#JJU_Students_Complaint
ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ከሁለት ወር በፊት ካስመረቃቸው ተማሪዎቹ መካከል፣ 3 ሺሕ ለሚሆት እስካሁን ጊዜያዊ ሰርተፊኬት አለመስጠቱን ዋዜማ ከተመራቂ ተማሪዎቹ ሰምታለች። ዩኒቨርሲቲው ጊዜያዊ ሰርተፊኬታቸውን ካልሰጣቸው ተመራቂዎች መካከል፣ የኢኮኖሚክስ፣ አካውንቲንግ፣ ማኔጅመንትና ፋይናንስ፣ ጋዜጠኝነት፣ ሶሲዮሎጂ፣ ሳይኮሎጂ እና የልዩ ፍላጎት ተማሪዎች እንደሚገኙበት ዋዜማ ተረድታለች። ዋዜማ ያነጋገረችው አንድ ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈለገ የኢኮኖሚክስ ተመራቂ ተማሪ፣ ዩኒቨርሲቲው ወደ 4 ሺሕ 300 ለሚጠጉ የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲና ከሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ለመጡ ተማሪዎችና ቀደም ሲል የመውጫ ፈተናውን ወድቀው በድጋሚ ለሚፈተኑ ተማሪዎች ከጥር 24 እስከ 30 ድረስ የመውጫ ፈተና መስጠቱን ተናግሯል። ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎቹ ፈተናውን ከተፈተኑ ከሁለት ሳምንት በኋላ ውጤታቸውን በበይነ መረብ አማካኝነት መልቀቁንና የምርቃት ሥነ ሥርዓታቸውም በዚያው ሰሞን መከናወኑን ገልጦ ነበር። ይሁንና ይህ ዜና እየተጠናቀረ እስካለበት እስከ ዛሬዋ ዕለት ድረስ ተማሪዎች ጊዜያዊ ሰርተፊኬታቸውን መውሰድ እንዳልቻሉና የዩኒቨርሲቲውን አሥተዳደር ሲጠይቁም የሚሰጣቸው ምክንያት የተለያየ እንደሆነ ዋዜማ ያነጋገረችው ተማሪ ገልጿል። አሥተዳደሩ ለተማሪዎቹ ከሰጣቸው ምክንያቶች መካከል፣ 'ወቅቱ የረመዳን ወር ስለሆነ ነው'፤ 'ውጤታችሁን የያዘባችሁ ትምሕርት ሚንስቴር እንጂ ዩኒቨርሲቲው አይደለም' የሚሉ እንደሚገኙበት ይሄው ተማሪ ለዋዜማ አብራርቷል። ዩኒቨርስቲው በተመሳሳይ ጊዜና በአንድ ክፍል ውስጥ ጭምር ለፈተናቸው የጤና መኮንን፣ ነርሲንግ እና የሜዲካል የላቦራቶሪ ተማሪዎች ጊዜያዊ ሰርተፊኬታቸውን መስጠቱን የገለጹት ዋዜማ ያነጋገረቻቸው ተመራቂ ተማሪዎች፣ የኛ ተለይቶ የዘገየበት ምክንያት ሊገባን አልቻለም በማለት ቅሬታቸውን ገልጸዋል። በተጨማሪም፣ ከግል ዩኒቨርስቲዎች ሄደው በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የመውጫ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ጊዜያዊ ሰርተፊኬታቸውን መቀበላቸውን ገልጸዋል። ዩኒቨርሲቲው የመውጫ ፈተናውን በሰጠ በሁለተኛው ቀን ተማሪዎቹ ግቢውን ለቀው እንዲወጡ ማድረጉን የገለጹት ተማሪዎች፣ በሺሕዎች የሚቆጠሩ ተመራቂ ተማሪዎች በጅግጅጋ ከተማ ቤት ተከራይተው ለመቀመጥ መገደዳቸውንና፣ ቀሪዎቹ ደሞ ወደ ቤተሰቦቻቸው መሄዳቸውን ተናግረዋል። ተማሪዎቹ በዚህ ወቅት የቀን ሥራና ሌሎች ጊዜያዊ ሥራዎችን በመስራት የቤት ኪራይና ለዕለት ጉርስ የሚሆናቸውን ገንዘብ ለማግኘት ጥረት እያደረጉ መሆኑንም አስረድተዋል። ከተመረቁ ሁለት ወር ሊሆናቸው የቀናት እድሜ ብቻ እንደቀራቸው የገለጹት ተመራቂ ተማሪዎቹ፣ ብዙ የሥራ ዕድሎች እያለፏቸው መሆኑንና በከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ውስጥ እያለፉ መሆኑንም አብራርተዋል። ዋዜማ በጉዳዩ ዙሪያ የዩኒቨርሲቲውን አሥተዳደር ለማነጋገር በተጋጋሚ ያደረገችው ጥረት ሊሳካ ባለመቻሉ ሃሳባቸውን ለጊዜው ማካተት አልተቻለም።
⭐ For ExitExam Questions 👇
@Exit_Exam_Questions
@Exit_Exam_Questions
⭐ትምህርት ሚኒስቴር