የይርጋለም ነዋሪው ወጣት ምሳሌ ዘለቀ ለረጅም ጊዜ ላይታች በማለት ስራ ሳፈላልግ ቆይቻለሁ በማገኘው አጋጣሚም ሎተሪ ከመቁረጥ አልቦዘንኩም ፈጣሪም ጥረቴን አይቶ ዕድለኛ አድርጎኛል ይላል ወጣት ምሳሌ ፡፡ ወጣቱ በተለይ የአድማስ ዲጂታል ሎተሪን በየዙሩ ደጋግሞ እንደሞከረ ይናገራል ፡፡ እንደተለመደውም በ32ኛው ዙር የአድማስ ዲጂታል ሎተሪ ዕጣ ደጋግሞ የላከ ሲሆን በ3ኛው ዕጣ የ1ሚሊየን ብር ተሸላሚ ሆነዋል ፡፡ በደረሰው ገንዘብ ምን እንደሚሰራበት ሲጠየቅ የራሴን ስራ በመፍጠር ህይወቴን እቀይርበታለሁ በማለት ገልፀዋል ፡፡