሕዝቡ መቅሰፍት እንዳይታዘዝ ለነፍሱ ቤዛ እንዲሰጥ ታዟል።

° ለሰው ነፍስ ቤዛው ሀብቱ ነው
                                            ምሳ 13:8

እዚህ ጋር ቤዛ ሀብት ተብሎ ተተርጉሟል እርግጥ ነው አቅንቶ ተርጉሞ ለሌላ ማድረግ ይቻላል ነገር ግን ቀጥታ ንባቡ ቤዛን ሀብት አድርጎታል።

እኔ የእስራኤል ቅዱስ አምላክህ እግዚአብሔር መድኃኒትህ ነኝ፤ ግብፅን ለአንተ ቤዛ አድርጌ፥ ኢትዮጵያንና ሳባንም ለአንተ ፋንታ ሰጥቻለሁ።
                                   
                                           ኢሳ 41:3

ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል?
ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል?

                                        ማቴ 16:26

° እዚህ ጋር ቤዛ ፈንታ ተብሎ ተተርጉሟል


  ይህን ሙሴን በቍጥቋጦው በታየው በመልአኩ እጅ እግዚአብሔር ሹምና ቤዛ አድርጎ ላከው።
                                       የሐዋ 7:35

° እዚህ ጋር ቤዛ፣ሹም፣ዳኛፈራጅ ተብሎ ይፈታል።

የኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛነት

የኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛነት ደሙ በማፍሰስ ሥጋውን በመልዕልተ ቀራንዮ በመቁረስ ተከናውኗል።

ስለ አዳም እና ልጆቹ ሁሉ ኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛ ሆኗል !

የእመቤታችን ቤዛነት

እነ ቅዱስ ያሬድ እነ ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በመጻሕፍታቸው ተባብረውበታል በጠቅላላ በሁሉም ዘመናት የተነሱ ቅዱሳን ሊቃውንት ተባብረውበታል።

የእመቤታችን ቤዛነት ክርስቶስን በመውለድ ፣ በኃጢአት ዓይኑ ለታወረበት ዓይን በመሆን ተገልጾል።

ምክር ቢጤ ፦ ይህን ሳያውቁ ስለ ቤዛ ድምዳሜ መስጠት ነውር ነው ከትልቅ ሰው አይጠበቅም።

                       መ/ር ነቢዩ ኤልያስ

ለመማር: https://t.me/Terha_Tsion
ለመወያያት:
https://t.me/Ze_Wengel 

16.3k 0 285 25 219

አንዱ አባት እመቤታችን ቤዛ አትባልም 🗣

የቤተክርስቲያናችን ሊቃውንት በማህሌቱ ላይ

ቤዛዊተ ዓለም ማርያም አስተበቁዓኪ አንሰ፤ ትቤዝዊ በኪዳንኪ ዘዚዓየ ነፍሰ፤ እስመ በሥራያ ይዕቲ ቀብዓተኒ ፈውሰ።

#ከነሐሴ_ኪዳነምህረት_ማህሌት 🥰

15k 0 26 72 212

ወረቦቹን ነገ ይጠብቁን


☀️☀️☀️☀️☀️☀️☀️☀️☀️☀️☀️☀️☀️☀️
አመ ዕስራሁ ወሡሉሱ ለሚያዝያ በዓለ ጊዮርጊስ ስርአተ ማህሌት
⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።
@EOTCmahlet
መልክዐ ሥላሴ
ሰላም ዕብል ለንዋየ ውስጥ ምሕረትክሙ። ትሩፋተ ገድል ኩኑኒ ሥላሴ አምጣነ ትሩፋት አንትሙ። ሶበ ሖርኩሰ ከመ እሳተፍ ገድሎሙ። ጊዮርጊስ ኢወሀበኒ መጠነ ነጥበ ጠል እምደሙ። ወተክለሃይማኖት ከልአኒ ስባረ እምዓጽሙ።
@EOTCmahlet
ዚቅ
በደመ ሰማዕት መዋዕያን : ወበገድለ ጻድቃን ቡሩካን : ተሣሃለነ እግዚኦ።
@EOTCmahlet
ዘጣዕሙ፦
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ። ለወልድኪ አምሳለ ደሙ። መሠረተ ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ። ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ። እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ።
@EOTCmahlet
ዚቅ
ጻድቃን ይበውኡ ውስቴታ : የዋሃን የዓውዱ መሠረታ : ሰማዕት ይቀውሙ ዓውዳ : በዕለተ ጊዮርጊስ ስብሐት የዓውዳ ለቅድስት ቤተክርስቲያን።
@EOTCmahlet
ነግሥ
ሰላም ለቆምከ ዘአዳም ቆሙ። ወለመልክዕከ በይነ ሰላሙ። ቅዱስ ጊዮርጊስ መክብበ ሰማዕታት ኲሎሙ። ሶበ መተሩ ክሣደከ ምድረ አጥለለት ደሙ። ወጊዜ ሞትከ ብርሃናት ፀልሙ።
@EOTCmahlet
ዚቅ
ሶበ መተርዎ ሶበ መተርዎ : ሶበ መተርዎ ለጊዮርጊስ : ፀሃይ ጸልመ : ወወርኅ ደመ ኮነ : ዬ ዬ ዬ : አድለቅለቀት ምድር ወተከሥቱ መቃብራት።
@EOTCmahlet
መልክዐ ጊዮርጊስ
ሰላም ለዝክረ ስምከ ዘሰሌዳ ሞገስ መጽሐፉ። ዘያሜኒ ኲሎ ወዘያስተሴፉ። ጥዑመ ዜና ጊዮርጊስ ለሀሊበ ዕጎልት ሱታፉ። ሰላምከ ወረድኤትከ በላዕሌየ ያዕርፉ። አኮ ለምዕር ዳዕሙ ለዝሉፉ።
@EOTCmahlet
ዚቅ
ከመ ሀሊብ ዘዕጎልት : ወከመ ወይን ዘገነት : ይጥዕም ስምከ ጊዮርጊስ ሰማዕት።
@EOTCmahlet
ወረብ
ከመ ሀሊብ ዘዕጎልት ወከመ ወይን ዘገነት/፪/
ስመከ ይጥዕም "ጊዮርጊስ"/፪/ ሰማዕት/፪/
@EOTCmahlet
መልክዐ ጊዮርጊስ
ሰላም ለክሣድከ ዘተመሰለ ምንሐረ። በአንቅዖ ሀሊብ ወማይ አመ በመጥባሕት ተመትረ። ጊዮርጊስ ዘፆርከ ሥቃየ ኲነኔ መጽእረ። በለኒ በቃለ ብሥራት ከመ ነሃሉ ኅቡረ። ጥቃ ቤተ ነፍስየ ለከ ሐነጽኩ ማኅደረ።
@EOTCmahlet
ዚቅ
ቅዱስ ጊዮርጊስ ሶበ ተከለለ : ደም ወሀሊብ እምነ ክሣዱ ፈልፈለ።
@EOTCmahlet
መልክዐ ጊዮርጊስ
ሰላም ለሕሊናከ ዘመከረ በልባዌ። በሞቱ ወበተንሥኦቱ ለተሳትፎ መርዓዌ። ዓቃቤ ሥራይ ጊዮርጊስ መፈውሰ ደዌ። ለወለት ከመ ቤዘውካ እምአፈ ደራጎን አርዌ። ተረፈ ሕይወትየ ቤዙ እምኲሉ ምንሳዌ።
@EOTCmahlet
ዚቅ
ጸርሐ ጊዮርጊስ በዓቢይ ቃል : ወይቤ እፎ ኢይኄሊ ከመ አምላኪየ ተሰቅለ ዲበ ዕፀ መስቀል።
@EOTCmahlet
ዚቅ ዓዲ (ወይም)
ሰኪቦ ለወልድ ትንሣኤ ሞቶ : ጊዮርጊስ ወረሰ ሰማያዊተ መንግሥቶ።
@EOTCmahlet
ዓዲ ዚቅ
ቀዊሞ ገሃደ ውስተ ዓውደ ስምዕ : ጊዮርጊስ ሰበከ ትንሣኤ ሞቱ ለበግዕ።
@EOTCmahlet
ወረብ
ወይቤ ጊዮርጊስ በዓቢይ ቃል ጸርሐ በዓቢይ ቃል ወይቤ/፪/
እፎ ኢይኄሊ ከመ አምላኪየ ተሰቅለ ዲበ ዕፀ መስቀል/፪/
@EOTCmahlet
ዓዲ (ወይም)
ጸርሐ ጊዮርጊስ በዓቢይ ቃል ወይቤ በዓቢይ ቃል/፪/
እፎ ኢይኄሊ ከመ አምላኪየ ተሰቅለ ዲበ ዕፀ መስቀል/፪/
@EOTCmahlet
መልክዐ ጊዮርጊስ
ሰላም ለፀዓተ ነፍስከ ጽዋዓ ደመ ስምዕ ሰሪቦ። እማኅፈደ ሥጋ በገድል መከራ ስቃይ ድኅረ ረከቦ። ጊዮርጊስ ስመከ ሶበ እጼውእ በአስተርክቦ። ረድኤትከ ኀበ ሀሎኩ በአርአያ ብእሲ ቀሪቦ። ለትካዘ ልብየ ዘልፈ ያሰስል ዕፅቦ።
@EOTCmahlet
ዚቅ
ጊዜ ፮ቱ ሰዓት : አጽነነ ርዕሶ #ጊዮርጊስ ወወጽአት መንፈሱ ሶቤሃ።
@EOTCmahlet
ወረብ
ጊዜ ፮ቱ ሰዓት "ጊዜ"/፪/ ፮ቱ ሰዓት/፪/
አጽነነ ርዕሶ ጊዮርጊስ ወወጽአት መንፈሱ ሶቤሃ/፪/
@EOTCmahlet
መልክዐ ጊዮርጊስ
ሰላም ለበድነ ሥጋከ እምርጢነ ገለአድ ዘተኃርየ። በላዕለ ድውያን ፈወሰ እስመ ፈድፋደ አርአየ። ጊዮርጊስ ለከ ትብለከ ነፍስየ። በበድነ ሥጋከ ተማኅጸንኩ ኢታስተኀፍር ተስፋየ። ስዕለተ ከናፍርየ ስማዕ ወፈጽም ጻህቅየ።
@EOTCmahlet
ዚቅ
ፈወሰ ዱያነ ወከሠተ አዕይንት ዕውራን : ወኲሎ ፈጺሞ አዕረፈ ጊዮርጊስ ሰማዕት።
@EOTCmahlet
መልክዐ ጊዮርጊስ
ሰላም ለግንዘተ ሥጋከ በዕደ አግብርቲከ ፪ኤ። ድኅረ ሰለጥከ መዊተ እንዘ ብከ ተስፋ ትንሣኤ። ጊዮርጊስ ዘፆርከ ሥቃየ ዓመታት ሱባኤ። ስመከ በተአምኖ ሶበ አወትር ጽዋዔ። አስራበ ረድኤትከ ያጥልል ዘዚአየ ጒርኤ።
@EOTCmahlet
ዚቅ
፯ ዓመተ ዘኮነንዎ : ለቅዱስ ጊዮርጊስ ኢመሰሎ ከመ አሐቲ ዕለት : ብእሲ ጻድቅ ቅዱሱ ለእግዚአብሔር።
@EOTCmahlet
መልክዐ ጊዮርጊስ
ሰላም ለመቃብሪከ ምክሐ አድያሚሃ ወዓጸዳ። ለምድረ ሙላድከ ልዳ። ጊዮርጊስ ዘልፈ ሀብተ በረከት ዘእፈቅዳ። ከመ ትጸጊ ሕንባበ ረዳ ለኢያሪኮ በዓውዳ። በዲበ ድማኅየ ትጽጊ እምሰማይ ወሪዳ።
@EOTCmahlet
ዚቅ
ወረደ ብርሃን ኀበ መቃብሩ ለብእሴ እግዚአብሔር : ወኮነ መቃብሩ ዘየሐዩ ዱያነ : ጸሎቱ ለጊዮርጊስ ወበረከቱ የሃሉ ምስሌነ።
@EOTCmahlet
ምልጣን
ዮም ተጽሕፈ እምነገሥት ከላሌሁ በመጥባሕት ለጊዮርጊስ ሰማዕት : ጸለየ ጊዮርጊስ ወአውዓዮሙ በነበልባል : አማን ኃያል ገባሬ ኃይል።
@EOTCmahlet
አመላለስ
አማን በአማን ኃያል 'አማን በአማን'/፪//፪/
ኃያል ገባሬ ኃይል/፬/

ወረብ፦
ዮም ተጽሕፈ እምነገሥት ከላሌሁ በመጥባሕት ለጊዮርጊስ/፪/
ጸለየ ጊዮርጊስ ወአውዓዮሙ በነበልባል አማን ገባሬ ኃይል/፪/

@EOTCmahlet
እስመ ለዓለም
ወሰበረ ኆኃተ ብርት ሞዖ ለሞት : ተንሥእ ወልድ በሣልስት ዕለት : ወአግዓዘ ነፍሰ ጻድቃን እምጽልመት ወጽላሎተ ሞት : ካዕበ ይቤሎሙ ለአርዳኢሁ : ገሊላ እቀድመክሙ።
@EOTCmahlet
እስመ ለዓለም (ዓዲ)
ንግበር በዓለ በትፍሥሕት :በአስተሐምሞ ቅድስተ ፋሲካ ተዝካረ ትንሣኤሁ ለጊዮርጊስ ነገሮ ኅቡዓተ ኲሎ ሥርዓተ ምሥጢር በደኃሪ ይትገበር ዘሀሎ በንዝኃተ ደሙ ለክርስቶስ ለመፃጉዕ ዘአሕየዎ በቃሉ ወለዕውርኒ ዘከሠተ ዓይኖ  ተንሥአ እሙታን ለአልዓዛር ተንሥእ ዘይቤሎ ወለያዕቆብ ዘአዕተዎ ብሔሮ ተንሥአ እሙታን ምዕረ ሦዓ ርእሶ ወተዓውቀ በመንፈሱ በፈቃዱ ወልድ አቅተለ ርእሶ ተንሥአ እሙታን ሲኦለ ወሪዶ ሰበከ ግዕዛነ በመስቀሉ ወልድ ገብረ መድኃኒተ ተንሥአ እሙታን ጸርሐት ሲኦለ ወትቤ ሰማያዊ ዝስኩ ዘለኪፎቶ ኢይክል።

👇👇👇👇👇👇🇪🇹
👉@EOTCmahlet👈                 
👉@EOTCmahlet👈
👉@EOTCmahlet👈
🇪🇹👆👆👆👆👆👆🇪🇹

      @EOTCmahlet
    #Join & share


🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀
አመ ፳፪ቱ ለሚያዝያ ጊዮርጊስ ሥርዓተ ዋዜማ
🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂
ዋዜማ
ዝንቱሰ ብዕሴ መስተጋድል ኮከበ ክብር ዘዓቢየ ኃይል ይገብር ተውህበ ሎቱ ሥልጣን ረገፀ ምድር አንስአ ሙታን ጊዮርጊስ ኃያል መስተጋድል
@EOTCmahlet

አመላለስ፦
ጊዮርጊስ ኃያል መስተጋድል/2/
ጊዮርጊስ ኃያል መስተጋድል/4/

እግዚአብሔር ምድር በምላህ፦
ሰአል ለነ ጊዮርጊስ ቅዱሱ ለእግዚአብሔር ሰአል ለነ ጊዮርጊስ
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
እግዚአብሔር ነግሠ፦
ትቤሎ ብእሲት መበለት ለብፁዕ ወለቅዱስ ጊዮርጊስ ሙታነ አንሳእከ በሥልጣነ አቡከ ሰናይ ገድለ ተጋድልከ
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ይትባረክ፦
አስተብፅዕዎ ወይቤልዎ እለ ይነብሩ ፈለገ እሳት ሰአል ለነ ጊዮርጊስ ቅዱስ ለእግዚአብሔር
@EOTCmahlet

ሰላም በ፫ ሃሌታ፦
ፀለየ ቅዱስ ጊዮርጊስ እንዘ ይብል እፄውአከ እግዚኦ ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚእየ ወአምላኪየ ኢትግድፋ ለነፍስየ ወዘንተ ብሒሎ ፈፀመ ገድሎ በሠናይ ወበሠላም አተወ ውስተ ምዕራፊሁ
@EOTCmahlet
አመላለስ፦
ወዘንተ ብሒሎ ፈፀመ ገድሎ በሠናይ ወዘንተ ብሒሎ/2/
ወበሰላም አተወ ውስተ ምዕራፊሁ/4/

ሰላም በ፮ (ዘእልፍኝ ጊዮርጊስ)፦
ትቤሎ ብእሲት መበለት ለብፁዕ ወለቅዱስ ጊዮርጊስ፤ ሰናይ ገድለ ተጋድልከ አምደ ቤትየ ዘአቋፀልከ ፤ሰላም ለከ ጊዮርጊስ
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
አመላለስ፦
አምደ ቤትየ ዘአቋፀልከ /፪/
ሰላም ለከ ጊዮርጊስ ሰላም ለከ/፬/

👇👇👇👇👇👇🇪🇹
👉@EOTCmahlet👈
👉@EOTCmahlet👈
👉@EOTCmahlet👈
🇪🇹👆👆👆👆👆👆🇪🇹

@EOTCmahlet
#Join & share


💖 🍒 💖

ከትንሣኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን፡፡


✞ ሰኞ- ማዕዶት ይባላል፡-
💛
ማዕዶት ማለት መሻገር፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን፡፡

✞ ማክሰኞ- ቶማስ ይባላል፡-
💛
በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ፤ "ጌታዬና አምላኬ" ብሎ መመስከሩ ይዘከራል፡፡ ዮሐ.፳፥፳፯-፳፱

✞ ረቡዕ- አልአዛር ይባላል፡-
💛
በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ፡ በድልም ያረገ ንጉሥና የባህርይ አምላክ መሆኑን እንመሰክራለን፡፡

✞ ሐሙስ- አዳም ሐሙስ ይባላል፡-
💛
በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና የተገባለት ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን፡፡

✞ አርብ- ቅድስት ቤተክርስቲያን ይባላል፡-
💛
በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ ይሰበካል፡፡ ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል፡፡

✞ ቅዳሜ- ቅዱሳት አንስት ይባላል፡-
💛
በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል፡፡

✞ እሁድ- ዳግም ትንሣኤ ይባላል፡-
💛
በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀ መዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል፡፡
💛
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን፡
#Via @EOTCmahlet 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
Join$share it

17.5k 0 348 8 230

የሚያዝያ 23 ማህሌት በቅርቡ ይጠብቁን 🥰

መልካም በዓል የእኛ ዕንቁዎች


✝ክርስቶስ ተንስአ እሙታን
በዐቢይ ኃይል ወስልጣን
አሠሮ ለሰይጣን
አግዐዞ ለአዳም
ሰላም
እምይእዜሰ
ኮነ
ፍሥሓ ወሰላም

"አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነስቷል
ሞት በሰው በኩል ስለ መጣ
ትንሣኤ ሙታን በሰው በኩል ሆኗልና፤ ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ እንዲሁ
ሁሉ በክርስቶስ ደግሞ ሕያዋን ይሆናሉና"
፩ኛ ቆሮ ፲፭፥፳
ሰላም የቻናላችን ቤተሰቦች
እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ ትንሣኤ በሰላም በጤና በፍቅር አደረሳችሁ አደረሰን። በዓሉን የሰላም የፍቅርና የበረከት ያድርግልን።

75 ሺህ ደርሰናል እናመሰግናለን 🥰

          ✝ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ✝
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹


‹‹መለኮት በሥጋ አካል በመቃብር ሳለ የሥጋ ሕይወት በምትኾን በነፍስ አካል ወደ ሲኦል ወረደ፤ እንደዚህ ባለ ተዋሕዶ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ፡፡ ከትንሣኤ በኋላ አይያዝም፤ አይዳሰስም፡፡ በዝግ ቤት ገብቷልና፡፡ ነገር ግን ምትሐት እንዳይሉት ቶማስ ዳሠሠው፡፡ የተባለውን ከፈጸመ በኋላ ቶማስ አመነበት፤›› (ቅዱስ ኤጲፋንዮስ፣ ሃይ. አበ. ፶፮፥፴፯-፴፰)፡፡
‹‹ክርስቶስ የሙታን በኵር እንደምን ተባለ? እነሆ በናይን ያለች የደሀይቱን ልጅ አስቀድሞ አስነሣው፤ ዳግመኛም አልዓዛርን በሞተ በአራተኛው ቀን አስነሣው፡፡ ኤልያስም አንድ ምውት አስነሣ፡፡ ደቀ መዝሙሩ ኤልሣዕም ሁለት ሙታንን አስነሣ፤ አንዱን ሳይቀበር፣ ሁለተኛውን ከተቀበረ በኋላ ሥጋውን አስነሣ፡፡ እነዚያ ሙታን ቢነሡ ኋላ እንደ ሞቱ፤ እነርሱ ኋላ አንድ ኾነው የሚነሡበትን ትንሣኤ ዛሬ ተስፋ ያደርጋሉ፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ግን የሙታን ትንሣኤያቸው በኵር ነው፡፡ ‹እንግዲህ ወዲህም ሞት የሌለበትን ትንሣኤ አስቀድሞ የተነሣ እርሱ ነው፤ ዳግመኛም ሞት አያገኘውም› ተብሎ እንደ ተጻፈ፤›› (ቅዱስ ኤጲፋንዮስ፣ ሃይ. አበ. ፶፯፥፫-፮)፡፡
‹‹ቃል ሥጋውን በመቃብር አልተወም፤ በሲኦልም ካለች ከነፍሱ አልተለየም፡፡ ከነፍስ ከሥጋ በአንድነት ነበረ እንጂ፡፡ ለዘለዓለም ክብር ምስጋና ይግባው፤›› (ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ ሃይ. አበ. ፷፥፳፱)፡፡
‹‹ጌታ ለደቀ መዛሙርቱ ‹በትንሣኤ ከእናንተ ጋር እስከምመጣበት ቀን ድረስ ከዚያ ወይን ጭማቂ አልጠጣም፤ በሐዲስ ግብር በምነሣበት ጊዜ የምታዩኝ እናንት ምስክሮቼ ናችሁ› ያለውን የማቴዎስን ወንጌል በተረጐመበት አንቀጽ እንዲህ አለ፤ ሐዲስ ያለው ይህ ነገር ምንድን ነው? ይህ ነገር ድንቅ ነው! መዋቲ ሥጋ እንዳለኝ ታያላችሁ፤ ነገር ግን ከትንሣኤ በኋላ የማይሞትነው፤ አይለወጥም፤ ሥጋዊ መብልንም መሻት የለበትም፤ ከትንሣኤ በኋላ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ቢበላም ቢጠጣም መብልን ሽቶ አይደለም፤ እርሱ ከሙታን ተለይቶ እንደ ተነሣ ያምኑ ዘንድ በላ ጠጣ እንጂ፡፡ ይህ ድንቅ ሥራ ነው! ያለ መለወጥ ሰው የኾነ ቃል የተቸነከረበትን ምልክት (እትራት) አላጠፋምና፡፡ በሚሞቱ ሰዎች እጅ እንዲዳሠሥ አድርጎታልና፡፡ አምላክ የኾነ ሥጋ የሚታይበት ጊዜ ነውና አላስፈራም፡፡ እርሱ በዝግ ደጅ ገባ፤ ግዙፉ ረቂቅ እንደ ኾነ ሥራውን አስረዳ፡፡ ነገር ግን በትንሣኤው ያምኑ ዘንድ የተሰቀለው እርሱ እንደሆነ የተነሣውም ሌላ እንዳይደለ ያውቁ ዘንድ ይህን ሠራ፡፡ ስለዚህም ተነሣ፤ በሥጋውም የችንካሩን ምልክት (እትራት) አላጠፋም፤ ዳግመኛም ከትንሣኤው አስቀድሞ ደቀ መዛሙርቱ ጧት ማታ ከእርሱ ጋር ይበሉ እንደ ነበረ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር በላ፤ ስለዚህም በአራቱ መዓዝነ ዓለም ትንሣኤውን አስረዱ፡፡ ከትንሣኤውም በኋላ ‹ያየነው ከእርሱም ጋር የበላን የጠጣንም እርሱ ነው› ብለው አስረዱ፤›› (ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ሃይ. አበ. ፷፮፥፯-፲፪)

ለመማር: https://t.me/Terha_Tsion
ለመወያያት: https://t.me/Ze_Wengel 


ትንሣኤ

የጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ የድኅነታችን ብሥራት በመኾኑ ለአምሳ ቀናት ያህል በቤተ ክርስቲያን በቅዳሴው፣ በማኅሌቱ፣ በወንጌሉ ወዘተ. ይዘከራል፡፡ በዚህ ሰሙን ‹‹ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን …›› እየተባለ ሞት መደምሰሱ፣ ነጻነት መመለሱ ያታወጃል፡፡ በየጊዜያቱና በየዘመናቱ የተነሡ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንም ስለ ክርስቶስ ትንሣኤ ከዚህ ቀጥሎ የተገለጠውን ትምህርትና ምስክርነት ሰጥተዋል፤
‹‹ከሙታን ተለይቶ ተነሥቶ ሲኦልን ረግጦ፣ በሞቱ ሞትን አጠፋው፤ በሦስተኛው ቀንም ከሙታን ተለይቶ ከተነሣ በኋላ ‹አባት ሆይ፤ አመሰግንሃለሁ› ብሎ ሥግው ቃል አመሰገነ፤›› (እልመስጦአግያ ዘሐዋርያት ፭፥፩)፡፡
‹‹እንደ ሞተ እንዲሁ ተነሣ፤ ሙታንንም አስነሣ፡፡ እንደ ተነሣም እንዲሁ ሕያው ነው፤ አዳኝ ነው፡፡ በዚህ ዓለም እንደ ዘበቱበት፣ እንደ ሰደቡት፣ እንዲሁ በሰማይ ያሉ ዅሉ ያከብሩታል፤ ያመሰግኑታል፡፡ ለሥጋ በሚስማማ ሕማም ተሰቀለ፤ በእግዚአብሔርነቱ ኃይል ተነሣ፤ ይኸውም መለኮቱ ነው፡፡ ወደ ሲኦል ወርዶ ነፍሳትን ማረከ፤›› (ቅዱስ ሄሬኔዎስ፣ ሃይ. አበ. ፯፥፳፰-፴፩)፡፡
‹‹እንዲህ ሰው ኾኖም ሰውን ፈጽሞ ያድን ዘንድ ታመመ፤ ሞተ፤ ተቀበረ፡፡ በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ፤›› (ሠለስቱ ምዕት፣ ሃይ. አበ. ፲፱፥፳፬)፡፡
‹‹ሞትን ያጠፋው፣ ከሙታን ተለይቶ በመነሣቱ የሞት ሥልጣን የነበረው ዲያብሎስን የሻረው እርሱ ነው፡፡ ሰው የኾነ፣ በሰው ባሕርይ የተገለጠ አምላክ ነው፡፡ እግዚአብሔር ያደረበት ዕሩቅ ብእሲ አይደለም፤ ሰው የኾነ አምላክ ነው እንጂ፡፡ ፈጽሞ ለዘለዓለሙ በእውነት ምስጋና ይገባዋል፤›› (ቅዱስ አትናቴዎስ፣ ሃይ. አበ. ፳፭፥፵)፡፡
‹‹ሥጋው በመቃብር ያሉ ሙታንን አስነሣ፤ ነፍሱም በሲኦል ተግዘው የነበሩ ነፍሳትን ፈታች፡፡ በዚያም ሰዓት የጌታችን ሥጋው በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ሳለ መቃብራት ተከፈቱ፤ ገሃነምን የሚጠብቁ አጋንንትም ባዩት ጊዜ ሸሹ፡፡ የመዳብ ደጆች ተሰበሩ (ሊቃነ አጋንንት፣ ሠራዊተ አጋንንት ድል ተነሡ)፡፡ የብረት ቁልፎቿም ተቀጠቀጡ (ፍዳ፣ መርገም ጠፋ)፡፡ ቅድስት ነፍሱ በሲኦል ተግዘው የነበሩ የጻድቃን ነፍሳትን ፈታች፤›› (ዝኒ ከማሁ ፳፮፥፳-፳፩)፡፡
‹‹ሥጋ ከመለኮቱ ሳይለይ በመቃብር አደረ፤ ነፍሱም ከመለኮት ሳትለይ በገሃነም ተግዘው ለነበሩ ነፍሳት ደኅነትን ታበስር ዘንድ፣ ነጻም ታደርጋቸው ዘንድ ወደ ሲኦል ወረደች፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ እንደ ተናገረው ቃል ዐፅም፣ ሥጋ ወደ መኾን ፈጽሞ እንደ ተለወጠ የሚናገሩ የመናፍቃንን የአእምሮአቸውን ጉድለት ፈጽመን በዚህ ዐወቅን፡፡ ይህስ እውነት ከኾነ ሥጋ በመቃብር ባልተቀበረም ነበር፡፡ በሲኦል ላሉ ነፍሳት ነጻነትን ያበስር ዘንድ ወደ ሲኦል በወረደ ነበር እንጂ፡፡ ነገር ግን ከነፍስና ከሥጋ ጋር የተዋሐደ ቃል ነው፡፡ እርሱ የሥጋ ሕይወት በምትኾን በአካለ ነፍስ ወደ ሲኦል ወርዶ ለነፍሳት ነጻነትን ሰበከ፡፡ ሥጋ ግን በበፍታ እየገነዙት በጎልጎታ በዮሴፍ በኒቆዲሞስ ዘንድ ነበረ፤ ቅዱስ ወንጌል እንደ ተናገረ፡፡ አባቶቻችን ሥጋ በባሕርዩ ቃል አይደለም፤ ቃል የነሣውሥጋ ነው እንጂ ብለው አስተማሩን፤ ይህንን ሥጋም ከሙታን ተለይቶ ከተነሣ በኋላ ቶማስ ዳሠሠው፤ በሥጋው ሲቸነከር ቃል ታግሦ የተቀበለውን የችንካሩን እትራትም (ምልክት) በእርሱ አየ፤›› (ዝኒ ከማሁ ፴፥፴፩-፴፮)፡፡
‹‹አሁን እግዚአብሔር ሞተ ሲል ብትሰማ አትፍራ፤ ‹የማይሞተውን ሞተ ሊሉ አይገባም› ከሚሉ፤ ዕውቀት ከሌላቸው፤ ሕማሙን፣ ሞቱን ከሚክዱ መናፍቃን የተነሣ አትደንግጥ፡፡ እኛ ግን በመለኮቱ ሞት እንደ ሌለበት፤ በሥጋ ቢሞትም በመለኮቱ ሥልጣን እንደ ተነሣ እናውቃለን፡፡ ሞት የሌለበት ባይኾንስ ኖሮ በሥጋ በሞተ ጊዜ ሥጋውን ባላስነሣም ነበር፤ ሥጋው እስከ ዓለም ፍጻሜ በመቃብር በኖረ ነበር እንጂ፤›› (ቅዱስ ባስልዮስ፣ ሃይ. አበ. ፴፬፥፲፯-፲፰)፡፡
‹‹ከመስቀሉ ወደ ሲኦል በመውረዱ አዳነን፤ በአባታቸው በአዳም በደል በሲኦል ተግዘው የነበሩ ጻድቃንን ፈታ፤ ከሙታን ተለይቶ አስቀድሞ በተነሣ በእውነተኛ ትንሣኤውም አስነሣን፡፡ የንስሐንም በር ከፈተልን፤›› (ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ፣ ሃይ. አበ. ፴፮፥፴)፡፡
‹‹በአባታችን በአዳም በደል የተዘጋ የገነት ደጅን የከፈተልን፤ ዕፀ ሕይወትን የሚጠብቅ ኪሩብንም ያስወገደው፤ የእሳት ጦርን ከእጁ ያራቀ፤ ወደ ዕፀ ሕይወት ያደረሰን እርሱ ነው፡፡ ፍሬውንም (ሥጋውን፣ ደሙን) ተቀበልን፡፡ አባታችን አዳም ሊደርስበት ወዳልተቻለው፤ በራሱ ስሕተት ተከልክሎበት ወደ ነበረው መዓርግ ደረስን፡፡ ክፉውንና በጎውን ከሚያስታውቅ፤ ወደ ጥፋት ከሚወስድ፤ በአዳምና በልጆቹም ላይ ኃጢአት ከመጣበት ከዕፀ በለስ ፊታችንን መለስን፤›› (ዝኒ ከማሁ ፴፮፥፴፰-፴፱)፡፡
‹‹የሕይወታችን መገኛ የሚኾን የክርስቶስ ሞት የእኛን ሞት ወደ ትንሣኤ እንደ ለወጠ እናምናለን፤ ክርስቶስም ሞትን አጥፍቶ የማታልፍ ትንሣኤን ገለጠ፤ እንደ ተጻፈ፡፡ ከሰው ወገን ማንም ማን ሞትን ያጠፋ ዘንድ፣ ትንሣኤንም ይገልጣት ዘንድ አይችልም፤ ዳዊት ‹በሕያውነት የሚኖር፤ ሞትንም የማያያት ሰው ማነው? ነፍሱን ከሲኦል፤ ሥጋውን ከመቃብር የሚያድን ማን ነው?› ብሎ እንደ ተናገረ፤›› (ቅዱስ አቡሊዲስ፣ ሃይ. አበ. ፵፪፥፮-፯)፡፡
‹‹በመለኮትህ ሕማም፣ ሞት የሌለብህ አንተ ነህ፡፡ በሥጋ መከራ የተቀበልህ አንተ ነህ፡፡ ከአብ ጋር አንድ እንደ መኾንህ ሞት የሌለብህ አንተ ነህ፡፡ ከእኛም ጋር አንድ እንደ መኾንህ በፈቃድህ የሞትህ አንተ ነህ፡፡ በመቃብር ያደርህ አንተ ነህ፡፡ በኪሩቤል ላይ ያለህ አንተ ነህ፡፡ ከሙታን ጋር በመቃብር የነበርህ አንተ ነህ፡፡ በአንተ ሕማምና ሞትም ድኅነት ተሰጠ፤ ከሙታን ጋር የተቆጠርህ አንተ ነህ፤ ለሙታንም ትንሣኤን የምትሰጥ አንተ ነህ፡፡ ሦስት መዓልት፤ ሦስት ሌሊት በመቃብር ያደርህ አንተ ነህ፤ በዘመኑ ዅሉ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የምትኖር አንተ ነህ፤ በመለኮት ሕማም ሳይኖርብህ በሥጋ የታመምክ አካላዊ እግዚአብሔር ቃል አንተ ነህ፤›› (ቅዱስ ኤራቅሊስ፣ ሃይ. አበ. ፵፰፥፲፪-፲፫)፡፡
‹‹እኛስ ኃጢአታችንን ለማስተሥረይ በሥጋ እንደ ታመመ፤ እንደ ሞተ፤ ከነፍሱም በተለየ ጊዜ ሥጋውን እንደ ገነዙ፤ ከሙታንም ተለይቶ በእውነት እንደ ተነሣ፤ ከተነሣም በኋላ በእውነት ወደ ሰማይም እንደ ዐረገ እናምናለን፡፡ በኋላም በሚመጣው ዓለም እርሱ በሕያዋንና በሙታን ይፈርድ ዘንድ ይመጣል፡፡ የሰውን ወገኖች ዅሉ በሞቱበት፤ በተቀበሩበት ሥጋ ከሞት ያስነሣቸዋል፡፡ ከትንሣኤውም በኋላ ያለ መለወጥ ዅልጊዜ ይኖራል፡፡ እርሱ በዚህ በሞተበት፤ በተገነዘበት ሥጋ ከሙታን አስቀድሞ እንደ ተነሣ፤›› (ቅዱስ ዮሐንስ ዘኢየሩሳሌም፣ ሃይ. አበ. ፶፪፥፲፩-፲፪)፡፡
‹‹የሥጋን ሕማም ለመለኮት ገንዘብ በአደረገ ጊዜ የእግዚአብሔር አካል በባሕርዩ በግድ ሕማምን አልተቀበለም፤ ሕማም በሚስማማው ባሕርዩ ኃይልን እንጂ፡፡ ሞትም በሥጋ ለእግዚአብሔር ቃል ገንዘብ በኾነ ጊዜ ሞትን አጠፋ፡፡ ከሞትም በኋላ ፈርሶ፣ በስብሶ መቅረትን አጠፋ፤›› (ቅዱስ ቴዎዶጦስ ሃይ. አበ. ፶፫፥፳፯)፡፡


እንበለ ደዌ ወሕማም
እንበለ ፃማ ወድካም
አመ ከመ ዮም
ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሣኤሁ
እግዚአብሔር በፍስሓ ወበሰላም!

"ያለ ደዌና ያለ ሕማም፥ ያለ ፃማና ያለ ድካም እግዚአብሔር ለትንሣኤው ብርሃን እንደ ዛሬ ቀን በደስታና በፍቅር በአንድነት ያድርሰን ያድርሳችሁ!"

ብለን እየጸለይን ያለ ደዌ ያለ ሕማም እስከዚች ሰዓት አድርሶናል

እንኳን አደረሳችሁ 😍

ማህሌቱን ለምትቆሙ ሁሉ መልካም አገልግሎት ይሁንላችሁ 🙏

ዛሬን በልዩ በልዩ ምክኒያት በጦርነት  በመቅደሱ ማሳለፍ ላልቻሉ ወገኖቻችን በጸሎት እያሰባችሁ (አደራ)

በተጨማሪም ለቻናላችን አገልግሎት መሳካት አስተዋጽኦ የነበራቸው አንድ የቻናላችን አፍቃሪ አሉ ውዳሴ ማርያም ከማህሌት በፊት ስትደግሙ አስቡልን

የክርስትና ስማቸው 👉 ገብረ ማርያም

እናመሰግናለን በድጋሜ መልካም በዓል ይሁንላችሁ

መልካም በዓል ❤️🙏

25.1k 0 105 43 684

ሥርዓተ ማኅሌት ዘትንሣኤ (ግእዝና አማርኛ)

ደወል እንደተደወለ ከኹሉ አስቀድሞ ነቢያት ተደግሞ ውዳሴ ማርያም በዜማ ይደርሳል።

"ተፈሥሂ ማርያም ለአዳም ፋሲካሁ" ይባላል። መልክአ ሥዕል አይባልም።

ከዚያም ተአምረ ማርያም እና ተአምረ ኢየሱስ ይነበባል። ቀጥሎም ወተንሥአ ይሰበክና ከአራቱ ወንጌላት 3ቱ ተነበው "አርያም" በተባለው ምስጋና ማኅሌቱ ይጀመራል።

ይ.ዲ ምስባክ መዝ: ፸፯ : ፷፭

ወተንሥአ እግዚአብሔር ከመ ዘንቃሕ እምንዋም፤
ወከመ ኃያል ወኅዳገ ወይን፤
ወቀተለ ፀሮ በድኅሬሁ።


እግዚአብሔር ከእንቅልፉ እንደሚነቃ ተነሣ
የወይንም ስካር እንደተወው እንደ ኃያል ሰው
ጠላቶቹንም በኋላው መታ

አርያም፦
ሃሌ ሉያ ለአብ፤ ሃሌ ሉያ ለወልድ፤ ሃሌ ሉያ ወለመንፈስ ቅዱስ፤ ቀዳሚ ዜማ ግበሩ በዓለ  በትፍሥሕት እስከ አቅርንቲሁ ለምሥዋዕ፤ ዛቲ ፋሲካ ቀዳሚት ሕግ።
ሃሌ ሉያ ለአብ፤ ሃሌ ሉያ ለወልድ፤ ሃሌ ሃሌ ሉያ ወለመንፈስ ቅዱስ ፤   ይገብሩ በዓለ ሰማያት፤ ይገብሩ በዓለ ደመናት፤ ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ተሐጺባ በደመ ክርስቶስ።


ሃሌ ሉያ ለአብ፤ ሃሌ ሉያ ለወልድ፤ ሃሌ ሉያ ወለመንፈስ ቅዱስ፤ በመጀመሪያ ዜማ በደስታ እስከ መሠዊያው ቀንዶች ድረስ በዓልን አድርጉ እርሷም የመጀመሪያዋ ሕግ ፋሲካ ናት።

ሃሌ ሉያ ለአብ፤ ሃሌ ሉያ ለወልድ፤ ሃሌ ሉያ ወለመንፈስ ቅዱስ፤ በሰማያት በዓልን ያደርጋሉ፤ በደመናት በዓልን ያደርጋሉ፤ ምድርም ፋሲካን(ደስታን) ታደርጋለች በክርስቶስ ደም ታጥባለችና።

ምልጣን
ዮም ፍሥሐ ኮነ በሰንበተ ክርስቲያን፤ እስመ ተንሥአ ክርስቶስ እሙታን፤ ቀደሳ ወአክበራ እምኲሎን መዋዕል አልዓላ፤ አማን ተንሥአ እምነ ሙታን።

ዛሬ በክርስቲያን ሰንበት ደስታ ኾነ፤ ክርስቶስ ከሙታን ተነሥቷልና፤ ከቀናቶች ኹሉ ቀደሳት፣ አከበራት፣ ከፍ ከፍም አደረጋት፤ በእውነት ከሙታን ተነሥቷል።

'አማን በአማን'/፪/ ተንሥአ 'አማን በአማን'/፪/
ተንሥአ እምነ ሙታን/፬/


'እውነት በእውነት'/2/ ተነሣ 'እውነት በእውነት"/2/
ከሙታን ተለይቶ ተነሣ /4/

ወረብ፦
ዮም ፍሥሐ ኮነ በሰንበተ ክርስቲያን/፪/
ቀደሳ ወአክበራ እምኲሎን መዋዕል/፪/


ዛሬ በክርስቲያን ሰንበት ደስታ ኾነ /2/
ከቀናት ኹሉ ቀደሳት አከበራትም /2/

እስመ ለዓለም
ትንሣኤከ ለእለ አመነ፤ ብርሃንከ ፈኑ ዲቤነ።

ትንሣኤህን ለምናምን፤ ብርሃንህን ወደእኛ ላክልን።

አመላለስ
ትንሣኤከ ለእለ አመነ/፪/
ፈኑ ዲቤነ ብርሃነከ ፈኑ ዲቤነ/፪/


ትንሣኤህን ለምናምን/2/
ብርሃንህን ወደእኛ ላክልን/2/

ከእስመ ለዓለሙ ጋር ተያይዞ  ሰላም ይፃፋል
ሰላም፦
ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ይእቲ ማርያም እምነ፤ ወእሙ ለእግዚእነ፤ ሰአሊ በእንቲአነ፤ ከመ ይምሐረነ ወይሣሐለነ፤ ያስተርኢ ኂሮቶ ላዕሌነ፤ ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ፤ ፍሥሐ ወሰላም ለእለ አመነ።

ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ማርያም እናታችን ናት፤ ለጌታችንም እናቱ፤ ስለእኛ ለምኚ፤ ይምረን እና ርቅር ይለን ዘንድ፤ ቸርነቱንም በእኛ ላይ ያሳይ ዘንድ፤ ሰንበትን ለዕረፍታችን ሠራልን፤ ለምናምን ደስታ እና ሰላም ይኾነን ዘንድ።

አመላለስ፦
ሠርዓ ለነ ሰንበት ለዕረፍተ ዚአነ/፪/
ሠርዓ ለነ ሰንበት ለዕረፍተ ዚአነ/፬/


ሰንበትን ለዕረፍታችን ሠራልን/2/
ሰንበትን ለዕረፍታችን ሠራልን/4/

ኪዳንን ከተደረሰ በኃላ

መዝሙር በ፩፦
ሃሌ ሉያ ይትፌሣሕ ሰማይ ወትትኃሠይ ምድር፤ ወይንፍሑ ቀርነ መሠረታተ ሕምዝ፤ ወይወውኡ አድባር ወአውግር፤ ወኲሉ ዕፀወ ገዳም ወዮምሰ ዓባይ ፍሥሐ በሰማያት፤ ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ተሐጺባ በደመ ክርስቶስ።

ሃሌሉያ ሰማይ ይደሰት ምድርም ሃሴትን ታድርግ፤ የጭፍሮች መሠረቶችም ኹሉ መለከትን ይንፉ፤ ተራሮች እና ቁልቁለቶችም ይደንፉ፤ የምድረ በዳ ዕፅዋትም በሙሉ ዛሬ በሰማያት ታላቅ ደስታ ነው፤ ምድርም ፋሲካን(ደስታን) ታደርጋለች በክርስቶስ ደም ታጥባለችና።

አመላለስ
ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ፤/2/
ተሐጺባ በደመ ክርስቶስ/4/

ምድርም ፋሲካን ታደርጋለች/2/
በከርስቶስ ደም ስለታጠበች /4/

ሰላም
ፍጹመ ንጉሠ ኮነንዎ አይሁድ፤ ተካፈሉ አልባሲሁ ሐራ ሠገራት፤ ወኮርዕዎ ርእሶ በኅለት፤ ረገዝዎ ገቦሁ በኲናት፤ ትንሣኤሁ ገብረ በሰንበት፤ ሰላመ ይጸጉ ለነገሥት፤ ለአሕዛብ ወለበሐውርት።


ፍጹም ነጉሥ ላይ አይሁድ ፈረዱ፤ ወታደሮችም ልብሶቹን ተካፈሉ፤ ራሱንም በዘንግ መቱት፤ በጦርም ጎኑን ወጉት፤ ትንሣኤውንም በሰንበት አደረገ፤ ለነገሥታት፤ ለአህዛብ እና ለሕዝቦች በሙሉ ሰላምን ይሰጥ ዘንድ።

ከዚህ በኃላ ወደ ሥርዓተ ቅዳሴ።

https://t.me/EOTCmahlet

26.5k 0 1.3k 14 700
Показано 20 последних публикаций.