ለአካል ጉዳተኞች ተጠቃሚነት እውን መሆን መገናኛ ብዙኃን ከፍተኛ ሚና ሊጫወቱ እንደሚገባ ተገለፀ
ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የአካል ጉዳተኞች በተለይም መስማት የተሳናቸው የህብረተሰብ ክፍሎችን አካታችነት በተመለከተ የመገናኛ ብዙኃን ሚና ወሳኝ ስለመሆኑ ከመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡
በመድረኩ የተገኙት የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዮናስ ፋንታዬ፤ አካል ጉዳተኞች የብሩህ አእምሮና እምቅ አቅም ባለቤቶች በመሆናቸው ሁለንተናዊ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነታቸውን በማረጋገጥ የመብታቸው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከማድረግ ባሻገር ለሀገር እድገት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ለማስቻል የመገናኛ ብዙኃን ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በመድረኩ ላይ የአካል ጉዳተኞች ተጠቃሚነትን በማሳደግ ረገድ የመገናኛ ብዙኃን ሚናን በሚመለከት የመነሻ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ በውይይቱም መገናኛ ብዙኃን የአካል ጉዳተኞችን በትምህርት፣ በስራና በሌሎች የማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና በፓለቲካዊ ጉዳዩች ላይ የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች ያገናዘበና የመረጃ ተደራሽነትን ያከበረ የሚዲያ ሽፋን በመስጠት የአካል ጉዳተኞችን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ረገድ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት ሊወጡ እንደሚገባ ተመላክቷል።
የአካል ጉዳተኛ የህብረተሰብ ክፍሎች የመገናኛ ብዙኃን ተጠቃሚነት በተመለከተ በመገናኛ ብዙኃን አዋጅ 1238/2013 አንቀፅ 55/1/ኘ መሰረት ማንኛውም የብሮድካስት አገልግሎት ባለፈቃድ ለአካል ጉዳተኞች በተለየ ሁኔታ የተዘጋጁ የፕሮግራም ይዘቶችን የማሰራጨት ግዴታ እንዳለበት ይገልጻል፡፡