╔═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╗
.......📓መጅኑኑ_ዲያሪ📓......
✎ ፀሐፊ፦𝕞𝕦𝕜𝕖𝕣𝕖𝕞
╚═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╝
┎━─━─━─━─━─━─━─━┒
🌟በ 𝕙𝕒𝕗𝕦 𝕚𝕤𝕝𝕒𝕞𝕚𝕔 𝕡𝕠𝕤𝕥 የተዘጋጀ🌟
┖━─━─━─━─━─━─━─━┚
╔════•| ✿ |•════╗
#ክፍል_ 2️⃣3⃣
╚════•| ✿ |•════╝
ፊትናው ሲከብድበት አቅሉን ሲያስተው፤
መከራው ሲበዛ ሀዘን ሲደቁሰው፤
ቀን ጣለውና የውስጡን ስብራት ሳይረዳለት ሰው፤
እድለኛ አይደለም ከመሬት እንዳለ ላም ደፍሮ ነከሰው፨
ጀናዛውን ከሆስፒታል ሳንቀበል ቀኑ ለምሽቱ ቦታውን ይለቅ ገባ።ቀስዋ ያለ እህል ውሃ እያለቀሰችና እየጮኸች የዋለችበት ጉሮሮዋ ደርቆ አቅም አጥታ ከአንዱ ወንበር ላይ አቀርቅራ ድምፅ ሳታወጣ ታነባለች።ጎረቤቶቻቸው ተሰባስበው አዩብን እንዲለቁት ቢጠይቁም የተፈነከተው ዶክተር "ይህ ልጅ በደረሰበት ተደራራቢ ሀዘን ምክንያት የአዕምሮ እክል ገጥሞታል አሁን እኛ ብንለቀው እንኳ የወደፊት የልጁ ህይወት ህክምና በማጣት ሊመሰቃቀል ይችላል ለናንተም አስጊ ይሆንባችኋል"አላቸው።ዶክተሩ የተፈነከተ ጭንቅላቱን ተሰፍቶ ታሽጎለትም የሚጨነቀው ስለ አዩብ ነበር።ከራሱ ህመም በላይ የሰውን ህመም የሚሰቃይ ምርጥ የህክምና ባለሞያ ነው።እኔም ቀስዋን አቅፌ ተቀመጥኩ።ጎረቤቶች ምን ማድረግ እንዳለባቸው ግራ ገብቷቸው በቆሙበት ሰዓት አንድ ዘመድ ነኝ የሚል ዘለግ ያለ ሰውዬ ከመሸ መጥቶ ዶክተሮችን እና ጎረቤቶችን ማናገር ጀመረ።በመጨረሻም ከመሸም ቢሆን ጀናዛውን ፈርሞ ተረከበ።ወደ ቤትም ሄድን።እዚያ ስንደርስ ድንኳን ተጥሎ ጀናዛውን የህዝብ ማዕበል ተቀበለ።"ይሄ ሁሉ ህዝብ ከየት መጣ?እስከዛሬስ የት ነበር?ለዚያውም በዚህ ምሽት?"መልስ የሌለውን ጥያቄ ለራሴ ጠየቅኩት።እኔ ቀስዋን ይዤ ከቤት ገባሁ።ቀስዋንም አባብዬ ትንሽ ምግብ እንድትመገብ አደረግኩ።ሰዉ ሌሊቱን ሙሉ በዋይታና በለቅሶ ያለ እንቅልፍ አነጋው።እኔም እንቅልፍ በአይኔ ሳይዞር ፀሃይ ወጣ።በጠዋቱ የቀብር ስነ ስርዓቱን ለማስፈፀም ሰው ይሯሯጥ ጀመረ።ብዙ ዘመዶች ከክፍለ ሃገር አዳሩን ከአዲስ አበባ ከትመዋል።በተቸገሩ ሰዓት ዞር ብሎ ያላያቸው ዛሬን እዩኝ እዩኝ አብዝቶ ጀናዛ ከአፈር ለመዶል ሲጣደፍ ማየት ሌላ ልብ የሚነካ ልብን ሌላ የሀዘን ድሪቶ የሚያከናንብ አሳዛኝ እውነት ነው።ከድንኳኑ ውስጥ ከቀስዋ ጋር በተቀመጥንበት ጀናዛውን ፈርሞ ያወጣው ሰውዬ ወደኛ መጣ።
አላት።'ይህ ሰውዬ ጤነኛ ነው?ገና እናቷን ሳትቀብር የምን መበርታት ነው የሚያወራው'ለራሴ አጉተመተምኩ።እሷም የርሱን የፌዝ የሚመስል ጥያቄ ችላ ብላ
ጮኸችበት።
በቁጣ ተናግሯት ሄደ።በራሷ የሀዘን ድግስ ማዘዝን መከጀሉ ነደደኝ።
ብላኝ አለቀሰች።የዙሁር ሰላት ሲቃረብ የእናቷን ጀናዛው ቀስዋ እንድትሰናበት አጎቷ ይዟት ገባ።ከደቂቃዎች በኋላ ህዝቡ በእንባ እየተራጨ ጀናዛውን ሸኘ።እኔም ከቀብር ቦታ ተገኘሁ።እዚያም በሰው ብዛት መደመሜን ቀጠልኩ።ዞር ዞር እያልኩ ሰዉን ስመለከት አዩብ ከአይኔ ላይ ገባ።እጆቹ በገመድ ተጠፍንገው የሆስፒታሉን የታማሚዎች ልብስ አልብሰውት ከተቆፈረው ጉድጓድ በቅርብ ርቀት ላይ በሁለት ወጠብሻ ወንዶች ተይዟል።ምንም የማስቸገር ባህሪ አይታይበትም።የማሚን ጀናዛ ከጉድጓዱ ሲጨምሩት ግን የያዙትን ወንዶች እያመለጠ ከመሬት ጋር ይጋጫል፣እየጮኸ ማልቀስ ጀመረ።የአዩብን ሁኔታ ሲመለከት የነበረው ቀብርተኛ ጩኸቱን ለቅሶውን አበረታው።በሀዘን እምባም ተራጨ።ከቀብሩ በኋላ አዩብን መልሰው በአምቡላንስ ውስጥ አስገብተው ይዘውት ሄዱ።እኛም ቤት እስከምንደርስ እምባዎቻችንን መቆጣጠር ተሳነን።ወደ ድንኳኑ ተመልሰን ሀዘናችንን ቀጠልን።ቀን ቀንን እየወለደ ማሚ ከተቀበረች ሁለት ሳምንት ተቆጠረ።ከክፍለ ሀገር የመጡ ዘመዶች ተመለሱ።ሰውም ረገብ ከማለት ጭር ወደማለቱ ተጠጋ።በዚህ መሃል አጎቷ ብቻ ነበር እስካሁን አብሮ የዘለቀው።ከኔም ጋር በትንሹ ተግባብተናል።በየቀኑ አዩብን እየሄድን እንጠይቀዋለን።አንዳንዴም ቀስዋን ይዘናት እንሄዳለን።አንድ ምሽት ቀስዋ አጎቷን
ጣልቃ ገባሁ።
ጠየቅኩት።
ይህንን ሲናገር ቀስዋ ምንም ማድረግ እንደማትችል ተረዳች።ከአልጋዋ ላይ ተደፍታ ማልቀስ ጀመረች።ሰውየው ቀስዋ በሩን ከፍታ ትጠፋለች በሚል ቁጭ ብሎ መጠበቅ ጀመረ።ሶስታችንም እንቅልፍ በአይናችን ሳይዞር የሱቢህ ሰላት አዛን ከሰፈራችን መስጂድ መሰማት ሲጀምር የመኪና ጡሩንባ ከጊቢ ውጪ ተሰማ።
ሰውየውም ታግሎ አስለቀቃት።እያለቀሰች ይዟት ሊወጣ ሲል እሷን ለማስጣል ስታገለው ሰውየው ከአልጋው ላይ ገፍትሮ ጣለኝ።ተነስቼ ተከተልኳቸው።ከመኪናው አስገብቶ ቆለፈባትና ሹፌሩን ጠብቅ ብሎት ቤት ገብቶ ያዘጋጀላትን ሻንጣ አምጥቶ ከመኪናው ላይ ጫነው።ቤቱን ጨምሮ የጊቢውን በር ቆልፎ ከመኪናው ገባ።መኪናውንም አስነስቶ መሄድ ሲጀምሩ ተሰፋ ቆርጬ ከመሬቱ ተዘረገፍኩ።ቀስዋ ከመስታወቱ ላይ ተለጥፋ እያለቀሰች እጆቿን አወዛወዘቻቸው።
ይቀጥላል .....❤️🔥
Like 1⃣0⃣0⃣+♥️ካልሆነ ቀጣዩ ክፍል አይለቀቅም🚫
★ @Hafu_posts🪄 || ★ 𝖍𝖆𝖋𝖚 𝖕𝖔𝖘𝖙🌙 ★