Репост из: FDRE Education and Training Authority
#ማሳሰቢያ
ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት
ባሉበት
ጉዳዩ፦ አዲስ ተማሪዎችን ዝርዝር መረጃ እንድትልኩ ስለማሳሰብ ይሆናል፤
የፌዴራል መንግስት አስፈፃሚ አካላት ስልጣን እና ተግባር ለመወሰን የወጣ አዋጅ 1263/2014 ዓ.ም እና የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ለማቋቋም በሚኒስትሮች ምክርቤት በወጣ ደንብ ቁጥር 515/2014 ዓ.ም መሰረት በተሰጠው ስልጣን እና ተግባር የትምህርት ጥራትና አግባብነት ለማስጠበቅ እና ለመከታተል ያስችለው ዘንድ በመመሪያ 987/2016 ዓ.ም አንቀፅ 17 ንኡስ አንቀፅ 2 መሰረት አዲስ ተማሪዎችን ዝርዝር መረጃ ወቅቱን ጠብቆ ለባለስልጣኑ መላክ እንዳለባችሁ ተደንግጓል፡፡
በመሆኑም በተቋማችሁ ፈቃድ በተሰጣችሁ ትምህርት መስኮች፣ ትምህርት ደረጃ፣ መርሃ ግብር እና ካምፓስ በ2017 ዓ.ም የመዘገባቸውን አዲስ ተማሪዎች ብቻ ከዚህ በፊት በተላከው ቅጽ መሰረት ዝርዝር መረጃውን ከታህሳስ 1/2017 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 15/ 2017 ዓ.ም በሶፍት እና በሃርድ ኮፒ እንድትልኩ እናሳስባለን፡፡
በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA
በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA
በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA
በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ