ቴስላ ሮቦቫን የተሰኘ አዲስ ሾፌር አልባ ተሽከርካሪ አስተዋወቀ፡፡
ሮቦቫን የሚል መጠሪያ የተሰጠዉ ሾፌር አልባ መኪና በትናንትናዉ ዕለት ቴስላ ባዘጋጀዉ የትዉዉቅ መድረክ ላይ ይፋ ተደርጓል፡፡ 20 ሰዎችን የመጫን አቅም ያለዉ መኪናዉ 30ሺህ ዶላር መሸጫ ዋጋ ተተምኖለታል፡፡
መኪኖቹ በዋናነት የታክሲ አገልግሎት እንዲሰጡ ታስበዉ እንደተሰሩ ቴስላራቲ በድረ ገጹ አስታዉቋል፡፡ የቴስላ ባለቤት ኤለን መስክ በትውውቅ መርሓ ግብሩ ወቅት እንደተናገሩት ከአውሮፓውያኑ 2027 በፊት ተሽከርካሪዎቹን ለገበያ ለማቅረብ እንደሚሰሩ ተናግረዋል ፡፡
ሮቦቫን ወደ ስራ ሲገባ የትራንስፖርት ዋጋ በመቀነስ ብሎም የመንገድ ላይ ቆይታን በማሳጠር ምቹ የሆነ የትራንስፖርት ሥነ ምህዳርን ለመፍጠር እንደሚያስችል ተመላክቷል፡፡
በፈረንጆቹ 2003 በኤሌክትሪክ የሚሰሩ መኪኖችን ለመስራት የተቋቋመዉ ቴስላ አሁን ላይ ትኩረቱን ሾፌር አልባ የሆኑ ተሽከርካሪዎች ማምረት ላይ አድርጓል ፡፡
════❁✿❁ ═══════
ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፦
ፌስቡክ አድራሻችንን
Gettechinfofb (https://www.facebook.com/profile.php?id=100022088745521)
የቴሌግራም አድራሻችንን
https://t.me/Gettechinfonow