ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ የብሪክስ ሀገራትን አስጠነቀቁ
ከጥቂት ሳምንታት በኋላ የአሜሪካ ፕሬዝደንት በመሆን ኋይት ሀውስ የሚገቡት ዶናልድ ትረምፕ የብሪክስ ሀገራት ዶላርን በራሳቸው አዲስ መገበያያ ለመተካት ከሞከሩ ከአሜሪካ ጋር እንደሚቆራረጡ አስጠንቅቀዋል።
ትረምፕ ከደቂቃዎች በፊት በማህበራዊ ሚድያ ገፆቻቸው ላይ እንዳሰፈሩት የብሪክስ ሀገራት ከዶላር ለመራቅ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ሀገራቸው ቆማ አትመለከትም።
"እነዚህ ሀገራት አዲስ መገበያያ እንደማይፈጥሩ ወይም ዶላርን በሌላ መገበያያ እንደማይቀይሩ ማረጋገጫቸውን እንፈልጋለን፣ አለበለዛ 100 ፐርሰንት የታሪፍ ጭማሪ ይጠብቃቸዋል፣ በአሜሪካ ገበያ ላይም [ምርቶቻቸውን] እንዳይሸጡ ይደረጋሉ" ብለው ተመራጩ ፕሬዝደንት ፅፈዋል።
ኢትዮጵያን ጨምሮ ቻይና እና ሩስያ ያሉበት የብሪክስ ሀገራት ስብስብ አዲስ መገበያያ ሊኖረው እንደሚችል በመጀመርያ የተጠቆመው እ.አ.አ በ2023 ሲሆን በቅርቡ በሩስያ በተካሄደው የመሪዎች ስብሰባ ላይም በአጀንዳነት ቀርቦ ውይይት እንደተደረገበት ተዘግቦ ነበር።
ይህ አዲስ የመገበያያ ስርአት ተገፍቶበት ተግባራዊ ከሆነ እና አሜሪካ ታሪፍ፣ ማዕቀብ እና እርዳታ ብታቆም ከፍተኛ ተጎጂዎች እንደ ቻይና ያሉ ምርታቸውን በብዛት ወደ አሜሪካ የሚልኩ ሀገራት እና እንደ ኢትዮጵያ ያሉ የውጭ ብድር እና እርዳታ የሚያገኙ ሀገራት እንደሆኑ ተንታኞች ሲገልፁ ቆይተዋል።
#Ethio@EthioGlobal_News
#ፑቲን