ሰላም ቤተሰብ 💥
በዚህ ቻናል ላይ እንደጠፋሁና እንደድሮው የተለያዩ ጥናቶችን እየጻፍኩ እየለቀኩ እንዳልሆነ ታውቃላችሁ። በዛም ምክንያት ነው፣ ባለፉት አመታት ቻናላችን ከ 6K ወደ 3K ተከታዮች የወረደው - አሁን ብዙም እየቀነሰ ያልሆነውም ፕሮሞሽን ስላለ ነው። ማታ ማታ ሚለቀቀው ፕሮሞሽን ለናንተ አሰልቺ ቢሆንም ምቹ ሁኔታ እስካገኝ ድረስ ቻናሉን እንዳላጣው ሌላ አማራጭ ስለሌለ ነው።
📌 አሁን አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ ነው የመጣሁት. . .
እንዳልኳችሁ ረጃጅም ጽሁፎችንና የ YouTube ቪዲዮዎችን እየሰራው ለመልቀቅ ጊዜና የተለያዩ ነገሮች ስላልተመቹኝ፥
አጫጭር ነገሮችን እያዘጋጀው ከ 30 ሰከንድ እስከ 3 ደቂቃ የሆኑ ዝግጅቶችን ለ Tiktok በሚሆን መልኩ እያዘጋጀው በ ቲክታክ ልለቅ አስቤያለሁ; አውቃለሁ ይህም ለኔ አሁን ላይ ትልቅ ስራ ነው ግን ይጠቅማል ብላችሁ ካሰባችሁ ችግር የለውም😅🙏
እና እዚጋ የናንተን ሃሳብ መቀበል ስላለብኝ ነው ይህን የጻፍኩት ።
ከታች ያለውን Vote በማድረግ አብረን እንወስን።
አመሰግናለሁ👍`