Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
በChina እየተዘጋጀ ባለው የHumanoid robot ውድድር ብዙ አስገራሚ ነገሮች እየታዩ ነው።
በዚህ ውድድር ላይ የአለማችን ፈጣኑ ሰው የUsian Bolt የ100 ሜትር ሪከርድ ተሰብሯል።
የቻይናው ስማርትፎን እና ቴክኖሎጂ አምራች ኩባንያ Honor ያበለጸገው Lightning የተሰኘው ባለ ሁለት እግር Humanoid ሮቦት 100 ሜትርን በ9.39 ሰከንድ በመጨረስ ታሪካዊ ውጤት ማስመዝገቡ ተዘግቧል።
ይህ ሰዓት ጃማይካዊው ፈጣን ሯጭ ዩሴን ቦልት እ.ኤ.አ. በ2009 የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ያስመዘገበውን የ9.58 ሰከንድ የሰው ልጆች ክብረ ወሰን በ0.26 ሰከንድ የሚያሻሽል ነው።
Lighting ከዚህ ቀደም በሚያዝያ ወር በተካሄደው የቤጂንግ ግማሽ ማራቶን (21 ኪሎ ሜትር) ላይ ተሳትፎ 50 ደቂቃ ከ26 ሰከንድ በማስመዝገብ አንደኛ ወጥቶ እንደነበር ይታወሳል።
የስፖርት ባለስልጣናት ይህ ሰዓት በሮቦት የተመዘገበ በመሆኑ ከሰው ልጆች ኦፊሴላዊ የዓለም አትሌቲክስ ክብረ ወሰን ጋር በቀጥታ እንደማይመደብ ቢገልጹም በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እና ሮቦቲክስ ቴክኖሎጂ ውስጥ የታየ ታላቅ እመርታ መሆኑ ተነግሯል።